>
5:13 pm - Sunday April 19, 1925

የኢትዮ ቴሌኮም ንብረቶች "በጨረታ ሽያጭ" ስም ወደ ትግራይ እየተጓዙ ነው!?! (ሀይሌ ባንቴ)

 አዲስ አበባ እና የተለያዩ ቦታዎችን ለቀው የሚሄዱ የትግራይ ተወላጆች ቁጥር ጨመረ። 
የወያኔ አገዛዝ ከእንግዲህ በኋላ የትግራይ ተወላጆችን የበላይነት ማረጋገጥ የማይችልበት ደረጃ ደርሷል የሚል ግንዛቤ እየተጠናከረ መሄዱን ተከትሎ ከወያኔ ጋር ቀጥተኛ እና ተዘዋዋሪ ጥቅም ያገኙ የነበሩ ብዛት ያላቸው የትግራይ ተወላጆች መሬት በርካሽ ዋጋ እየሸጡ እና ንብረቶቻቸውን በውክልና እያስያዙ ከሀገር በመልቀቅ ላይ ናቸው
ከዚህ ጋር ተያይዞም ወደ ውጭ ሀገር የሚሸሸው የገንዘብ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረ ሲሆን ወደተለያዩ ሀገራት ከቤተሰቦቻቸው ጋር እየወጡ ያሉ የትግራይ ተወላጆች ቁጥርም በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል
በሌላ በኩል አዲስ አበባ ሀያ ሁለት መገናኛ እና ተክለሀይማኖት ሰፈሮች አካባቢ የሚኖሩ የቀድሞ የወያኔ ታጋይ ወታደሮች እስከ ስርአቱ የመጨረሻ ደቂቃ ድረስ ባሉበር ለመቆየት እና ስርአቱን እስከመጨረሻው ለመከላከል ወስነዋል የሚሉ መረጃዎች እየወጡ ነው
አዲስ አበባ ሀያ ሁለት መገናኛ እና ተክለሀይማኖት ሰፈሮች አካባቢ ወደ ሀምሳ ሺህ የሚጠጉ የታጠቁ የቀድሞ የወያኔ ወታደሮች እንደሚኖሩ የሚያሳዩ መረጃዎች አሉ።
የኢትዮ ቴሌኮም ንብረቶች በጨረታ ተሽጠው ወደ ትግራይ እየተጏዙ ነው
በሀገሪቱ ውስጥ የተፈጠረውን የፖለቲካ ቀውስ ተከትሎ የመንግስት መስሪያ ቤቶች “የተረፈ ምርት ማስወገድ” በሚል የሽያጭ ዘመቻ የመንግስት እና የህዝብ ሀብትና ንብረትን በ”ጨረታ ሽያጭ” ሽፋን ወደ ትግራይ እየተሸጋገሩ ነው
ከፍተኛ የመንግስት በጀት ተመድቦላቸው ትላልቅ የእቃ ግዥ ከሚያከናውኑ መስሪያ ቤቶች አንዱ የሆነው ኢትዮ ቴሌኮም “የቋሚ ንብረቶች አላቂ እቃዎች ቁርጥራጭ ብረታብረቶች እንዲሁም የማሸጊያ እቃዎች እና የተረፈ ምርቶች ማስወገድ” በሚል ዘመቻ የኢትዮ ቴሌኮም ንብረት የሆኑ የተለያዩ እቃዎችን በጅምላ በመሸጥ ላይ ይገኛል
በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ዋጋ ያለቸው ንብረቶችም ለሜቴክ በ”ጨረታ” ተላልፈው ተሰጥተዋል ሜቴክም በ”ጨረታ የገዛቸውን” ንብረቶች ወደ ትግራይ እንዲያዘዋውር መመሪያ ተሰጥቶታል
የወያኔ እድሜ እያጠረ መምጣቱን ተከትሎ በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተመሳሳይ የ”አላስፈላጊ ንብረት ማስወገድ” ዘመቻ በስፋት ተጀምሯል ከነዚህም ውስጥ የ ኢትዮዽያ ኤሌክትሪክ ሀይል ሌላኛው መስሪያ ቤት ነው
የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ሽቦዎች ትራንስፎርመሮች ስማርት ሜትሮች እና የኤሌክትሪክ ሽቦ ተሸካሚ ምሰሶዎች “አላስፈላጊ ንብረት ማስወገድ” በሚል ሰበብ በዘመቻ እና በ”ጨረታ” ለሜቴክ ተላልፈው እየተሰጡ እና ወደ ትግራይ እየተላኩ ነው።
Filed in: Amharic