>

ሌላ ቁልቁለት! ከ50 በላይ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ወጡ (ሀብታሙ አያሌው)

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ልጆች በደረሰባቸው ሐይማኖት ተኮር በደልና ጥቃት  የደቡብ ክልል ዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ግቢን ለቀው ወጥተዋል። ጠባቂ ያጡ መንጋዋች መከራቸው ቀጥሏል የህወሓቱ አባ ማትያስ እንኳን ጠበቃ ሊሆኑ አባ ጳውሎስ ከቅድስተ ማርያም እያስወጡ ለአጋዚ እንደሰጡ ሁሉ ሌጋሲውን እያስቀጠሉ ነው። ቤተክርስቲያንን ከህወሓት እስር ቤት እስካላስፈታን ገና ብዙ እንዋረዳለን አርቲስት እና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ከነገረን በላይ ገና ሌላ ቁልቁለት እንወርዳለን።

የተማሩትም እንዳልተማሩ የሚያስቡባት ዋቸሞ ዩኒቨርስቲ

ሄቨን ዮሀንስ
ይሄው ገና ፕሮቴስታንት መሪ አገኘን በማለት ይመስላል ይሄን ያህል ዓመት ፕሮቴስታንቶች ፀብ አንስተው የማያውቁትና ሰላማዊ የነበሩ ሲሆን ዛሬ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት ጀምረዋል። በዋቻሞ ዩኒቨርስቲ ከወጥ ቤጥ እስከ ፕሬዝዳንቱ ድረስ ፕሮቴስታንት ሲሆኑ ኦርቶዶክስ ማየት አይፈልጉም ።
 ተዋህዶ ናት የኢትዮጵያ ባለ ውለታ ፊደል ቀርፃ ቀለም በጥብጣ ብራና አልፍታ ይቺን ሀገር ጠብቃ የእኛ የምንለው ቀን አቆጣጠር አሰናድታ መልክ አስይዛ ትናንት እናንተ የመጣችሁ ።
በዋቻሞ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ከተዋህዶ ልጆች ጎን በመቆም ችግሩን አብረው ተጋፍጠዋል ። ይቺን ሀገር እንዴት እናድን እንዴት እናከም በሚለው አብረው መምከር ሲገባቸው ጭራሽ ችግር ይፈጥራሉ ። የእነሱ መማር ምኑ ጋር ነው ። ለዚህ ለዚህማ ይቅርባችሁ ። ይልቁንስ እንደ አባቶቻችሁ ተከባብራችሁ ብትኖሩ መልካም ነው ። እግዚአብሔር ጥጋበኞችን መቅጣት ያውቅበታል ።
ሔቨን ዮሐንስ 8/8/ 2010 ዓ.ል
Filed in: Amharic