>

"ከደበደቡኝ ሰዎች መሀል የአሁኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለሰ አለም አንዱ ናቸው" - ሰይፉ አለሙ ተሰማ 

“ጉራጌ ሌብነት እንጂ ፖለቲካን የት ያውቃል እየተባልኩ ምራቅ እየተተፋብኝ ነበር ስደበደብ ነው የከረምኩት “
       “ከደበደቡኝ ሰዎች መሀል የአሁኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለሰ አለም አንዱ ናቸው” ሰይፉ አለሙ ተሰማ
(በጌታቸው ሽፈራው)
    የዛሬን የፍ/ቤት ውሎ ስፅፍ እያለቀስኩ ነው። በእርግጥ ዛሬን ብቻ ሳይሆን በተደጋጋሚ አልቅሻለሁ። ከማእከላዊ ጀምሮ እስከ ቂሊንጦ በነበረኝ የሁለት አመት ከሁለት ወር የእስር ቆይታ የበዙ ወንድሞቼን በማእከላዊ የደረሰባቸውን ስቃይ ማለትም የእግር ጥፍሮቻቸው የተነቀለባቸውን ብልታቸው የተኮላሸባቸውን በድብደባ ብዛት ሰውነታቸው ላይ የነበረውን ጠባሳ ስመለከት በሀዘን አለቅስ ነበር። ዛሬም በፍ/ቤት ተገኝቼ ሰይፉ አለሙ ተሰማ በማዕከላዊ የደረሰብኝ ነው ብሎ ልብሱን አውልቆ ሰውነቱን ሲያሳይ በአካላቱ ላይ ጉዳት እና ጠባሳ ሳይ በሀዘን አልቅሻለሁ ።
        መዝገቡ የሚጠራው በእነ ጌታሁን በየነ ሲሆን ለዛሬ የተቀጠረው ተከሳሽ ሰይፉ አለሙ የመከላከያ ምስክሮቹን ለማሰማት ነው ተከሳሽም የተከሳሽነት ቃሉን ሰጥቶል።
     *በማዕከላዊ ከመርማሪዎች ጋር ሳይሆን ጥቃትን ከሚያደርሱ አካላት ጋር ነበርኩ።
     * እኔ የተያዝኩት አርባምንጭ ሆቴል ውስጥ ነው የያዘኝም ደህንነት ነው ይዞም ማዕከላዊ የሚባል ሲኦል ውስጥ ነው የከተተኝ የተረከበኝም ኮማንደር ተክላይ ነው
      *ይደበድቡኝ የነበሩት በጣም ብዙ ናቸው ሴቶችም አሉበት ከኮማንደር ተክላይ ጋር ሰክረው ነበር የሚደበድቡኝ
       *ከሚደበድቡኝ ሰዎች መሀከል የአሁኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ መለሰ አለም አንዱ ነበር
      *በማዕከላዊ ጥቃት ይደርስብኝ የነበረው በቤሄሬ ነው ጉራጌ ሌብነት እንጂ ፖለቲካን የት ያውቃል እየተባልኩ ምራቅ እየተተፋብኝ ነበር ስደበደብ የነበረው
      *ከዚህ በፊትም ማዕከላዊ ተይዘው የገቡ ብዙ ጉራጌዎች ተደብድበዎል ተኮላሽተዎል በዚህ ቤሄር ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት ሊቆም ይገባል
     *ሰውነቴ ላይ የሚታዩት እነዚህ ጠባሳዎች ከእናቴ ማህፀን ስወለድ ያገኘሆቸው ሳይሆኑ በማዕከላዊ በደረሰብኝ ድብደባ ምክንያት ሰውነቴ ላይ የቀሩ ናቸው
     *ይሄ ሁሉ ድብደባ ደርሶብኝ ሰውነቴም መግሎብኝ ህክምና እንኮን አለገኘሁም ነበር
     *በጊዜው አብረውኝ የነበሩ እስረኞች ህክምና ያግኝ ብለው የረሀብ አድማ አድርገው ነበር ሀላፊዎቹም ህክምና ይደረግለተል ብለው ቃል ከገቡ በሆላ እኔን ጠርተው አንተን አናክምህም ብለው ማስታገሻ ብቻ ሰተውኛል
       *ስደበደብ የነበረውም የግንቦት ሰባት አመራር ነህ ተብዬ ነው
      ሲል የተከሳሽነት ቃሉን የሰጠ ሲሆን ሶስተ የመከላከያ ምስክሮች አቅርቦ አሰምቶል
       *ምስክሮቹም በወቅቱ መዕከላዊ አብረው መታሰራቸውን ገልፀው ሰይፉ አለሙ ላይ ይደርስ የነበረውን ሰቃይ በድብደባ ምክንያት ሰውነቱ ላይ ይታዩ የነበሩ ቁስሎችን እና የህክምና እርዳታ እንዲያገኝ የረሀብ አድማ ማድረጋቸውን ገልፀው ለፍ/ቤቱ አስረድተዎል
      ፍ/ቤቱም በመከላከያ ምስክሮች ላይ ብይን ለመስጠት ለሚያዚያ 16/2010 ዓ.ም ቀጠሮ ሰቶል
—‘-””””
Filed in: Amharic