>
5:13 pm - Sunday April 19, 8809

"አብይ"ን በአሁኑ ጊዜ ለጠቅላይ ሚኒስቴርነት አለመፈለግ የንቃተ-ህሊና ምጥቀት ነው፤ምክንያቱም "ዐቢይ"ን ሆነው አናገኛቸውምና፤ይመሳሰላሉ እንጂ።

(በአብይ ኢትዮጵያዊ)

ለሕዝባዊ መንግሥት ጥያቄአችን ከአርባ አራት ዓመታት በኋላም ምላሽ እናገኛለን ብለን፤በጥንቃቄ የዶክተር ዓቢይ አህመድን ምንነት መመርመርኩት።

የሚገርመው ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር”አብይ”፣”አቢይ”ይባሉ እንጂ”ዐቢይ”ን ሆነው አላገኘኋቸውም፤ዳሩ ግን ይመሳሰላሉ።
          እንዳለንበት ዘመን ሳይሆን በእነርሱ ዘመን የነበሩት ወላጆቻችን፣ሕፃናት ከመፀነሳቸው በፊት ሥም ሲያወጡላቸው፣እንደትንቢት እየታከለበትም ሆነ፤ሳይተነበይበት ባይቻል ለቆይታ፣የቤት ሥያሜ፣ከተቆረጠም ሥም ይሰጣቸዋል፤አባትና እናት ብቻ አይደሉም ሰያሚዎቹ ቤተሰቡ ይሁን ያለው ባዕድም ሊሆን ይችላል።የአመቺሳንና የክርስትናን ሥም ጨምሮ ለልጆቻቸው ይህ ቅድሚያ “የሰውነት”አስተሳሰብ የገለፅበትና የእንስሶች ችሎታ ያልሆነ፤መለያ ሥም የዕውቀት ውጤት ነው።ሥም በራሱ አንዱን ከሌላው ለይቶ መጥሪያ ረቂቅ ችሎታ እንጂ በራሱ ስያሜው ግብ አይደለም፤ግን አንዳንዴም ረቂቁ-ትርጉም ይዘው እንዲገኙ ይፈለግና ሥያሜው ከሥም በላይ ገዝፎ ይገኛል።ይህን ጥበብ የአማርኛ ፊደላት፣ረቂቅ ፍቺአቸውን በቃላትና በሐረጎች እያጠናከሩ ማስቀመጣቸውን ስንረዳ ትንታኔያቸው ግርምትን ያጭሩብናል፤በሌሎች አገሮችም እንደሚገኘው።በአንድ ወቅት በቀኃሥ ዩነቨርስቲ ለጥናት ተብሎ ከአንድ ምሁር ተፅፎ የተቀመጠው ጥናት አነበብኩ”የባሪያው ሥም በአማራው ባሕል”ይላል፤የሥምን አስፈላጊነትና የሚያደርገውን ማሕበራዊ ተፅዕኖ “መጥሪያውን” ብቻ ሳይሆን፣ከእነ “ወይ” መባያውን ጭምር ምን እንደነበር በደምብ አሳወቀኝ።
ከዚህ አንፃር ነው ዶክተር “አቢይ አህመድ” የሚባሉትን ግለ-ሰብ፣የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ተብለው ሲሾሙ(ሹመታቸውን ባልደግፈውም)በዐይነ-ሕሊናዬ በሩቁ እና በሕሊና-ዳኝነቴ አቅርቤ ውስጣቸውን ፈልቅቄ ማየት ጀመርኩ፤የሚገርመው ደግሞ ለዚህ ነው ዶክተሩ ጠቅላይ ሚኒስቴር”አቢይ”ግን “አብይ”እንጂ “ዐቢይ”ን ሆነው አላገኘኋቸውም ያልኩት።እናም የትኛው ሥም”ትልቅ”የትኛውም ሥም”አብዮት”እንደሆነና፣ከሰዋስው የፊደላት አጠቃቀም አንጻር ደግሞ”በፍፁም የሌለ”እንደሆነ ተመራምረን የምንደርስበት።ለምን ቢባል የኢትዮጵያ ሕዝብ ተስፋ ከአንድ ግለሰብ ላይ መንጠላጠል ይጀምራልና ነው።
እናም የእኛ የምንላቸው መሪዎች ቢያንስ ተስፋችንን የሚሸከሙት እኛ ሰጥተናቸው ሳይሆን አዕምሮአቸው በተገቢው መንገድ እንደ ሕዝብ አስቦ ስለሆነ ነው።ስለዚህ ዶክተሩ ሰው…ሰው…እንደሸተቱን ሳይሆኑ፤ትንፋሻቸው ሕዝብ…ስለሸተተን ነበር “እሰይ!”ብለናቸው የነበረው።ኋላም ከሕዝብ መሸሽ በመጀመራቸው ነው ሕዝብ ጥርጥር ውስጥ የመደባቸው፤ዳሩ ግን”ሕዝብ ከሚናድብህ የድንጋይ ክምር ቢናድብህ ይሻላል የሚሉት፤”የኮንሶ ሕዝብ፦ምክንያታቸውን ሲሰጡ፦”የድንጋይ ክምር ቢናድብህ ሕዝብ ተባብሮ ያነሳልህል፦ሕዝብ ቢናድብህ ማንስ ያነሳልሃል ብለው በጥያቄ ይመልሱልሃልና የሕዝብ አገልጋይ ወይስ የመንግሥት መምረጥ ግዴታ ነው።እናም ዶክተሩ እና አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስቴራችን የሕዝብ ደም እየፈሰሰ ከሃያ ሰባት ዓመታት የትግል ምጥ በኋላ በደም አበላ ውስጥ ተነክረው ተወልደዋል።ይሁን እንጂ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ የኢትዮጵያ አዳኝ ለመሆናቸው የጥርጥር ሞራን ተከናንበው መገኘታቸው ሕዝቡን በእርሳቸው ላይ ዕምነት አሳጥቶታል።
በዚህ ጽሁፌ ውስጥ እንደጀመርኩት ስለኢትዮጵያ ሕልውና አና የወደፊት ምንነቷ ለመገምገም በዘመናችን(እሷን)ኢትዮጵያችንን ከጥፋት  ለማዳን ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆኖ ዶክተር አቢይ አህመድ እንዲመረጥ ተደርጓል። ስለዚህም ለተፈጠሩት ችግሮች የመፍትሄ ቀንደኛ አካል ነው ወይም አይደለም የሚያስብል ድብቅ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል፤ስለዚህም እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የየራሱን የሕሊና ዳኝነት መነጽሩን እያነሳ በማየት፣በማስተዋል፣በማገናዘብ፣በመወያየት፤ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ትክክለኛው የችግራችን መፍቻው ቁልፍ ናቸው፣ወይም አይደሉም የሚል አከራካሪ ሁኔታዎች ሲያደርጉ ይታያሉ፤ከነዚህም ግለሰቦች አንዱ እኔ ነኝ ስል በትርፍ ጊዜዬ የጀመርኩት ኃላፊነት ሳይሆን፤ከሃያ ሰባት ዓመታት በላይ በየደቂቃዋ የታገልኩበት ኢትዮጵያዊ ግዴታዬ ነው።
    የእኔም መነሻ ጽሑፌ በዚህ ሐቅ ላይ የተመሠረተ፤አገላለጼም  በቀላሉ ሊዋጥ የማይችል ስለሆነ ሊያንቅ ይችላልና ለመዋጥ ግን ግዴታ የሚሆነው ከዕውነት በላይ(አብሶሉይት ትሩዝ)ሐቅ ስለሆነ ነው።በዚህ  ጽሁፍ ውስጥ አድራጊ፣አስደራጊ፣አደራራጊ፣ተደራጊ፣ተደራራጊ እና ሌሎችንም ርባታዎች የሚከተሉ ክንውኖችን የምናይበት ላይሆንም ይችላል፤ሐቀኛነቱን ግን ተገንዝቦ ሰዉ ሕሊናው ቅዱስ እና ቅን ተግባሮችን ብቻ መርጦ እንዲመገብ ነው።ቅንነትና ቅዱስ ተግባሮች የሕዝብ ፍላጎት ሲሆኑ ምንጊዜም የነዚህ ባሕርያት ያላቸው ሰዎች የሕዝብ ድጋፍ እና ጥበቃ አይለያቸውም።ዋናው በታሳቢነት ዐቢይ መረጃዬ ሆኖ  እና እንዲያዝልኝ የምፈልገው የመጽሐፍ ቅዱስ መለኪያዬ የ”ሰይጣን ዋናው ማጭበርበሪያ መሳሪያን”ምን እንደሆነ መግለፅ በመሆኑ እሱን አስቀድማለሁ፤እሱም “ማስመሰል”ነው።
     የሰይጣንን ክፉ ተግባራት ሁሉ ከመሠረታቸው ብናይ በ”ማስመሰል” የተፈጸሙ ርኩስ ተግባሮች ናቸው፤እሱንም የሚያመልኩ ሁሉ የወንጀሎቻቸው ምንጭ “ማስመሰል”መሆኑን በግልጽ ልንገነዘብ እንችላለን።ጠቅላይ ሚኒስቴራችንን አይደለም የማናፅረው፤መለኪያችን እንዲሆን ማገናዘቢያዬን ማጣቀሴ ነው።እናም”እሳቸውን”
በዕምነታቸው ሰበብ ጉድፍ ፈላልገው ሊያጥላሏቸው የፈለጉት፣አንዱን ሆነው አላገኟቸውም።አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስቴርን እስላም ሲሏቸው፣ክርስቲያን ይሆናሉ፤ወያኔ ሲሏቸው የሕዝብ ሆነው ብቅ ይላሉ፤አሊያም እኛ ነን ያሳደግነው ለሚሉት ትግሬዎቹ ሳይሆኑ የእናታቸው ኢትዮጵያዊነታቸውን አረጋገጡና ኢትዮጵያዊነታቸውን በአደባባይ በቃላት አረጋገጡ።ሥያሜ ነውና አባት ግን መስማማታቸውን በአደባባይ የተገለጠ ነገር የለም።የኢትዮጵያ ሕዝብ የዋዛ አይደለምና እንዴት ሆኖ ታረጋግጥልናለህ ብሎት አፋጠጣቸው።የመንግሥት አፈቀላጤ ሲባሉ የሕዝብ ብሶትን በየዓይነቱ ይደረድራሉ፤አማራም ናቸው ያሉትም ሆነ የእኛ ኦሮሞ ናቸው ብለው የተኩራሩትም ቢሆኑ በዚህ በኩል ሲያዩዋቸው ሌላውን ይሆኑባቸዋል፤የፈረንጁን ስድስት እና ዘጠኝ ቁጥር አሃዝ ሆነው፣እንደየቦታው ማንነታቸውን እንደ እሥስት ይቀያይራሉ።አጥብቆ ጠያቂ የናቱን ሞት ይረዳልና፦ከታሪክ መዝገብ የተማሩት ኢትዮጵያውያን፣ኢትዮጵያዊነታቸውን ሳይክዱባቸው ኢትዮጵያን ለጠላት ያስወጉ ባንዳዎች እንደነበሯት እያስገነዘቡ።ግማሾቹ ኢትዮጵያዊነቱ አያጠራጥረንም ግን ደግሞ ኢትዮጵያዊነቱ ለማን ነው ብለን በተግባር አይተን ልናረጋግጥ የሚያስችል በቂ ግዜ የለንምና ሕዝባዊ መንግሥት አሁኑኑ ይቋቋም ሲሉ፤እኩሌታዎቹ ደግሞ፣ቃሉን ሰጥቷል ፍላጎቱን አሳይቷል ዳሩግን”እሱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ልጅ እንዳይሆንና ሕዝብ በተሳሳተ መንገድ እንዲጠላው የሚያደርጉ ፀረ-ኢትዮጵያ የሆኑ የባንዳ የልጅ ልጆች አሉ ብለው በጥያቄ ከመወጠር ችላ አላሉም።ኢትዮጵያውያን አሉና፣ከጎኑ ሆነን ልንረዳው ይገባል፤”የሚሉ እንየውን ደግፈውታል።
የእኔ ደግሞ አስተያየት ስለአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስቴራችን አመጣጥ፣አካሄድ እና አቅጣጫ ልናገናዝባቸው የሚገቡ መሠረታዊ የታሪክ ሐቆች አሉና በጥንቃቄ ገና አልተገነዘብንም ስለዚህም አሁን ልንወስን አይገባም ባይ ነኝ።ፈረሱን አስደንብሮ ንግስቲቱን መሬት ላይ አስከስክሶ ያስገደላትን ፍለጋ ግለሰቦች ሲመራመሩ ሰኮና ጠጋኙ ባለሙያ ግን በትክክል ያልገባች ጠማማ ምስማር መሆኑን በማረጋገጥ የስንቶቹን ሕይወት ያዳነ ተቆርቋሪ ዜጋ እንደነበር በምሳሌ ዛሬም ድረስ ይነገራል።
ከዚህ የትግል መስመር አንጻር አሰላለፋቸውን በወዳጅና በጠላት ከፍለነው እንያቸው።
ሀ/ጉጅሌ ጠላት ፤ለ/ተቃዋሚዎች(ተፎካካሪ ብሎ ነገር የለም)ወዳጅ፤ በሁለቱ ተቃራኒ ቡድኖች ውስጥ የሚሰለፉትን እንደልድል።
ያሉት ሕዝባዊ ተቋማት ጠላት፤     የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ወዳጅ
የፍርድ ቤቶችና ምርጫ ኮሚሽን ጠላት፤    የሕዝብ መገናኛ ኢሳት ወዳጅ እንዲህ እያልን ብዙ መቀጠል እንችላለን፤ቁምነገሩ ሁለት ቦታ የተከፈለበት ምክንያትና ያስፈለገበት አስገዳጅ ሁኔታ፣ተገደውም ይሁን ወደው ሁለት ባሕርያት ያሏቸው አካላትና ቡድኖች በመኖራቸው ነው።ለዚህም አባባሌ ዋናው ተምሳሌት ራሳቸው አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ናቸው።ከኋላቸው ያለውን ሰበብ እና ምክንያት በእርግጠኝነት ለመናገር፣ስሊያም ራሱ ለምንገር የሚችልበት ጠንካራ ሁኔታ ላይ አይደለምና።በቀላል አቀራረብ በምሳሌ ሳስቀምጠው በገዳይ እጅ ያለ ሰው አጠገቡ ያለው ገዳዩ እንጂ የሚረዳው ሰው አለመሆኑን ገዳዩ ሳያውቅ ለሚረዳው አዳኝ ሰው እንዴት መናገር ይኖርበታል፤ይህ ነው ዶክተር አብይ ላይ እየሆነ ያለው፤ቁምነገሩ ፈልጎ ነው አይደለም ለማለት ዕውነተኛ ሁኔታውን አናውቅም።
የፈለግነውን ያህል ብንተነትነውም ዕውነተኛውን ሁኔታ አውቃለሁ የሚል ውሽታም ብቻ ነው።በመሠረቱ ሠይጣን ዓለምን የሚገዛበት አንደኛው ዓላማ ለውሸቱ መኖሪያ ሲሆን፤ዋና መሳሪያው ደግሞ “ማስመሰል”ብቻ ነው።በዘመናችንም የምናያቸው የሠይጣን ተግባሮች፣ወንጀሎች፣ቤተ ሠይጣኖች፣ቡድኖች፣ድርጅቶች በግልፅ የሚያደርጉት ይህን”ማስመሰልን” ነው።
በአንፅሩም በአብይ”የተፈጠረው ርኩስ መንፈስ አማኞችን ለማዳን ነው፣”የሚለው ተዛምቷል፤ውድ አንባቢዎቼ ይፈቀድልኝና በመረጃዎች ላስደግፈው ።በቅድሚያ ግን በሥሞቹ ስያሜ ላይ ያለውን ትርጉም ከሊቃውንት የተሰጡትን አፈታት ላስቀምጥ፤አቢይ፣አብይ እና ዐቢይ የሥም ትርጉም የሚኖራቸው ከአማርኛ ረቂቅ የቋንቋው ብስለትና የፊደል አጠቃቀም አንፃር ብቻ ነው።በአጭሩ አብይ እንቢ ማለት፡እንቢተኛ፣መጓደድ ማለት ሲሆን፤ዐቢይ ትልቅ፣ታላቅ ማለት ነው።
   በመሠረቱ ርኩስ መንፈስ የሚለው ጥገኛ ሐረግ ለምን መግባት አስፈለገ? ? ?ምክንያቱም በአንድ ጉዳይ ላይ ምንጊዜም ወይ ከቅዱስ አሊያም ከርኩስ ከሆነ ጉዳይ ጋር ስለሚያያዝ፣ስለዚህም ከሁለቱ አንዱ ብቻ ምርጫ ስለሚደግፈው ነው።እነዚህ በገሃዱ ዓለም ቢጠቃለሉም ቅዱስ እና ርኩስ ዓይነት ተብለው ለየብቻ ተከፍለዋል።እንደጉጅሌ ዓይነት መሰሪ በባዕዳን አማካሪዎችና አባባዮች የሚረዳ፤በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የዘረፈ እና እየዘረፈ የሚገኝ፤በትሪሊዮን የሚገመት ቋሚ እና ተንቀሳቃሽ ንብረት ዘርፎ ከባለቤቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያሸሸ እና በማሸሽ ላይ የተጠመደ፤በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን በድብቅና በስውር አስሮና ገድሎ ለአርባ አራት ዓመታት ተጠያቂ ሆኖ የማያውቅ፤ገንዘብ እንደተጫነች አህያ የፈለገው አገር እንደራሱ ዋሻ እየገባ የሚፈልገውን የሚያደርግ የዘመናችን ቅዱስ መሳይ ርኩስ ፍጥረት፤ቤተክርስቲያንና መስጊዶችን ሳይቀር እንደ ዳቡ እየከፋፈለ በመካከላቸው መርዝ ግንኙነት እየፈጠረ የሚያፋጅ እንዲህ በቀላሉ የመንግሥትነት ሥሙን አሳልፎ ለሕዝብ ያስረክባል ብሎ የሚመኝ፣በትክክል ላም ብቻ ሳይሆን ጥጃዎችም ዶሮችም በሰማይ ላይ አሉኝ ብሎ የማይጠገብ ወተትና የወርቅ እንቁላል እንደመጠበቅ ይቆጠራል።
ስለዚህም ሕሊናዬ ሚዛን ላይ ነገሮችን ወይም ተግባሮችን የሚያስቀምጠው ከሁለቱ የዳኝነት ልዩነት  አንጻር(ርኩስ ወይም ቅዱስ)እና አሊያም ከሁለት ነባራዊ ዓለሞች(ሥጋዊናመንፈሳዊ)ተፈጥሮዎች የሚመነጩ ናቸውና፣ከዚሁ ጋር ትንንቁ እና ትግሉ ምን ዓይነት እንደሆነ፣እንዴት መቋቋም እንደሚገባን፣በምን አይነት ሕግ፣ደንብና ፖሊሲ መሆን እንደሚገባን ለመግለፅ አይደለም።
አቶ አቢይ፣አብይ እና ዐቢይ የሥም ትርጉም ቢኖራቸውም ይህ ጠቅላይ ሚኒስቴር እና ዶክተር፣ “አብይ”(አብዮት ይጠብቃቸዋል)እንጂ አቢይም(በፊደላት ሕግ)አሊያም ዐቢይም(የመንግሥት እንጅ የሕዝብ ባለመሆናቸው)ይመስላሉ እንጂ ዐቢይ አይደሉም።
Filed in: Amharic