>
5:13 pm - Thursday April 20, 3719

የኦሮሞን የብሄርተኝነት ግብ አታሳንሱት (ደረጄ ገረፋ ቱሉ)

1. ሌንጮ ለታ በ1970ዎቹ የኦሮሞ ቤሄርተኝነት ግቡ የኦሮሚያን ነፃ ሀገሪነት እንዲገነባ ስሰራ እና ሲንከባከብ ነበር።
ይህው ጉሙቱ ፖለቲከኛ ከ1990ዎቹ ጀምሮ የኦሮሞ ቤሄርተኝነት ግቡ ተለጥጧል ብሎ ስከራከር ነበር።ለማስተካከልም የኦሮሞ ፖለቲከኞች መገንጠልን እንደመጨረሻ ግብ መያዝ የለባቸውም ብሎ ብዙ ፅፈዋል።መንገድ ለማሳየት ምስራቅ አፍርካ እንደ የጋራ ቤት ( Horn as common homeland)  የሚል መፃፍ አላቸው።
2 በ1980ዎቹ ዶር መራራ የኦሮሞ ቤሄርተኝነት ግቡ የማይኖርት( minority)  አይነት መሆን የለበትም ብሎ ከኦሮሞ ቤሄርተኞች በተለይም ከኦነግ ደጋፍዎች ጋር እልህ አስጨራሽ ክርክር አድርጓል።ዶር መራራ ቅርንጫፍ እንጂ ግንድ አይገነጠልም እያለ ስከራከር ምን ማለት እንደሆነ ግልፅ ነው።
3 ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ኦሮሞ የኢትዮጵያ ባለቤት ፣የአክሱም ስልጣኔ ባለቤት ፣የግብፅ ስልጣኔ ባለቤት (የግብፅ ፕራሚዶችን የሰራው) ነው ይላል።ፀጋዬ ገብረ መድህን ሙሴ ኦሮሞ ነው ይላል።ፀጋዬ ገብረ መድህን የመፃፍ ቅዱስ ታሪክ የጥቁር ህዝቦች ታሪክ ነው ይላል።ፀጋዬ የኩሽ ህዝብ የአፍሪካ መሰረት ነው ይላል።የጥቁር ህዝቦች አባት ነው ይላል።የኩሽ ህዝብ ታላቁ ልጅ ኦሮሞ ነው ይላል።
እናም የታላቋ አፍሪካ አባት ኦሮሞ ነው ይላል።
ፀጋዬ በ1970ዎቹ  የኦሮሞን  ቤሄርተኝነት ከመገንጠል ጋር ካያያዙት ጋር እጅግ ተኳርፏል።የኦሮሞን ቤሄርተኝነት ግብ አሳንሳችኃል የሚል ወቀሳ ያቀርባል።
4 የኦሮሞ ቤሄርተኝነትን መልሶ ለመገንባት ብዙ መስዋዓትነት ተከፍሎበታል። የተገንባው የኦሮሞ ቤሄርተኝነት ግብ ላይ ለመስማማትም ብዙ ክርክር ተደርጓል።ያላፉት 10 ዓመታት በተለይም ያለፉት 5 አመታት የኦሮሞ ቤሄርተኝነት ስኬት በስኬት የሆነው ያለ ነገር አይደለም።የቤሄርተኝነት ግቡ ኢትዮጵያን ገንብቶ አፍሪካን በሚገንባ መልኩ ይቃኝ የሚለው ኃይል የበላይነቱን እየያዘ ስለመጣ ነው።ይህ ኃይል ሌላኛውን ምን ይላል? የኦሮሞን ቤሄርተኝነት ግብ አታሳንሱት በማለት ይኮንናል።
ለማጠቃለል ከክርክሮች ሁሉ ከአንቀፅ አረፍተ ነገር ስቦ መከራከር ፤ከአረፍተነገር ቃል ስቦ መከራከር አድካምም አስጠልታም ነው።ቀጥሎ የሚያስጠላው ነገር ነጠላ ኢቭንቶች ላይ መከራከር ነው።
ለምሳሌ በዚህ ዓመት ከተደረጉት ክርክሮች በአስጠልነቱ የማልረሳው ፕረዝዳንት ለማ የኢሬቻ በዓል ላይ ይገኝ ወይስ አይገኝ የሚለው ላይ ያደረግነው ክርክር ነው።ለማ ኢሬቻ ላይ መገኘት የለበትም ብለው የተከራከሩን ወገኖች በኃላ ላይ ደግሞ ለማ ጠቅላይ ሚንስትር ካልሆነ ብለው ተከራክረውናል።
Filed in: Amharic