>
5:13 pm - Sunday April 19, 5739

ማነዉ የቋንቋ Phobia ያለበት?? (ሚኪ አምሀራ)

ዋና አጀንዳችን ለማሳትና የአማራ Phobia እንደለመዱት የተነሳባቸዉ ሰወች ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትግርኛም ሆነ በኦሮሞኛ ቢናገር ምንድን ነዉ ችግሩ የሚልና ይሄን ያነሱት የአማራ ልጆች እንደሆነ አድርገዉ የሚጽፉትና የሚናገሩት ያን የ 27 አመት አማራ እንዲህ  እንዲያ ነዉ እያሉ የተዛባ አመለካከት ሌላዉ ላይ ሲፈጥሩት የቆዩት አይነት ፕሮፖጋንዳ ነዉ፡፡ አማራ የቋንቋ Phobia ሆነ የሌላዉን የማንኛዉንም ህዝብ Phobia የለበትም፡፡  ከ10  ሚሊየን በላይ በኦሮሚያ ዉስጥ የሚኖር አማራ ወይ ኦሮሞኛ አቀላጥፎ ይናገራል ወይም ያፍ መፍቻ ቋንቋዉ ነዉ፡፡ 1.5 ሚሊየን በትግራይ የሚኖር አማራ ወይ ትግርኛ አቀላጥፎ ይናገራል ወይም የአፍ መፍቻ ቋንቋዉ ነዉ፡፡ 2.5 ሚሊየን አማራ በደቡብ በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖር ጉራገኛ፤ሲዳመኛ፤ወላይተኛ፤ጋሞኛ አቀላጥፎ ይናገራል እንደየሚኖርበት አካባቢ፡፡ በድሬዳዋ፤ጅጅጋና ቀብሪዳህር የሚኖሩ ከ1 ሚሊየን በላይ አማራወች ሶማለኛ ወይ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸዉ ነዉ አለበለዚያ አቀላጥፈዉ ይናገራሉ፡፡ ከ20 ሺህ በላይ አማራ ሀደረኛ አቀላጥፎ ይናገራል፡፡ ግማሽ ሚሊየን ገደማ የመተከል አማራ ሽናሸኛ ጉሙዝ አቀላጥፎ ናገራል፡፡ እሰከ ሩብ ሚሊየን የሚደርስ አማራ አፋረኛ ወይ የመጀመሪያ ቋንቋዉ ነዉ አለበለዚያ አቀላጥፎ ይናገራል፡፡ እሱ ብቻ አይደለም አማራ ክልል ተብሎ በተካለለዉ ዉስጥ እንኳን ከ 1.5 ሚሊየን በላይ የሚሆን አማራ ኦሮሞኛ አቀላጥፎ ይናገራል፤ከ 1.5 ሚሊየን በላይ የሚሆን አማራ ትግርኛ አቀላጥፎ ይናገራል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የአማራ ህዝብ ሃብት የሆኑ በክልሉ ዉስጥ አንደ አገወኛ/ህምጥኛ፤ አርጎባ፤ ግእዝ፤ቅማንትኛ፤ ጋፋት የመሳሰሉ ቋንቋወች ከአማረኛ በተጨማሪ በዉስጡ አሉ፡፡ እነሱንም እናሳድጋቸዋለን በመጥፋት ላይ ያሉትንም እንመልሳቸዋለን፡፡ የአማራ ህዝብ ይሄ ነዉ፡፡ በየትኛዉ በኩል ነዉ አማራ ሌላ ቋንቋ እንዳይነገር የሚለዉ፡፡ እንዲሁ የተለመደዉ ቋንቋዉን ጭኖብን የሚል የዉሸት ፕሮፖጋንዳ ለመንዛትና እና የአማራ ህዝብ እየጠየቀ ያለዉን የፍትህና የእኩልነት ጥያቄ በዚህ ለማሸማቀቅ ነዉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦረና ላይ ሄዶ 10ሺህ ሰዉ ሰብስቦ በአማራኛ ቢያወራ ምናልባትም 5 ወይም 10 ሰወች ሊሰሙት ይችላሉ፡፡ አዲግራት ሄዶ በአማረኛ ቢያወራ 5 ወይም 10 ሰወች ሊሰሙት ይችላሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ባህርዳር ወይም ጎንደር ወይም ደሴ፤ደብረማርቆስ ደብረብርሃን ወይም አዲ አባባ ላይ 10ሺህ ሰዉ ሰብስቦ በትግርኛ ቢያወራ በእርግጠኝነት ከ 4 ሺህ በላይ አማራ ይሰማዋል፤ በኦሮሞኛ ቢያወራ ከአምስት ሺህ በላይ አማራ ይሰማዋል፡፡ ሌላዉ ቀርቶ እንኳን ብአዴን ዉስጥ ያሉ እንደንጉሱ ጥላሁን አይነት አማራዎች  ኦሮሞኛ እና አማረኛ አቀላጥፎ የሚናገርሩ እንደምሳሌ መዉሰድ ይቻላል፡፡ የአማራን ህዝብ አማረኛ ብቻ እንደሚያዉቅና ለሌሎች ቋንቋወች Phobia እንዳለበት አድርጎ የሚስል ያዉ የተለመደዉ የዉሸት ትርክት ነዉ፡፡ የቋንቋ ፎቢያ ካለበት ብአዴን ነዉ ያለበት እሱም የእንግሊዝኛ ቋንቋ Phobia ነዉ፡፡  ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ እራሱን መግለጽ በሚችልበት ቋንቋ ቢናገር የአማራ ህዝብ ምንም ችግር የለበትም፡፡ የአንድነት ጎራዉ ነዉ የቋንቋን ጉዳይ ሲያቦካዉ የነበር፡፡ እና እኛ ምናአገባን፡፡ አንድነቱ ዉስጥ የእነ ለገሰ ዋቅጅራ ና የእነ ለታ ልጆች የእነ አርያና የእነ በርሄ ልጆች ነዉ ያሉበት፡፡ የአማራ የብሄርተኝነት ፖለቲካ ከዚህም በላይ እጅግ ጤነኛ እና ለሌለዉ ተምሳሌት ሊሆን የሚችል ነዉ፡፡ እንደደረሰብን በደል እማ ቢሆን ይሄኔ አብረን አልነበርንም፡፡
የአማራ ህዝብ ጥያቄወች የሚከተሉት ናቸዉ
• የማንነት(ወልቃይት፤ራያ፤መተከል) እንዲሁም አማራወች በያሉበት በቋንቋቸዉ የመጠቀም፤ባህላቸዉን የመሳደግና  የፖለቲካ ዉክልና የማግኘት
• የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ  ፍትሃዊ ተጠቃሚነት
• እኩል የፖለቲካ ተሳትፎ
• እኩል የሀገር ሀብት ክፍፍል
• ነጻነት፤ዲሞክራሲና የመብት መከበር
• ፍትህ ያለ አድሎ የማግኘት ናቸዉ
• የአማራ እራሱ በመረጣቸዉ ልጆቹ እንዲተዳደር ናቸዉ ጉልህ ጥያቄወች
ከዚህ ዉጪ ያለዉ ተራ ፕሮፖጋንዳ ይሄን ትልልቅና ወቅታዊ የአማራ ህዝብ ጥያቄ ለመሸፋፈን ነዉ፡፡ መስመር ሳንለቅ ና distract ሳንደረግ ጥያቂያችን በዚሁ መንገድ እናቀርባለን
የአማራ ህዝብ open society የምንለዉ አይነት ህዝብ ነዉ፡፡ የአስተሳሰብ፤የባህል፤የቋንቋ፤ የሃይማኖት ፤የአመለካከት፤ የጀነቲከስና የአዲዮሎጂ ብዝሃነት በጸጋ ተቀብሎ የሚኖር ህዝብ ነዉ፡፡ አማራን ከማኝኛዉም ማህበረሰብ ባላይ ወደፊት ተጠቃሚ እና በቀላሉ እራሱን እንዲለዉጥ የሚያድረገዉ ያለዉ የተፈጥሮ ሃብት ሳይሆን በእነዚህ ልዩነቶች የተገነባዉ የሰዉ ሀብቱ ነዉ፡፡ እኒህ ጤነኛ የአስተሳሰብ፤የባህልና የቋንቋ ብዝሃነት የቴክኖሎጅ ፍልስፍናን ይጨምራል (innovation)፤entrepreneur and pragmatic ማህበረሰብ እንዲኖር ያደርጋል፤ ብዙ ሳይንቲስቶች፤አስተማሪዎች፤መሪወችና የመብት ተሟጋቾች የሚወጣበት ማህበረሰብ ይሆናል፡፡ የአማራ ህዝብ future እጅግ አንጸባረቂ  በየትኛዉም የአለም ክፍል ያለ ማህበረሰብ ሊኖረዉ የማይችል ጸጋና ተስፋ  ከፊቱ ይጠብቀዋል፡፡ የአማራ ህዝብ አዋጅ አላወጣም ይሄን ቋንቋ እንዳትናገር ብሎ ወይም ታፔላ አልዘቀዘቀም፡፡ We embrace diversity. አብዛኘዉ የአማራ ህዝብ ከአማረኛ በተጨማሪ ሁለትና እና ሶስት ቋንቋ ይናገራል፡፡ማነዉ እና የቋንቋ Phobia ያለበት? ንገሩኝ ባይ ሁላ፡፡
Filed in: Amharic