>

"አብይ እዚህ መኾኔን፥ መታሰሬንም ያውቃል" (ታዬ ደንዴአ)

ሃብታሙ ምናለ 

አክቲቭስትና መምህር ስዩም ተሾመንና የኦሮሚያ ፍትህ ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ታዬ ደንደዓ ከወዳጆቼ ጋር ሰብሰብ ብለን በማዕከላዊ/ሙዚየም በተነገረን መሠረት/ ተገኝተን ስለ ጤንነታቸው ስላሉበት ሁኔታ፥ ስለኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ ኹሉቱም ጋር ካወጋን በኃላ ብዙ ደቂቃዎችን አቶ ታዬ ደንደዓ
*****ስለጠቅላይ ሚንስቴር ምርጫ ስንጠይቀው
“………..በመመረጡ ደስ ብሎኛል፥ ትልቅ እንደሚሰራም እምነቴ ነው…..
*****አንተ እዚህ መኾንህ ያውቃል? እና እንዴት ዝም ይላል?
“አብይ እዚህ መኾኔን፥ መታሰሬንም ያውቃል፥ ለምን ፈጣን ምላሽ አልሰጠም? ለምን አላስፈታኝም አልልም፥ ለመፈታት እኔም ተራ መጠበቅ አለብኝ፥ ብዙ ሰዎች ታስረዋል፥ እነሱንም እንደሚፈታ እርግጠኛ እሆናለሁ። እኔ 2 ወርም 3 ወርም ብታሰር ግድ የለኝም። ይሄ አያስጨንቀኝም፥ ዋናው ነገር ህዝቡ ለውጥ ይፈልጋል። ስለዚህ ህዝቡም አብይን መታገስ ግድ ይላል። አብይ ጥሩ ተናጋሪ ነው፥ አቅምም አለው፥ አንድ ቀን ሲናገር ብትሰማ የእሱን ንግግር ሰምተህ ማደር አትችልም። ለውጥ ማምጣት እንዳለብህ ስታብሰለስል እንድታድር ያደርጋል። እኔም ይሄ ነገር አጋጥሞኛል የተወሰነ ጊዜ ስብሰባ ላይ ሲናገር ሰምቼው ተፅእኖ ተፈጥሮብኛል።”
*****ብአዴን በአብይ ምርጫ ላይ ያለው አስተዋፅኦ እንዴት ታየዋለህ?
“እመኑኝ ኦሮሚያ መቼም ከአማራ ልጆች ተለይታ አትኖርም። አማራ ያለ ኦሮሞ፥ ኦሮሞም ያለ አማራ መኖር አይችልም። ይሄንንም በደንብ ከእዚህ በፊት በተለያየ መድረክ አሳይተናል። ይሄንንም በአብይ ምርጫ ላይ አሳይተዋል። ከእዚህ በፊት የተዘራብንን የኹለታችን የማራራቅ ተግባር በቅርብ ጊዜ አከርካሪውን ሰብረን አንድ እንደሆንን አሳይተናል። አብይን ቢመርጡ ቀድሞ ከተሠራው ሥራ አንፃር ምንም የተለየ ነገር አይደለም”
*****ስለገዱና ስለ ንጉሱ ጥላሁንስ ብአዴን ማንቃታቸው ለአብይ ጥሩ ሆነለት
ገዱ አንዳርጋቸው ጠንካራ፥ ንጉሱ ጥላሁንም ኹለቱም ጎበዝ ናቸው። ከስር ደግሞ ያሉ ወጣቶች ከምታስቡት በላይ ጎበዝ ናቸው። እድሉን ሲያገኙ ታዩታላችሁ። ገዱ ይሄን እንደሚሠራ አልጠራጠርም ነበር። ግባቸውን መተዋል።……… ብሏል።
በመኃል ስዩም ተሾመ አብሮን ን ከነበረው ጠያቂ ጋር #አይዳ ብለው በሽብር ስለተከሰሰች የመተማ ወጣት ሲያወሩ መኃል ላይ ቆሞ የሚጠብቀው ፖሊስ “#IDEA ማውራት አትችሉም!” ሲል “ስዩም ናና አውራልኛ፥ የማወራውን ምረጥልኛ” ብሎ ከፖሊሱ ጋር እሰጣ – ገባ ውስጥ የገቡ ሲኾን በመጨረሻም አይዳ እንጂ #IDEA አላለም። ቢልም ግን መብት አለው በማለት ሌሎችም ፖሊሶች በመኃል በመግባት ችግሩን ለመፍታት ሞክረዋል።

Filed in: Amharic