>

የህግ የበላይነት አፈር ድሜ መብላቱን የሚያመላ የክተው የጠቅላይ አቃቤ ህጉ ሹመት (መሳይ መኮንን)

አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ ይባላሉ። በዶ/ር አብይ ካቢኔ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሆነው የተሾሙ ናቸው። ከ7ዓመት በፊት ከሰጡት ቃለመጠይቅ የተቀነጨበውን ያዳምጡት። እንግዲህ የዶ/ር አብይ ካቢኔ ምንም ለውጥ የማያመጣ፡ የግዑዛን ስብስብ ነው የሚለውን ከሚያረጋግጡ ፍልጥ ካድሬዎች አንዱ ይህ ሰው። ዶ/ር አብይ እንደቃላቸው፡ እንደምኞታቸው እየሆኑ አይደለም። መንግስታቸው ከሚለካበት አንዱ የካቢኔ ምርጫቸው ነበር። አሰሱን ገሰሱን ሰብስበው፡ በዕውቀት የነጠፉ፡ በሞላጫነት የመጠቁትን ለቃቅመው መምጣታቸው በእሳቸው አሻግረው ተስፋን ለሰነቁ ሚሊዮኖች አንገት የሚያስደፋ ነው።
 ወ/ሮ ፈትለወርቅ የተባለች የዲሞክራሲ ጸር የሆነች ሴት ለዲሞክራሲ ክላስተር መሪ አድርጎ መሾመን የመሰለ በህዝብ መቀለድ ይኖር ይሆን? ለማንኛውም ይህን አይኑን በጨው አጥቦ የሚቀጥፍን ሰውዬ አዳምጡት። የሀገሪቱ አቃቤ ህግ ሆኖ ተሰይሟል። የእጆቿን ጥፍሮች በጉጠት የተነቀለችውን ንግስት ይርጋን፡ ጡቷ በኤሌክትሪክ ሽቦ እየተተለተለ የተገረፈችውን እማዋይሽን፡ ያለዘር ቀርቶ የተኮላሸውን ወንድማችንን፡ በግርፋትና ድብደባ ህይወታቸውን ያጡትን በርካቶችን፡ ራቁታቸውን ወፌ ላላ የተቀጠቀጡትን ሺዎችን እያሰባችሁ ይህን የዶ/ር አብይን ካቢኔ አባል አድምጡት። በዶ/ር አብይ የአመራር ዘመን የህግ የበላይነት አፈር ድሜ መብላቱን የሚያመላክት ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1724511187594516&id=100001069545702

Filed in: Amharic