>

አሳዳጆቹ የሉም ቄሮ ግን ዛሬም አለ!!! (ዮሃ ንነስ)

1. የማስተርፕላኑ ጉዳይ፡-ተቃውሞ ሲገጥመው አቶ አባይ ጸሀዬ በይፋ ይህንን ጉዳይ የሚቃወሙትን ልክ እናስገባችኃለን ሲል ወ/ሮ አዜብ በበኩላቸው መፈጸሙ ለማይቀር ነገር ባይደክሙ ይሻላል ብላ ነበር፡፡ እና በቄሮ ድል አድራጊነት ፋይሉ ሲዘጋ አቶ አባይ ከፖሊሲ ጥናት ምርምር ማዕከል አመራርነት እና ወ/ሮ አዜብ ከህወሀት እና ከኢፈርት ስራ አስፈጻሚነት ከቦታቸው ተነስተዋል፡፡ እነሱ የሉም ቄሮ ግን አለ፡፡
2. ኢንሳ፡-በሙክታር ከድር ከቤኔ ጊዜ ለኢንሳ አመራሮችና እና ለተቋሙ የተሰጠውን መሬት ቲም ለማ ወደ አመራርነት ሲመጣ መሬቱን ቀምቶ ለአርሶአደሮች አስረከበ እናልህ የኢንሳው ዳይሬክተር ሜ/ጀ ተክለብርሀን…በጠ/ሚ አብይ አዲሱ ካቤኔ ከቦታው ተነሳ፡፡  እነሱ የሉም ቄሮ ግን አለ፡፡
3. ኮንትሮባዲስቶች፡-ከሻሸመኔ እስከ አዳማ፤ ከቦረና እስከ ሀር፤ ከጅማ እስከ ባሌ ኔትወርካቸውን ዘርግተው ሲቦጠቡጡ የነበሩ ኮንሮባንዲስች ክልሉ ፍሪ ዞን ሲሆን…እና እነሱ የሉም ቄሮ ግን አለ፡፡
4. ፌ.ፖሊስ ኮሚሽን፡-ኮሚሽነሩ አቶ አሰፋ አብዩ በቄሮ ላይ ጥልቅ ምርመራን ማድረግ መጀመሩን መጀመራቸውን በሪፖርተር ላይ አንብበን ነበር፡፡ አቶ ለማም ስለ ቄሮ ጥሩ የመልስ ምት በጊዜው የሰጡ ሲሆን ም/ጠ/ሚ አቶ ደመቀ በአምቦ ከተማ ቄሮ የህዳሲው መሀንዲስ ነው ብለው ፋይሉን ዘጉት፡፡ በሚገርም መልኩ ጠ/ሚ አብይ አዲስ ባዋቀሩት ካቢኔ ኮሚሽነሩን ከሀላፊነት በማንሳት በሌላ አመራር ተክተዋል፡፡ አሰፋ አብዩ የለም ቄሮ ግን አለ
5. አዲስ ካቢኔ፡-የመከላከያ ሚ/ሩ ስራጅ ፈጌሳ እና የጠ/አ/ህ ፕሬዘዳንት አቶ ጌታቸው አምባዬ መቼም በማንረሳው ንግግራቸው እና የኮማንድ ፖስቱ አስፈጻሚነታቸው ነው፡፡ እና አሁን ሁለቱም በቦታቸው የሉም …ቄሮ ግን አለ
6. አቶ ጌታቸው፡- እሳትና ጭድ እንዴት አንድ ላይ ይታያሉ ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ ብሎ ተንጨረጨረ እንደውም ይውጣልህ ተብሎ ቲም ለማ የአባይ ድልድይን ተሸግረው ባህርዳር ላይ ከተሙ፡፡ ጌች አሁን ከሚኒስትርነቱ ቦታው የለም……ቄሮ ግን አለ
7. የጠ/ሚ ምርጫ፡-ከውጤቱ ይልቅ ሂደቱ አጓጊ የነበረው የጠ/ሚ ምርጫ እጅግ አስገርሞን አልፏል፡፡ አቶ አስመላሽ ወ/ስላሴ ጠ/ሚ ከኦህዴድ ከሚሆን ሞቴን እመርጣለሁ ሲል አቶ በረከት የዶ/ር አብይ አካሄድ አብዮታዊ ዲሞክራሲን ያልተከተ ነው ብለው ነበር፡፡ እና ከመቀበል ውጪ አማራጭ አልነበራቸውም ል
8. ዳንጎቴ ሲሚንቶ፡- ፋብሪካው በክልሉ ሲገነባ የአካባቢው ነዋሪ ብዙ ተስፋ ቢያደርጉም…የአካባቢውን ወጣቶች ያገለለ ስራ መሰራቱ የሚታወስ ሲሆን በ2008 እና በ2009 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል ተቀጣጥሎ በነበረው ሕዝባዊ አመፅ ሳቢያ ሁለት ጊዜ ንብረቶቹ የተጎዱበት ዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ፣ የ2010 ዓ.ም. ዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ ባዘጋጀው የዋዜማ ድግስ ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር ዕርቅ አወረደ፡፡የዳንጎቴ ሲሚንቶ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሚስተር ዲፕ ካማራ ‹‹የኦሮሞ ሕዝብ ደግና ይቅር ባይ እንደሆነ ተነግሮኛል፡፡ ይቅር በሉና እንደ ጉዲፈቻ ልጃችሁ ተቀበሉኝ፤›› ብለው ዕርቅ ተፈጽሟል፡፡ አሁን የአካባቢው ነዋሪም ተጠቃሚ ሆኗ
እና ምን ለማለት ነው?…. አሳዳጆቹ የሉም፡፡ ቄሮ ግን ዛሬም አለ!!! የጫሉ ሁንዴሳን ጂራ የሚለውን ሙዚቃ ተጋበዙልኝ፡፡ https://www.youtube.com/watch?v=i8iVN8OBHSU
Yoha Nnes
Filed in: Amharic