>

የኤሌክትሪክ ሃይል ኢ -ፍትሃዊነትና የአማራ ህዝብ (ሚኪ አማራ)

 አይደለም ለፋብሪካ መገንቢያ መብራት ለአማራ ክልል ሊሰጥ፡ ነዋሪዉ እንኳን ወፍጮ አስፈጭቶ ሊበላበት የሚችል መብራት ሊያገኝ አልቻለም፡፡ 
በተቃራኒዉ ትግራይ ዉስጥ 167 መካከለኛና ከፍተኛ ፍብሪካዎች እንደፈለጉ ክፍያ እንኳን ሳይከፍሉ መብራት 24 ሰአት ያገኛሉ ምርትም ያለማቋረጥ ያመርታሉ፡፡ የአማራ ህዝብ የመብራት ችግርን እንደሚከተለዉ አስቃኛችዋለዉ፡፡
ይሄ ሪፖርት የክልሉ መንግስት እጅ ላይም አለ፡፡ በነገራችን ላይ የአማራ ህዝብ ብዙ ልናወራለት የሚገባ ችግር አለ፡፡ አንዳንድ በየጊዜዉ ብቅ እያሉ destruct ለማድረግ የሚፈልጉ ሰወች ሌላ ጊዜ እንመለስባቸዋለን፡፡ ጊዜ ስናገኝና ስራ ስናጣ፡፡ ከ 40 አመት በፊት ጡረታ ከወጣዉ ጋር ሁሉ ለመነታረክ ጊዜ የለንም፡፡
በባለፉት ሁለት ምርጫዎች መብራት ሊገባላችሁ ተብለዉ ፖል ቆሞ ገመድ ተዘርግቶ ንብረቱ ከጥቅም ዉጪ ሆነዉ የቀሩትን የተወሰኑትን
1. አማራ ክልል፡ ሰሃላ ሰየምት ወረዳ ከ 7 አመት በፊት የመብራት ፖል ተክለዉ የምሰሶ እንጨቱም እያረጀ የወደቀ
2.  አማራ ክልል፡ ባንጃ ወረዳ ጉበላ አካባቢ ፖል ከተተከለ 6 አመት የሞላዉ ፖሎችም ስራ ሳይሰሩ አርጅተዉ ወዳድቀዋል
3. አማራ ክልል፡ ከጎንደር ላይ አርማጭሆ ወደ ሮቢት የሚሄድ የገጠር ከተሞች ፖል ከተተከለ 11 አመት የሆነ
4.  አማራ ክልል፡ ደጀን አካባቢ ያሉ ቀበሌዎች የመብራት እንጨት ተተክሎ እየበሰበሰ ካለ 11 አመቱ
5. አማራ ክልል ፡ ከደሴ ተነስቶ በዙሪያዉ ላሉ የገጠር ከተሞች ፖል ከተዘረጋላቸዉ 5 አመቱ
6. አማራ ክልል፡፡ ከደብረታቦር ወደ ፋርጣ ቀበሌዎች ፖል ከተተከለ 6 አመት ያለፈዉ
7. አማራ ክልል፡ ደቡብ ጎንደር ደራ ወረዳ ከአንበሳሜ ከተማ -ሰኔማርያም ቀበሌ እና ጎሃ ቀበሌ እንዲሁም ደወል ቀበሌ መጀመሪያ የተተከለው ፖል ኤሌክትሪክ ሳይለቀቅበት በማርጀቱ ሁለተኛ ዙር አዲስ ፖል ተተክቶ እስካሁን የኤሌክትሪክ ሀይል ያልተለቀቀበት
8.  አማራ ክልል፡ ከ ከላላ አቤት ወሃ(ደቡብ ወሎ) ፖል ከተተከለ 4 አመት
9. አማራ ክልል፡ ሰሜን ሸዋ ካሉት ወረዳዎች ውስጥ አጣዬ/ኢፍራታ እና ግድም ወረዳ አላላ ይምለዋ ቀበሌ ከ7 አመት በፊት ፖል ተተክሎ የአካባቢው ሰው የመብራት ብር አዋጥቶ ለመንግስት ግቢ ካደረገ 7 አመት ሞላው።
10. አማራ ክልል፡ በጎንጅ ቆለላ ወረዳ የመብራት ፖልና ገመድ ከተዘረጋ ወደ 6 ዓመት ሁኖታል ሆኖም ግን መብራት የለዉም ፖሎቹ ወዳድቀው ከጥቅም ዉጪ ሆነዋል፡፡
11. አማራ ክልል፡ በሰሜን ሸዋ ዞን አንፆኪያ ገምዛ ወረዳ ሀርቡ ወልዴ ቀበሌ ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ ፖልና ገመድ ተዘርግቶ ነገር ግን አገልግሎት የማይሰጥ፡፡
12.  አማራ ክልል፡ ምስራቅ ጎጃም በጎንቻ ሲሶ ወረዳ ግንደወይን ከተማ የዛሬ 7 አመት የቆመዉ ፖልና ገመድ እንጅ መብራት ተለቆበት የማያዉቅ
13. አማራ ክልል፡ ደቡብ ጎንደር ደራ ወረዳ አካባቢ የተዘረጉ የኤሌክትሪክ ምሰሶወችና ገመዶች ያለጥቅም ተበላሽተዋል፡፡
14. አማራ ክልል፡ ደ/ጎንደር ከእስቴ ወደ ቆማ የተተከለው ፖል ምርጫ ሊደርስ ሲል እንቅስቃሴ ይጀምሩና ምርጫው ሲያልፍ ይተውታል 8 ዓመት ሞላው ፖሉም እየወደቀ ነው፡፡
 ጭራሽ መብራት የሚባል ገብቶላቸዉ የማያዉቁ ወረዳወች
1. ሰሜን ጎንደር ዞን
-በየዳ ወራዳ
-ጠለምት ወረዳ
-ምስራቅ በለሳ
-ምእራብ አርማጭሆ
-ላይ አርማጭሆ
-ጃናሞራ ወረዳ
2. ዋግህምራ ዞን
-ሰሃላ ሰየምት ወረዳ
3. አዊ ዞን
-ዚገም ወረዳ
መብራት ገብቶላቸዉ ከዛም እስከ ሁለትና ሶስት አመት በላይ የተቋረጠባቸዉ ወይም አንዴ ብቻ ብልጭ ብሎ በዛዉ የጠፋባቸዉ
1. ምእራብ ጎጃም ዞን- ቋሪት፤ደጋ ዳሞትና ሜጫ ወረዳ
2. ሰሜን ወሎ- የቡግና ወረዳ
3. ደቡብ ጎንደር-ታች ጋይንት
4. አዊ ዞን-አየሁ ጓጉሳ ወረዳ፤አንክሻ ወረዳ፤ጓንጓ
5. ምስራቅ ጎጃም- ይቦኝ ወረዳ (ድጓጺወን ዋና ከተማዉ)፤ እነሴና ሳር ምድር (መርጦ ለማሪያም ከተማ)፣ ሁለት አጅ አነሴ
6. ሰሜን ጎንደር-ምእራብ በለሳ፤ጭልጋ፤ ታች አርማጭሆ
የመብራት ማከፋፈያ sub-station ሊሰራላቸዉ ተብሎ ከ10 አመት በፊት ከአለም ባንክ እርዳታ ተደርጎላቸዉ ነገር ግን ገንዘቡ ተበልቶ ማከፋፈያዉም ሳይሰራላቸዉ የቀሩ፡፡ ይሄንም በባለፈዉ የአማራ ክልል መንግስት በቴሌቪዥን አቅርበዉት ነበር፡
1. ሰሜን ጎንደር- የሻዉራ ማከፋፈያ ጣቢያ
2. አዊ- የዳንግላ ማከፋፈያ ጣቢያ
3. ደቡብ ወሎ- የኮምቦልቻ ማከፋፈያ ጣቢያ
4. ምስራቅ ጎጃም- የደጀን ማከፋፈያ ጣቢያ
5. ሰሜን ወሎ- የወልዲያ ማከፋፈያ ጣቢያ
6. ምእራብ ጎጃም- የቡሬ ማከፋፈያ ጣቢያ
7. ሰሜን ጎንደር- የጭልጋ ማከፋፈያ ጣቢያ
8. ምእራብ ጎጃም-የፍኖተሰላም ማከፋፈያ ጣቢያ
ተጨማሪ አንዳንድ እዉነታዎች
-አንድ ማከፋፈያ ጣቢያ በአማራ ክልል ዉስጥ በአማካኝ ለ 10 ወረዳ ያገለግላል፡፡ለምሳሌ ደቡብ ወሎ የአቃስታ ማከፋፈያ ጣቢያ ለ 11 ወረዳ ያገለግላል፡፡ ለዛዉም ወፍጮ ለማስነሳት እንኳን የማይችል በ 66 ኪሎ ቮልት ተሸካሚ መስመር፡፡ ለዚህም ነዉ አብዛኛዉ ክልሉ ላይ መብራት በፈረቃ የሚሰጠዉ፡፡ አንድ ወረዳ መብራት እንዲያገኝ እስከ 2 ወር ፈረቃ ይጠብቃል፡፡ 10 ወረዳ እስከ 4 ሚሊየን ህዝብ ወይም የትግራይ ክልልን ህዝብ የሚክል ይሆናል ማለት ነዉ፡፡
-ህዝቡ ወፍጮ ለማስፈጨት ከአንድ ወረዳ መብራት አለበት ከተባለዉ ወረዳ እስከ ሶስት ቀን በመጓዝ አስፈጭተዉ ይመጣሉ፡፡
-ክልሉ ላይ ወደ 120ሺህ የሚሆን ህዝብ ገንዘብ ለትራስፎርመር፤ ኤሲ እና ቆጣሪ አዋጥቶ ለ9 አመት እየጠበቀ ይገኛል
-ክልሉ አንድ ከተማ ላይ አንድ ትራስፎመር ከተቃጠለ በአማካኝ ለመጠገን ወይም ለመቀየር 4 አመት ይፈጃል (የክልሉ መንግስት ሪፖርት ነዉ)
-ሱዳን ያለማቋረጥ 100 ሜጋ ዋት ሃይል ከኢትዮጵያ ለሱ ተብሎ ጎንደር አዘዞ ላይ በተሰራ የማከፋፈያ ጣቢያ አማካኝነት ያገኛል፡፡ ወያኔ አስከ በአመት 100 ሚሊየን ዶላር ይሰበስባል፡፡
-ለሱዳንና ለጅቡቲ የሚሸጠዉ 200 ሜጋ ዋት ሃይል አሁን አማራ ክልል ባለዉ እየተቆራረጠ በሚሰጠዉ መብራት መጠን ብንወስደዉ እስከ 6 ሚሊየን ህዝብ ይጠቅም ነበር፡፡
– በአሁኑ ሰአት 1/3ኛዉ የኤሊክትሪክ ሃይል አማራ ክልል ዉስጥ ይመረታል፡፡ ይሄን ኤሌክትሪክ ሃይል ለማምረት በመቶ ሺህ የሚቆጠር የአማራ ገበሬ መሬቱን ለግሷል፡፡ እያንዳንዱ ገበሬ ከበለስ ተነስቶ ወደ ትግራይና አዲ አባባ የሚወስደዉ ማስተላለፊያ መስመር መሬቱ ላይ ያለምንም ካሳ ተተክሎበታል፡፡
መልካም ቀን
ANDM CC officeANRS Communication Affairs OfficeSouth GondarCentral Gondar CommunicationN/Wollo Zone Communication Affairs Office Gedu Andargachew
Filed in: Amharic