>
5:13 pm - Monday April 19, 8128

የጠቅላዩ ምርጫ 1 (ደረጀ ገረፋ ቱሉ)

ኦህዲድ ከላይ እና ከታች እሳት እየነደደበት ስርዓቱን ተሸክሞ እዚህ አድርሶታል!!!
አቶ ፍቃዱ ተሰማ – የኦህዴድ ስራ አስፈጻሚ
የኢህአዴግ ምክር ቤት ትላንትናም ሆነ ከትላንት ወዲያ በጠቅላይ ሚንስትር ምርጫ ላይ በቀጥታ አልተወያየም።
እሮብ እለት ከሰዓት የምክር ቤት አባላት የኢህአዴግ ፅፈት ቤት  ስለ አባል ፖርቲዎች  ያቀረበውን ሪፖርት በግላቸው አንብበው ዶክመንቱን ይዞ መውጣት ስለማይቻል መልሰው አስረክበዋል።
ጠዋት ላይ በሪፖሪቱ ላይ ውይይት አካህደዋል።ሪፖርቱ ኦህዲድን ያለምህረት እንደሚተች ምንጮቼ ነግረውኛል። በዚሁ መሰረት በጠዋቱ ክፍለጊዜ በብዛት ሃሳብ ያቀረቡት ኦህዲዶች እንደነበሩ ሰምቻለሁ።
በኦህዲድ ላይ ከቀረቡት ትችቶች መካከል
1. ኦህዲድ ከኢህአዴግ ባህል እና አሰራር  ውጪ ስልጣን መውሰድ ይፈልጋል የሚለው አንዱ ሲሆን ዶር አለሙ የኢህአዴግ የስልጣን ሽግግር ባህሉ ምንድነው? ከዓለማችን የተለየ ነው እንዴ?
ከፓርቲያችን ጋር ተቀራራቢ ባህል ያለው የቻይና ኮሚንስት ፓርቲ መሪውን የሚያዘጋጀው 10 ዓመት ሲቀረው ነው።ኦህዲድ ወራት ሲቀሩት ጠቅላይ ሚንስትር የሚሆን ሰው ቢያዘጋጅ ምንድነው ስህተቱ? ኦህዲድ ጣሰ የተባለውስ የትኛውን የኢህአዴግ አሰራር እና ባህል ነው? በኔ እምነት ልክ እንደማንኛውም ዓለም ለወደፊቱም ፓርቲያችን ከዓለም ልምድ ወስዶ መሪው ስለቅ ብቻም ሳይሆን ቀደም ብሎ መሪ  ብያዘጋጅ ለሀገሪቷም ሆነ  ለኢህአዲግ በጣም  ጥሩ ነው።ኦህዲድም ይህንን በማድረጉ መበረታታት አለበት እንጂ መወቀስ የለበትም።
የኢንዱስትሪ ሚንስትር ዴታ የሆኑት ዶር አለሙ የኢህአዲግ አባል ድርጅቶች በምክር ቤቱ በእኩል 45 ሰው መወከላቸው ፊትሃዊ እንዳልሆነ እና  ሌሎች ነጥቦችን በመጨመር ሰፍ ሃሳብ እንደሰነዘሩ ምንጮቼ አክለው ገልፀውልኛል።
2. ሌላው በኦህዲድ ላይ የቀረበው ስርዓቱን አደጋ ላይ ለመጣል እየተንቀሳቀሰ ነው የሚል ትችት ነው።ለዚህ ደግሞ በዋናነት መልስ የሰጡት የኦህዲድ ስራ አስፈፃሚ አባል (ከ9 ሳይሆን ከ15ቱ አንዱ ናቸው።) የሆኑት አቶ ፍቃዱ ተሰማ ናቸው።አቶ ፍቃዱ ተሰማ ኦህዲድ ከላይ እና ከታች እሳት እየነደደበት ስርዓቱን ተሸክሞ እዚህ አድርሶታል።ኢህዲግ በሚያመጣቸው መዘዞች  አባሎቻችን ራቁታቸውን በህዝቡ  እየተገረፉ ስርዓቱን ብለን እየገፋን ነው ።ከዚህ በላይ ለዚህ ስርዓት ምን እናድርግለት ?
የኦሮሞ ህዝብ በሚሊዮኖች እየተፈናቀለ አሁንም ኢትዮጵያ ወይም ሞት እያለ እና የኢትዮጵያን  አንድነት አጠንክራችሁ ግፉበት እያለ ነው።ይህ ህዝብስ ከዚህ በላይ ለዚህ ሀገር እንዴት ታማኝ ይሁን በማለት እጅግ ሰፍ ሃሳብ አንስቷል።
ከሁለቱ በተጨማሪ አምባሳደር ደግፌ ቡላ እና የማዓድን ሚንስትሩ አቶ ሞቱማ መቃሳም ጥሩ ጥሩ ሃሳብ አንስተዋል።ይህ የጠዋቱን ክፍለ ጊዜ ውይይት  ብቻ የተመለከተ ነው።
ይህ ሃሳብ ዛሬ ጠዋት ዳንዔል ስለ ጠቅላይ ሚንስትር ምርጫ ባያቀርብ አይቀርብላችሁም ነበር።ሰለዚህ የኢህአዲግን ባህል በመጣስ ስላበረታታኝ ዳንዔል ብረሃኔን አመስግኑልኝ  ።
Filed in: Amharic