>

ከቂልንጦ ጨለማ ቤት ያሉ ጀግኖች ለህዝብ አስተላልፉልን ያሉት መልእክት

ዛሬ ማለትም 23/07/10 ዓ/ም ቂሊንጦ ማጎሪያ ቤት  መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጠኝ
አስቻለው አንጋው ተገኝ  የተባሉት የፖለቲካ ተከሳሾችን አገኘናቸው የሚገርም ሁኔታ ያሳዩን ጀግንነት፤ ልበ ሙሉነትና ፍፁም ኢትዮጵያዊነት እጅግ በጣም በሚገርም ሁኔታ ነው የገለፁልን ያሳለፉትን ችግርና መከራ ለመግለፅ ይህ ጊዜ ይፈጃል ካሳለፍነው በላይ ለመሞትም ዝግጁ ነን በማለት ባጭሩ መልሰውልን  ጊዜ ልንሰጠውና ቀጣይ ልናተኩርበት ወደሚገባው ጉዳይና ለኢትዮጵያ ህዝብ እንድናስተላልፍላቸው የነገሩን በተለይ ከመቶ አለቃ ማስረሻ ጋር ሰፊ ሰአት ለመነጋገር እድሉ ስለገጠመኝ ቃል በቃል ያለኝን እንደሚከተለው ነው፤
1. እኛ ወደዚህ ትግል የገባነው በግብተኝነት ተነሳስተን ሳይሆን አስበንበት መክረንበት መከፈል ያለበትን ዋጋ ሁሉ ለመክፈል ተዘጋጅተን ነው፡፡
2. እኛ ከዚህ እየከፈልን ያለው ዋጋ ለብዙሃኑ ህዝብ ሳይማር ላስተማረን ጭቁን ማህበረስብ ነው እኛ ሙተንም ቢሆን ለቀጣይ ትውልድ ያ የምንጠብቀው ያለዘር ሁሉም በኢትዮጵያዊነቱ እኩል የሚታይበትን ቀን እንዲመጣ ለማድረግ ነው፡፡
3. እየሄድንበት ማለትም እየከፈልን ያለው ዋጋ በተጠና መልኩና በተደራጀ  አግባብ ግብ እስከሚደርስ ድረስ ነው፡፡ ስለሆነም  ሂደቱንም እያየነው ስለሆነ ደስተኛ ነኝ፡፡
4. ኢትዮጵያ ድሮም ብዙ ተከፍሎባት ነው ከዚህ የደረሰችው  አሁንም ለኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ዋጋ ማለት ከሀገር ውስጥም ሆነ ውጭ ወገኖች ሁኔታው ሳይገድባቸው እየከፈሉ ያሉ ብዙ ናቸው፡፡ እኛም ይህን ነው እያደረግን ያለው፡፡
5. እኔ በግሌ ሁሉን አይቸዋለሁ ትምህርቱንም፤ ብሩንም ክብሩንም ስራውን ማለትም ጀት እስከማብረር ድረስ ሁሉን አይቸዋለሁ ግን ውሳኔዬ የማንነት ጥያቄ ነው፡፡ ለምን ቢባል በዘር የተከፋፈለው ስርአት እየተንስራፋ በጀግኖች ደም ተከብራ የቆየችውን ኢትዮጵያ ሲያፈራርሳት ስላየሁና ክብር ያለ እናት ሃገር ባዶ መሆኑን ተረድቸ ይህን በማንነቴ ላይ የመጣ ስርአትን ለመታግል ተገድጃለሁ፡፡
6. ሙህራን በከፍተኛ ሁኔታ ለትግሉ ተሳታፊ መሆን አለባቸው
7. በውሳኔዬ እጅግ ደስተኛ ነኝ አንድም የሚቆጨኝ ነገር የለም
8. በየትኛውም አለም የተደረገው ትግል ውጤት የሚኖረው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የተደራጀ ህዝብ ሲኖር ነው ስለዚህ በተገኘው አጋጣሚ ሰው መደራጀት አለበት፡፡ አሁን ላይ የምናየው የሀገሬ ህዝብ ወደ አንድ መምጣት እጅግ በጣም የሚያኮራ ነው ደስ ብሎናል፡፡
9. የኢትዮጵያ ህዝቦች በሃገራችሁና በወገናችሁ ላይ እየደረሰ ያለውን ሶቆቃ በጋራ ቁመን ተጨንቀን መክረን መፍትሄ ልንፈልግ ይገባል፡፡ ለምሳሌ በአሁኑ ሰአት ብዙ ያአማራ ልጆች በዘራቸው ብቻ የሀሰት ክስ ተመስርቶባቸው በሰቆቃው ማጎሪያ ቤት እንገኛለን ስለሆነም ስለ ሙሉ ኢትዮጵያ ለማውራት በአማራ ዘር ላይ ወያኔ እያደረሰ ያለውን ጥላቻና ግፍ በጋራ መታገል ስንችል ነው፡፡
Filed in: Amharic