>

" ግልፅና አጭር ደብዳቤ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ አብይ አህመድ

 ዲያስፖራ ኤርምያስ (የኔጌት ፍቅር)”
በመጀመርያ ደረጃ እንኳን ደስ አሎት ለዚህ እድል በመብቃቶ መልካም የትንሳኤበአልም እመኝሎታለሁ መቼም ውሀ ሽቅብ አይፈስም ! ይህንን ደብዳቤ ለእርሶ እዲደርስልኝ እየተመኘሁ:- ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ እርሶ ሲሾሙ ክርስቲያን ሙስሊሙ ካቶሊኩ እና ፕሮቴስታንቱ ሁሉም ከሊቅ እስከ ደቂቅ  በደስታ ተቀብሎታል እናም በሰው  ዘንድ መወደዶ እጅግ ሊያስደስቶት ይገባል ግን አንድ ነገር ልለምኖት እርሶ 3 ሴት ልጆች አሎት ከእርሶ የመጨረሻ ልጅ እኩያ የምትሆን እቦቀቅላ ህፃን እንባ እዲአብሱላት በአምሳያ  ልጆ ስም እለምኖታለሁ የኔ ልጅ ብትሆን ብለው እዲያስቡና እዲራሩላት ይች ልጅ የኢትዮጵያ ግማሽ አካል ናት እና ኢትዮጵያን ስታለቅስ ማየት እደማይፈልጉ ሁሉ የዝች ህፃን እንባንም ያብሱላት ዘንድ በትህትና እጠይቃለሁ የአባት ፍቅር ምን ያክል እደሆነ ልጆቾ ምስክር ናቸው! ላስታውሶት ወደ እምዬ ምንልሊክ ቤተመንግስት በገቡ ሰአት ልጆ ከእርሶ ስር ሙጥኝ ብላ ነበር ያደሞ ለምን እደሆነ ለእርሶ ግልፅ ነው ፍፍቅሮትን እንጂ አልጋ ወራሽ መሆን አምሯት አይደለም!! እባክዎ ስለልጆቾ ብለው አባቷን አንዳርጋቸው ፅጌን ይልቀቁላትና ይች ይፃን እዲሜዋን ሙሉ ትዉደዶት ነገ የሚሆነው አይታወቅምና አንድ ነገር  ላጫውቶት አንድ እስፓንሽ ትንሽ እህቱ ይርባታል እናም ምግብ ፍለጋ ይወጣል እድሜው ገና 8 አመት አልሞላውም ግን ለትንሽ እህቱ እራራ  እናም መሷእትነትን መርጦ አንድ የ 21 አመት ወጣት ሴት ምግብ ገዝታ ስትሄድ ያያል እናም በድንገት ቀብ አደረገው ምግቡን ግን ሊቀማት  አልቻለም ምክንያቱም አቅም አልነበረውምና  ታድያ ድንገት ባለሀብት ሲትደበድበው ያያል ነገሩን ለማጣራት ቀርቦ ይጠይቃቸዋል ልጅቱም ምግቤን ሊነጥቀኝ ነበር ይህ ችጋራም ብላ አሁንም ልትመታው ሰነዘረኝ  ግን ባለ ሀብቱ  ምንም ጥያቄ ሳያበዛ የገዛችበትን ገንዘብ ሰቶ ሸኛት ተጨማሪም የራሱን ልጅ  ምሳ ጨመረለት ህፃኑም ተቀብሎት እሮጠ  ለትንሽ እህቱ ሊደርስላት! ይህ ከሆነ ከእረጅም አመት ቦሀላ ያሀብታም ክፉኛ ታመመ ብዙ እክምና ከማድረጉ ብዛት ገንዘቡ ሁሉ አለቀ ዶክተሮቹም ካቅማችን በላይ ነው ብለው ወደሌላ ከፍተኛ ሆስፒታል ይልኩታል ከ አንድ ልጁጋ እክምናውን ተከታትሎ ዳነ ግን  ልጁ ተጨነቀች  ለእክምና የምትከፍለው ገንዘብ ስላልተሟላላት እንባዋን ጠራርጋ ስትመለስ አባቷ አልጋ ላይ  ተከፍሏል የሚል ደረሰኝ አገኘች በርሀቡ ግዜ የደረሰለት ሀብታምን አክሞ አድኖ ሂሳቡን የዘጋው ያ ህፃን ነበር ነገ እርሶና ይች ህፃን ምን እደሚገጥማችሁ አይታወቅም እና እባኮ ለእራሶ ሲሉ መልካም ይስሩ መልካም መሆን ለራስ ነው!!
ቀን 01/08/2010 የስራ ዘመኖን ፈጣሪ ይባርክ!
Filed in: Amharic