>
5:13 pm - Sunday April 19, 1789

ከዚህ በኋላ የህወሃት የበላይነት ዘመን አበቃ! (ጋዜጠኛ - ተመስጌን ደሳለኝ)

ህወሃት አምባገነን መሪዋ ከሞተ በኋላ አርጣለች። ከዚህ በኋላ ሽንፈቷን አምና መቀበል እንጅ መፈንራገጥ ትልቅ ዋጋ ያስከፍላታል። አሁን ሁለት አማራጮች አላት።
አንድ :- ሽንፈቷን አምና ተቀብላ ወደ ሽግግር መንግስት
መሄድ  (ይሄ ሲሆን በሰላም የመኖር ዕድል ይኖራታል)
ሁለት :- የህዝብን ድምፅ ለማፈን ሞክራ እንደ ጋዳፊ
እሬሳዋ አስፓልት ላይ መጎተት።
እሳት የሆነ ሞት የማይፈራ ትውልድ ተፈጥሯል። ነፃነቱን በሰላማዊ መንገድ ለማግኘት ሞክሮ በወታደር የሚገደል ከሆነ እና በሰላማዊ
መንገድ ተስፋ ከቆረጠ ከቀበሌ ሊቀመንበር ጀምሮ አንገትህን እየቆረጠ መብቱን የሚያስከክር ትውልድ ይፈጠራል። የእኛም ትግል እዚያ ጋ ሳይደርስ ለውጥ እንዲመጣ ነው።
ያ የማይሆን ከሆነ ግን የፈለገ ወታደር ቢኖርህ የህዝብን ትግል ማስቆም መቆጣጠር አትችልም። ዓለም ላይ የህዝብን ትግል ያሸነፈ አንባገነን አልታየም። የግዜ ጉዳይ እንጅ የትኛውም አንባገነን ተዋርዶ ይወድቃል።
 ከዚህ በኋላ የህወሃት የበላይነት ዘመን አበቃ። የጃጁ ሽማግሌዎች እየፎከሩ፣ እያስፈራሩ የሚኖሩበት ዘመን ላይመለስ አበቃ። በጃጀ አስተሳሰብ አዲሱን ትውልድ መግዛት አይቻልም።
Filed in: Amharic