>

ለትግራይ ህዝብ - የናንተዎቹ ታጋዮች ለእናንተ እንኳን የማይራሩ የእርግማን ውጤቶች ናቸው

(በርታ ወገኔ የ ‘ብእር ስም’)
የናንተዎቹ ታጋዩች: ቀን እየቆጠሩ ስለ ሃውዜን እልቂት የአዞ እንባ የሚተናነቃቸው በሚመስል ሁኔታ እያላዘኑ ሲተረተሩ ብሰማ ይችን መልእክት ፃፍኩ:: ባይዋጥላችውም እውነት ናትና እየመረራችው በትግስት እንድታነቧት ተማፅንኳችው::
እንደሚታወቀው ቀድሞ ማህበረ ገስገቲ ትግራይ በኃላ የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር ከተመሰረተ አሁን 43ኛ አመቱን አክብሯል:: ድርጅቱ በአረቦች እና በጣሊያኖች እጅን ተጠምዞ እስከተቀየረበት ጊዜ አንስቶ የነበረው አላማ በትግራይ በተደጋጋሚ እየተከሰተ የነበረውን የተፈጥሮ ድርቅ እና በወቅቱ የነበረውን አስተዳደራዊ በደል ለመለወጥ ተብሎ የተጀመረ ትግል እንደሆነ ግልፅ ነው:: አስተዳደራዊ በደሉ በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎችም ስለነበረና የተሻለች ኢትዮጵያን ማየት የሚፈልጉ ወጣት ምሁራን በመበራከታቸው የለውጥ ትግሉ በሁሉም የህብረተሰቡ ክፍሎች እንደነበር ታሪክ ዘግቦታል:: በተለይ በወጣት ምሁራን ዘንድ እጅግ ተቀባይነት አግኝቶ የነበረው ኢህአፓ እና በውጭ ሀገርና በሀገር ውስጥ የነበሩትን ኢትዮጵያውያን አስተባብሮ ይንቀሳቀስ የነበረው መኢሶን በህብረተሰቡ እያቆጠቆጡ የነበረበት ወቅት እንደነበር አይረሳም:: በመካከል ግን ታሪክ ተቀየረ ሳይታሰ ብዙ ጊዜ ተብሎ ተብሎ ያልተሳካው መፈንቅለ መንግስት በ1966ቱ እውን ሆኖ ንጉሱም ከስልጣናቸው ወርደው ወታደሩም ራሱን ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግስት ብሎ በመሰየም ስልጣን ላይ መጣ:: የደርግ ስልጣን ላይ መውጣት ነገሮችን ከማባባስ በቀር እምብዛም የቀየረው ነገር አልነበረም:: የጊዜያዊ ወታደራዊው
ስልጣን በህዝባዊ መንግስትም የመተካት እድሉ የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ:: በዚህ ምክንያት ወያኔን ጨምሮ በየስርቻው ተጅምረው የነበረ ድርጅቶች ደርግን ለመጣል ይፍጨረጨሩ ጅመር::
ወያኔን ከበርሃ አንስቶ ድጋፍ እያደረገ ከፍተኛ የምክር አገልግሎት እየሰጠ ለዚ ያበቃው አንድ አካል አለ:: በተለይ ህውሃት ትግራይን ከደርግ ነፃ ካወጣ በኃላ በርካታ የትግሬ ታጋዬች ተከዜን ተሻግረው ትግሉን መቀጠል አልፈለጉም ነበር:: በወቅቱ የሶሻሊስት ስርዓተ ማህበርን አሜሪካዎች እያሳደዱ በማጥፋት ደረጃ ላይ ስለነበር እና በተለይ በሶቬት ህብረት እርዳታ ተሰርቶ የነበረውን የአምቦ ጥይት ፉብሪካን ላማውደም ብሎም ለሚሳየል ማምረቻ ተሰብስቦ የነበረውን ዪራንየም ለመዝረፍ አሜሪካ በስለላ መረቧ በኩል እያደባች ነበር:: ህውሃት በ1980 ሙሉ ትግራይን ማለትም ከተከዜ በመለስ ከደርግ ነፃ አውጥቶ ነበር:: በርካታ የወያኔ ታጋዮችን ጦርነቱ አለቀ አገራችን ነፃ አወጣን ብለው ደስታቸውን ገለፅ:: ነገርግን ከበስተጅርባ የተደበቀው አካል አላማውን ስላላሳካ ጦርነቱ አዲስ አበባ የሚደርስበትን አዲስ ሴራ ሸረበ::
ይህን ለማድረግ ደግሞ የህውሃት ታጋዮችን ደርግ ጨርሶ ካልወደቀ መጥቶ ሊያጠፋቸው እንደሚችል ማሳመን ነበር:: ትግሬን በሎጅክ ማሳመን እንደማይቻል አሜሪካኖች በደንብ ያወቁ ይመስለኛል ስለዚ አንድ እጅግ ዘግናኝ ድርጊት መፈፅም ነበር:: ለዚ ደግሞ የተመረጠችው ሀውዜን ነበረች:: የቤት ስራውን መለስ ዜናዊ ከሲአይኤ ጋር ያከናውናል:: በመጀመሪያ በርካታ የትግሬ ህዝብ የተሰበሰበበት ቦታ መምረጥ ለዚህም ገበያ ቦታ ተመረጠ:: ቀጣይ አለም አቀፍ ጋዜጠኞችን መጥራት እና ከሜራዎቻቸውን እስትራቴጅ ቦታዎች ላይ አስተካክለው እንዲጠብቁ ማድረግ:: ይህ የቤት ስራ በሲአይኤ በኩል በሚገባ ተጠናቀቀ:: ቀጣዩ የህውሃት በርካታ ታጋዮች በተለይም አመራሮች ወደ ገበያ ቦታው እንዲገቡ ማድረግ ይህን የሚያሳይ መረጃ ደግሞ ለደርግ ደህንነቶች አሳልፎ መስጠት ነበር ይህም በሚገባ ተከናወነ:: ቀጥሎ የሚሆነውን ትይንት መጠባበቅ ነበር:: በስአቱ እንደሚደርስ የሰርግ ታዳሚ የደርግ የጦር በራሪ ጅቶች በሰልፍ ከተፍ አሉ: አሳልፎ በተሰጣቸው መረጃ መሰረት የተሸከሙትን የቦንብ መአት ሀውዜን ላይ አራገፋት:: የአሜሪካ ሲአይኤ ጋዜጠኞች የጦርነት አክሽን ፊልም እንደሚቀርፅ በተመቻቸላቸው ምቹ ቦታዎች ሆነው ቀረፁት:: የተቆረጠ እጅ: የተለያየ ወገብ: የተቀላ አንገት…አልወጣ ያለች የምትጣጣር ነብስ… የደም ጎርፍ ወዘተ… ቀጣዩ የቤት ስራ ሁለት ነገሮች ናቸው:: አንደኛ ሲአይኤዎች የቀረፁትን ቪዲዮ በአለም የመገናኛ አውታሮች ማስተጋባት:: ደርግ በአለም እጅግ ዘግናኝ ጨካኝ እና አላስፈላጊ መንግስት እንደሆነ የአለም መንግስታት በመረጃው አምነው እንዲቀበሉት በማድረግ ሁሉም ድጋፋቸውን ለህውሃት እንዲያደርጉ ማድረግ:: ሁለተኛው የመለስ ነው ጦሩን መሰብሰብ እና ደርግን ካልጣልን የከፍ ችግር ይደርስብናል ብሎ ማሳመን እና ጉዞ ወደ አዲስ አበባ ማድረግ:: ሁለቱም ተዋናዮች የቤት ስራቸውን በሚገባ ሰሩ:: በሲአይኤ አማካሪነት ከሀውዜን አዲስ አበባ ተገባ:: መንግስቱ ሃይለማሪያምም በጠዋት ተነስተው የብላቴ መኮንኖችን ሊመርቁ ሲሄዱ የግል አውሮፕላን አብራሬያቸው በአየር ላይ እንዳለ በቀጥታ ኬንያ እንዲያመራ ተገደደ:: የኬንያን መሬት ሳይረግጦ በኢትዮጵያ የዜና አገልግሎት  መፈርጠጣቸው ተስተጋባ:: የኬንያ መንግስት ግራ ተጋባ ጏድ መንግሥቱም ኬንያ ሆነው ለወዳጃቸው ሙጋቤ ጥገኝነት ጠየቁ ይሁንታውንም ሲያገኙ ጉዞም ከኬንያ ዚምባቡየ አደረጉ::የሚገርመው አዲስ አበባ ከተገባ በኃላም የህውኃት ታጋዮች በቃ ደርግን ጥለናል ወደ ትግራይ እንመለስ እያሉ አስቸግረው ነበር:: በመካከል መለስን እና ኢሳያስን የሲአይኤው ህርማን ኮህን የወቅቱ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር  ለንደን ወስዷቸው ነበር ያኔ ነበር እንደ ቅርጫ ስጋ  ኤርትራን ለኢሳያስ ኢትዮጵያን ለመለስ ያከፋፈላቸው:: የአሰብ ወደብ ሴራ እዝች ላይ ነበር: ህርማን አሰብን መለስ ይውሰድ ነበር ያለው:: ኢሳያስም ተቀብሎት ነበር:: ነገርግን  መለስ ኢትዮጵያን መምራት ላይሳካልኝ ይችላል ብሎብአስቦ ስለነበር ከኢሳያስ ጋር ባለው ፍቅር የተነሳ አሰብን ኢትዮጵያን መምራት ካልቻልኩ በኃላ ትግራይን ስገነጥል የትግራይ ትሆናለች ብሎ አስቦ ይዞላት እንዲቆይ ተነጋግረው ነበር:: መቸም ሲያልቅ አያንር ነው:: እንግዲህ የናንተዎቹ ታጋዮች ለእናንተ እንኳን የማይራሩ የእርግማን ውጤቶች ናቸው የምንለው ለዚህ ነው::
Filed in: Amharic