>

የተዓቅቦ ጥሪ የወያኔ ሕገ ወጥ የንግድ ተቋም በሆነው ፋና ብሮድካስቲንግ እና ግብረአበሮቹ ላይ!!! (አምሳሉ ገብረ ኪዳን)

እንደምታውቁት ፋና ብሮድካስቲንግ (ስርጭት) በመባል የሚታወቀው የራዲዮና የቴሌቪዥን (የነጋሪተወግና የምርዓየ ኩነት) ጣቢያ ከወያኔ የንግድ ተቋማት አንዱ ነው፡፡ ፋና ብሮድካስቲንግ (ስርጭት) እየሠራ ያለው በሕገ ወጥ መንገድ ነው፡፡ ፋና ራዲዮንና ቴሌቪዥንን (ነጋሪተ ወግንና ምርዓየ ኩነትን) ሕገ ወጥ የሚያደርገው ወያኔ ሥልጣን እንደያዘ ያወጣውና ሀገሪቱን አሥተዳድርበታለሁ በሚለው ሕግ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች (የእምነተ አሥተዳደር ድርጅቶች) የኤሌክትሮኒክ ሚዲያን (ነርኸላዊ የብዙኃን መገናኛን) እና የንግድ ተቋማትን ማቋቋምና ማንቀሳቀስ እንደማይችል ስለደነገገ ነው፡፡
ያው እንደምታውቁት ወያኔ ሕግ ሲያወጣ ሌላውን ሊቀፈድድበት እንጅ ለአንድም ቀን ቢሆን እራሱ ላወጣቸው ሕጎች ተገዝቶበትና አክብሮት አያውቅምና ይሄንንም ሕግ ተላልፎ አስቀድሞ ፋና ራዲዮ የሚባለውን ጣቢያ የቴሌቪዥን ስርጭት አገልግሎት ከጨመረ በኋላ ደግሞ ፋና ብሮድካስቲንግ በሚል ሥያሜ እየተገለገለበት ይገኛል፡፡
ፋና ብሮድካስቲንግ (ስርጭት) በቅርቡ የከፈተው የቴሌቪዥን (የምርዓየ ኩነት) ስርጭት በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ “ጅብን ሲወጉ በአህያ ተጠግተው ነው!” እንዲሉ ፋና ጥቂት አንጋፋና ተዋቂ ከያኔያንን (ተዋንያንን፣ ዘፋኞችን፣ ገጣምያንን፣ ደራስያንን፣ ጸሐፍያንን ወዘተረፈ.)  በመጠቀም ራሱ ጣቢያው ትኩረት ይስብልኛል፣ ተወዳጅነትን ያስገኝልኛል ብሎ የቀመረላቸውን የቀረጸላቸውን ዝግጅቶቻቸውን የሚያቀርቡባቸውን የአየር ሰዓት በመመደብ ወደ ሕዝብ ለመቅረብ፣ ተመልካች ለማፍራት፣ ተቀባይነት ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ ይሁንና ጣቢያው ለቀረጻቸው ዝግጅቶችና ላስጻፋቸው ተከታታይ ድራማዎች (ትውንተ ኩነቶች) በፈለገው መጠን ብቃትና ጥራት ለማሠራት ብዛትና ብቃት ያላቸውን ከዋኞች ማግኘት ስላልቻለ በአብዛኛው በሥራቸው ያልተሳካላቸውንና ማንም ሊያገኛቸው የሚችላቸውን  ጀማሪ የኪነት ሰዎችን ለማካተት ተገዶ ከንነሱ ጋር እየሠራ ይገኛል፡፡
ፋና ስርጭት የቴሌቪዥን (የምርዓየ ኩነት) አገለግሎትንም የከፈተው ለሁለት ዋና ዋና ዓላማዎች ነው፡፡ አንደኛው ፋና ራዲዮ (ነጋሪተ ወግ) ለዘመናት ሲያደርገው እንደኖረው ሁሉ የሆነውን እንዳልሆነ ያልሆነውን እንደሆነ እያደረገ በመንዛት የወያኔን የፖለቲካ (የእምነተ አሥተዳደር) ጥቅም ለማስጠበቅ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ አሁንም ፋና ራዲዮ ለዘመናት ሲያደርገው እንደኖረው ሁሉ የወያኔን የትግሮችንና የአጋር ባለሀብቶችን ሁሉን አቀፍ የተሳሰረ የቢዝነስ ኢምፓየር (የንግድ ግዛት) በበለጠ ደረጃ ስኬታማ ለማድረግ ነው፡፡
በዚህም መሠረት ይህ የቴሌቪዥን ሥርጭት እንደምታዩት፦
1ኛ. ሬዲዮ ፋና ሲያደርገው እንደኖረው ሁሉ ወያኔ ላለበት የፖለቲካ ቀውስ ሕዝብን የመደለያና የማታለያ፣ ሐሰተኛ ፕሮፖጋንዳ (ልፈፋ) መንዣና ቀውስ መቆጣጠሪያ በመሆን፣ ወያኔ ጠላቴ የሚለውን አካል መውጊያ፣ ስም ማጥፊያና ቅስም መሥበሪያ በመሆን፡፡
2ኛ. ገና ከመጀመሩ የወያኔን፣ የወያኔ/ኢሕአዴግ ባለሥልጣናትን፣ የትግሮችንና የጥቂት አጋር ባለሀብቶችን የንግድና የአገልግሎት ሰጭ ድርጅቶችን በተለያዩ ዝግጅቶች ስልታዊ በሆነ መንገድ አገልግሎታቸውንና ሸቀጦቻቸውን እያጋነኑ በማስተዋወቅ ለድርጅቶቹ ሽፋን በመስጠት የገበያው አቅጣጫ ወደእነሱ እንዲያመራ የተጠናና የታሰበበት ሥራ መሥሪያ በመሆን በከፍተኛ ደረጃ እየተጠቀመበት ይገኛል፡፡
ይታያቹህ! እነኝህ የወያኔ፣ የትግሬና የአጋር ባለሀብቶች የንግድና የአገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች አብዛኞቹ ቀረጥና ግብር ሳይከፍሉ የሚነግዱና አግባብ ያልሆነ ሕገወጥ ጥቅም የሚያግበሰብሱ ከመሆናቸው በተጨማሪ እነኝህ የንግድና አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች ጥራት ያለው አገልግሎታቸው የብዙኃን መገናኛን ትኩረት የሳበ ባስመሰለ አቀራረብ እንዲያ ባሉ ዝግጅቶች ሽፋን በመስጠት ገበያውን ጠቅልለው እንዲወስዱት በብዙኃን መገናኛዎቻቸው ሲታገዙ የቆዩ በመሆናቸው የንግዱ ማኅበረሰብ ከነሱ ጋር ፈጽሞ መፎካከር ስላልቻለ ብዙኃኑ የንግድ ማኅበረሰብ በከባድ ኪሳራ ከገበያ ውጭ በመሆኑ በአሁኑ ሰዓት አጠቃላዩ የንግዱ እንቅስቃሴ በትግሬ ተጠቅልሎ እየተያዘ ይገኛል፡፡
እንግዲህ ይታያቹህ እንዲህ ዓይነት ሸፍጥና ሴራ በሕዝብ ላይ እየፈጸመ የወያኔ ዘረኛ አንባገናዊ አገዛዝን ዕድሜ ለማራዘም፣ ሀብት ሁሉ በትግሬ በሞኖፖሊ (አጠቃሎ መያዝ) ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ ተግቶ ለሚሠራ የወያኔ የብዙኃን መገናኛ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነትን አግኝቶ እነኝህን ሸፍጠኛ ተግባሮቹን በብቃት መሥራት እንዲችል ለሱ መጠቀሚያ መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ አስቡት!!!
ፋና የማንና ምን እንደሚሠራ ጠንቅቀው እያወቁ በቀረበላቸው አማላይ ጥቅም ተደልድለው ሀገርንና ሕዝብን በመካድ እያደረጉት ባለው መልኩ ወያኔን እየተባበሩና እያገለገሉ ካሉ አንጋፋ ከያኔያን ውስጥ አቶ ደበበ እሸቱ፣ አቶ ፈቃዱ ተክለማርያም፣ አቶ ተፈሪ ዓለሙ፣ ወ/ሮ ዓለምፀሐይ በቀለ ይገኙበታል፡፡ አሁን በቅርቡ ደግሞ አቶ ደበበ እሸቱ ይመስለኛል ድለላውን የሠራው ዓለም ፀሐይ ወዳጆ የቀድሞ የጥላሁን ጉግሳ ባለቤት ወ/ሮ ሔለንና ሌሎች ሦስት ሴቶች በሚያዘጋጁት ወርቃማ ሴቶች ለተሰኘ ዝግጅት ተባባሪ አዘጋጅ ሆና ልትሠራ ነው፡፡
ከወጣቶቹ ደግሞ አቶ ዓለማየሁ ታደሰ፣ ወ/ሮ አዜብ ወርቁ፣ አቶ ሚካኤል ታምሪ፣ አቶ ሰኢድ ሙሔ ይገኙበታል፡፡ ከጀማሪዎቹ ውስጥ ደግሞ ዳሸን ቢራ በሕዝብ በመጠላቱ ስሙን ለመቀያየር ተገዶ ማስታወቂያ የሚሠራለት ዘፋኝ ባጣ ጊዜ ማስታወቂያ የሠራለት የጃኖ ባንዱ ዘፋኝ ዲበኩሉ ታፈሰ፣ በቅርቡ የሙዚቃ አልበሙን (የዘፈን ጥራዙን) የለቀቀው መሳይ ተፈራ ይገኙበታል፡፡
ስለእውነት ነው የምላቹህ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻ ለመውጣት ከወያኔ ጋር ጉርቦ ለጉርቦ ተናንቆ እየታገለና መራራ መሥዋዕትነትን እየከፈለ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ሕዝቡ በወያኔ የንግድ ድርጅቶች ላይ ማዕቀብ ጥሎ እንዳይንቀሳቀሱ በማድረግ፣ ምርቶቻቸውንና አገልግሎታቸውን ያለመጠቀም ያለመገብየት ተዓቅቦ አድርጎ ብዙዎቹን ኪሳራ ላይ በመጣል ድል እያስመዘገበና ወያኔን እያንበረከከ ባለበት በዚህ ሰዓት እነኝህ አንጋፋ ከያኔያንና ታዋቂ ሰዎች የግል ጥቅማቸውን ብቻ በማሰብ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም በተፃራሪ በመቆም የወያኔ ቅጥረኛና መጠቀሚያ ሆነው የፋና ሥርጭት በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝና ወያኔ የራሱን ጥቅም ማስጠበቅ እንዲችል በሙሉ ፈቃደኝነትና በጋለ ስሜት እየረዱት እየተባበሩት እንደሆነ ሳይ እውነቴን ነው የምላቹህ እጅግ በጣም ነው ሐዘን የተሰማኝ የከፋኝም፡፡
“እንዴት በዚህ ጊዜ እነኝህ ሰዎች እንደዜጋ በቻሉት መጠን ሕዝባዊ ትግሉን ማገዝ ሲኖርባቸው እንዴት በሚቃረን መልኩ የወያኔ ተባባሪው ሊሆኑ ቻሉ?” የሚለው ጥያቄም፦
* ግን እነኝህ ሰዎች በትክክልስ ማሰብ ይችላሉ ወይ???
* ላከበራቸውና ለዚህ ደረጃ ላበቃቸው ሕዝብስ ክብር አላቸው ወይ???
* እነኝህ ግለሰቦች ይሄንን እያደረጉ እንዴት ነው ሀገርንና ሕዝብን እንደሚወዱ የሚናገሩትን ነገር ሕዝቡ እውነት አድርጎ እንዲያስብላቸው የሚጠብቁት???
* ለሕዝብ ክብር ቢኖራቸውና ዘወትር እንደሚሸነግሉን ሀብታቸው ሕዝብ እንደሆነ ቢያምኑ ኖሮ፣ ቢወዱት ኖሮ ከጠላቱ ከገዳዩ ጋር ተሰልፈው ለጠላቱ ለገዳዩ ስኬት ተግተው በመሥራት ሕዝብን ከጀርባው ይወጉት ነበረ ወይ???
* ከሕዝብ ጠላት ጋር ተሰልፈው ለሕዝብ ጠላት እየሠሩ እንዴት ነው የሕዝብ ጠበቃነት፣ የእውነት መስካሪነት፣ የሕዝብ ብሶት መተንፈሻ መሣሪያ የሆነን የተከበረ ሞያ ባለቤት ነን ብለው “የከያኔ ነፍስ አለን ከያኔያን ነን!” ሊሉ የሚችሉት???
* ሕዝብ ስለወደደና ስላከበረ በዚህ ደረጃ መናቅ፣ መካድ ነበረበት ወይ???
* ካልናቁት በስተቀር እንዴት ነው በሕገወጥነቱ መዘጋት ላለበት ለወያኔ የንግድ ተቋማት መልማትና መደርጀት በመሥራት በሕዝብና በሀገር ላይ ጉዳት ለማድረስ የሚጥሩት??? አሰኝቶኛል፡፡ ግን በእርግጥስ እነኝህ ሰዎች ይሄንን ሁሉ ነገር ማሰብ ማገናዘብ አለመቻላቸው ምንን ያመለክታል???
እነኝህና ሌሎቹ ያልተጠቀሱ ግለሰቦች የጥፋት ኃይል የሆነውን ወያኔን በዚህ መልኩ ሲያገለግሉ ሀገርንና ሕዝብን እየወጉ እያደሙ በመሆናቸው በግል የቱንም ያህል አማላይ ክፍያ ቢከፈላቸው እንኳ በምንም ተአምር ቢሆን ተጠቃሚ አለመሆናቸውን መገንዘብ የሚያስችል ንቃተ ሕሊናና ማስተዋል ስለሌላቸው ነው ለፍርፋሪ ብለው የሀገርንና የሕዝብን ጠላት እያገለገሉ መጠቀሚያ ሆነው የሚገኙት፡፡ እንዲያው ግን ሀገርንና ሕዝብን ማሰብ ባይችሉ እንኳ እንዴት ለስማቸውና ለግል ታሪካቸው አይጨነቁም??? ስንት ዓመትስ ሊኖሩ ነው ባለቀ ሰዓት የሚያልከሰክሳቸው???
እባካቹህ እነኝህን አንጋፋና ታዋቂ ከያኔያንን ማለትም በፋና ቴሌቪዥን በሚተላለፉና በፋና ወጪ በተዘጋጁ ተከታታይ ድራማዎች (ትውንተ ኩነቶች) ፣ የተለያዩ የፋና ዝግጅቶች አዘጋጅ የሆኑ ታዋቂ ሰዎች፣ በተለያዩ የፋና ውይይቶች የሚሳተፉ ምንም የማይገባቸውና የማይነቁ ፖለቲከኛ (እምነተ አሥተዳደራዊ) ነኝ ባዮችና ታዋቂ ሰዎች ለፋና በመሥራትና በፋና ዝግጅቶች በመቅረብ ፦
* መጠቀሚያ መሆናቸውንና የሕዝብን ትግል እየተቃረኑ፣ ለሕዝባዊ ትግሉ እንቅፋት እንደሆኑ እየነገራቹህ ከዚህ ተግባራቸው እንዲታቀቡ ንገሩ፣ ምከሩ፣ አስጠንቅቁ???
* ለሕዝብና ለሀገር ጠላት ሆነው እየሠሩ መሆኑን እንዲያውቁ እንዲረዱ እንዲገነዘቡ አድርጓቸው???
* የማይታረሙ፣ የማይታቀቡ፣ የሕዝብን ምክር መረዳት መቀበል  የማይፈልጉ ከሆኑ እኛም በስውር የያዙትን ካድሬነት (ወስዋሽነት) በይፋ ለማስታወቅ እንደፈለጉ ቆጥረን ወያኔን በምናይበት ዐይን እንደምናያቸውና በሥራዎቻቸው ላይ ማዕቀብና ተዓቅቦ እንደምንጥልባቸው፣ ከጠላታችን ከወያኔ ጋር ተባብረውብናልና ከወያኔ ጋር ደርበን እንደምናጠቃቸው ወይም እርምጃ እንደምንወስድባቸው፣ ወያኔ የሚከፍለውን ዋጋ ለመክፈል የሚገደዱ መሆናቸውን  ንገሯቸው፣ አስጠንቅቋቸው??? ቀልድ የለም!!! ሕዝብ እየሞተና መራራ ዋጋ እየከፈለ ነው ያለው፡፡ ከወያኔ ጋር ተሰልፎ ሕዝብንና ሀገርን ለሚወጋ ባንዳ ቅጥረኛ ሁሉ ምንም ዓይነት ምሕረት ሊኖረን አይገባም!
ከሕዝቡ በኩልም ፋና ቴሌቪዥንንና ሬዲዮን ባለመመልከትና ባለማዳመጥ፣ ከዚህም በላይ የወያኔና የትግሬ የንግድና የአገልግሎት ሰጭ ድርጅቶችን ባለመጠቀም ወይም ተዓቅቦ በማድረግ፣ በፋና የሚተዋወቁ የንግድ ድርጅቶች ሸቀጦችንና አገልግሎቶችን ባለመጠቀም ባለመገበያየት፣ ነጻ የንግድ ድርጅቶችም በፋና ማስታወቂያን ባለማስነገር ለወያኔ ሕገወጥ የብዙኃን መገናኛና የንግድ ድርጅቶች ያለንን ተቃውሞ እንግለጥ፣ ሕዝባዊ ትግሉንም ልድል እናብቃ!!! ተዓቅቦው እንደአስፈላጊነቱ ኢቴቪንም ይመለከታል፡፡
በዚህ አጋጣሚ እንዳለኝ መረጃ ፋና በጥቅማጥቅም በመደለል የአየር ሰዓት ወስዳቹህ አብራቹህት እንድትሠሩ ሲጠይቃቹህ፣ በዝግጅቶቹ በእንግድነት እንድትቀርቡ ሲጠይቃቹህ የወያኔ መጠቀሚያ ላለመሆን፣ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም በተፃራሪ ላለመቆምና የሕዝብ ጠላት ላለመሆን “ጥቅሙ በአፍንጫዬ ይውጣ!” ብላቹህ የተለያየ ምክንያት በመስጠት ጥያቄውን ያልተቀበላቹህ ከያኔያን፣ ምሁራንና ታዋቂ ሰዎች አድናቆቴን መግለጥና ማመስገን እወዳለሁ ጀግኖች ናቹህ! ተባረኩ! ያጽናቹህም!!!
የእነኝህ ጀግና ከያኔያን ፈቃደኛ አለመሆን ነው ፋና ያገኘውን ሁሉ እንዲሰበስብ ያደረገው፡፡ ምሳሌ ብጠቅስ ፋና ለአንድ ኮሜዲያን (አሳቂ) ነኝ ለሚልና ሁሌም ሥራውን ሲያቀርብ ለሕፃናት የሚያቀርብ ለሚመስለው ደረጀ “ጥበብ በፋና!” የሚል አቅሙ የማይፈቅድለትን ዝግጅት አሸክመውት ዝግጅቱን እንዲመራ በጋባዥነት (በሆስትነት) ሠይመውታል፡፡ ይገርማቹሀል እኔ በግሌ ይሄ ሰው ቀልድ ብሎ በሚያቀርባቸው ነገሮች በስሕተት ለአንድ ጊዜም እንኳ አስቆኝ አያውቅም፡፡ እናም ኃላፊነት የሚሰማቸው ከያኔያን፣ ምሁራንና ታዋቂ ሰዎች እምቢታ ፋናን እንዲህ እንዲህ ዓይነቶችን ያልተሳካላቸውንና አቅም የሌላቸውን ሰዎች በአዘጋጅነት እንዲሁም ጀማሪ ዘፋኞችን በተዋናይነት እንዲያካትት አስገድዶታል፡፡
የተዓቅቦ (boycott) እርምጃ ከወያኔ ጋር የተያያዝነውን የሞት ሽረት ትግል በድል ለማጠናቀቅ ቁርጠኝነትን እንጅ ምንም ዓይነት ወጭንና የደም መሥዋዕትነትን የማይጠይቅ ለድል የሚያበቃ ዓይነተኛ መሣሪያ ነው፡፡ ሲቻል ደግሞ የማዕቀብ (sanction) እርምጃም እንዲሁ አስፈላጊና ጠቃሚም ነው፡፡ እናም በደንብ ልንጠቀምበት ይገባልና እባካቹህ በዚህ ላይ እንረባረብ ተግተን እንሥራበት??? ሕዝባችን ተዓቅቦን የሚያክል ትልቅ መሣሪያ እንዲጠቀምበት እናንቃው???
ተሿሚው ጠ/ሚ ለይስሙላም ቢሆን እስከአሁን ስንቱን ነገር ሲወሸክት ሀገር እየበዘበዙ፣ እየዘረፉ፣ እያራቆቱ ስላሉት ኤፈርትና ሌሎች ሕገወጥ የወያኔ የንግድ ድርጅቶች እንዲሁም ስለዚህ ስለ ፋና እና ድምፀ ወያኔ የመሳሰሉ ሕገወጥ የብዙኃን መገናኛዎች አንድም ያለው ነገር የለም! ይኖራል ብለንም አንጠብቅም፡፡ ዐቢይ በእነዚህ ሕገወጥ ድርጅቶች ጉዳይ ላይ ምንም ነገር ማለት ካለመፈለጉና እርምጃም መውሰድ ካለመፈለጉ መረዳት የምንችለው ዐቢይ ቁምነገር ቢኖር ዐቢይ “እንዲህ እንዲሆን ይደረጋል!….፣ ጽኑ እምነት አለን!…” እያለ የሚደሰኩረው ነገር ሁሉ ባዶ ፉገራ መሆኑን ነው ቁልጭ አድርጎ የሚያሳየው፡፡
በወያኔ ሕገወጥ የብዙኃን መገናኛ እና ሕገወጥ የንግድ ድርጅቶች ተዓቅቦ እና ማዕቀብ እናጧጡፍ!!! አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ወያኔን በቀላሉ ማንበርከክ የምንችልበት ታላቅ መሣሪያችን ይሄና ይሄ ብቻ ነውና እባካቹህን አንድ ኢትዮጵያዊ ሳይቀር እዚህ ላይ እንረባረብ!!! ያለጥርጥር አሸናፊዎች እንሆናለን!!!
 ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
Filed in: Amharic