>

ይግባኙን የቄሮ ችሎት ቢወስንበት (መስቀሉ አየለ)

ስዩም ተሾመ ታፍኗል።ሲያደባ የኖረው የትግራዩ ጀስታፖ  “ኮመንድ ፖስት” በሚል ጭንብል ስዩም ተሾመን በማፈን ስራውን አንድ ብሎ ሲጀምር  የት ድረስ ለመሄድ እንደተዘጋጀ  ማሳየቱ ነው። ስዩም ተሾመ እስከዛሬ ድረስ ሃሳቡን በድፍረት ሲያጋራን የኖረው የኦህዴድ ድጋፍ ስለነብረውም ጭምር መሆኑ ባይካድም ዛሬ ግን የእርሱ መታፈን ለኦህዴድ ክንድ መዛል መጀመር ምልክት ሊሆን ይችላል ወይ ብሎ ለመጠየቅ  ገና ማለዳ ነው።
በተደጋጋሚ እንደታየው የቄሮ ትልቁ ጥንካሬው አደርጋለሁ ያለውን ነገር ሁሉ ቃሉን ሳያዛንፍ ቀኒቱን ጠብቆ በተጨባጭ ተግባራዊ የሚያደርግ መሆኑ ነው።
በመሆኑም መሬት አንቀጥቅጥ የሆነ ማእበል በማስነሳት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞችን ለማስፈታት የቻለው የቄሮ ንቅናቄ በአንድ ስዩም ተሾመ ጉዳይ አረመኔዎቹን “ልክ ማስገባት!” ይሳነዋል ብዬ ለአፍታ አልገምትም። ይልቁንም  ስዩም ተሾመን ለአንድ ሰአት ማሰር ወያኔን በታማኝ አምላኪዎቹ ህይወትና ንብረት ሲመንዘር ምን ያህል ዋጋ  እንደሚያከፍለው ስሌቱን የሚደምርለት ሰው እስኪቸግረው በቶሎ ወደ አጸፋው መግባት ያስፈልጋል። ለምን ቢባል እርሱ በእጃቸው ላይ እስካለ ድረስ በእያንዳንዷ ደቂቃ የሚያወራርዱበት የበቀል በትር መኖሩ ብቻ አይደለም። የጸረ ወያኔው ትግል አንድ ላይ እንዲናበብ ብሎም በሰርጎ ገቦች አቅጣጫውን እንዳይስት በማድረግና ትግሉም በዚህ ደረጃ እንዲፋፋም የስዩም ተሾም አይነት ደፋርና ቪዢነሪ መንገድ አመላካች ሰው ፋይዳው ቀላል ስላልነበረም ጭምር ነው።ደግሞም ትግሉ ገና ከመሬት ከፍ ሳይል እንደርሱ አይነት መርሃ እውራን በዘመነ ከለባት ከትግሉ ላይ ታፍኖ መራቁ የኪሳራውን መጠን ወጣኒያኑ አይስቱትም።
የማኪያቬሊ ፕሪንሲፕል ማጥቃት መከላከል ነው የሚለውን የእግር ኳስ ቀመር ለሪቮሊዩሽን ሲጠቀምበት እንዲህ ይላል። ጠላትህን እገዛ ቤትህ ድረስ መጥቶ እንዲያጠቃህ እድል አት ስጠው፤ ይልቁንም እሳቱን ወደ እነርሱ መሃል ፈጥነህ ውሰደው እንጅ።
Filed in: Amharic