>

ኢትዮጵያ ሲባል ማን ዝም ይላል ሰምቶ (ግዛው ለገሰ)

ነገሮች በጣም እየተለዋወጡ ቢሆንም ህወሃት እየተሸንፈ መሆኑ፣ ኢትዮጵያዊነት እያሸነፈ መሆኑ አለተለወጠም።

ህወሃት በፖለቲካ፣ በትርካት፣ በስነልቦና ተሸንፏል። የቀረው ጦርና ፀጥታው ነው። የግዜ ጉዳይ ነው እንጂ እዚያም ይሸንፋል።
ለህወሃት የቀሩት ካርዶች ለአጭር ግዜ እየተንገዳገደ ሊጠቅሙት ይችላሉ፣ ግን ዋጋውን ለራሱም ለሌሎቻችንም ይጨምረዋል። የሚያሳዝነው ታሪክ መስራት እንችላለን የሚሉት የህወሃት አመራሮችና የትግራይ ምሁራን ከአድማስ ባሻገር ማየት አለመቻላቸው ነው። ዋግ ያስከፍላቸዋል።
ብአዴን ከስርመሰረቱ ባንዳ ነው፣ የአምራን ህዝብ አይወክልም ወክሎም አያውቅም። ብዙዎች ባለፉት ወራት ተስፋ ስንቀውበት ነበር። ግን በፓርላማ ማንነቱ በገሃድ አረጋገጠ። የወልድያ፣ የቆቦ፣ የመራስ ሃዘን ገና ትኩስ እንዳለ አጋዚ እንዲገል ድምፅ ሰጡ፣ የባሀርዳር፣ የጎንደር፣ የወልቃይት ህዝብ እሮሮ መፍትሄ ብአዴን የአጋዚን ጦር ነው አለ። ለእኔ ብአዴን (እንደድርጅትና አመራሩ) ህወሃት ነው፣ አንድም ሁለትም ናቸው።
አሁንም በቲም ለማ፣ በአቢይ ተስፋ አለኝ። መድረሻችን አንድ ላይሆን ይችላል፡ ግን ለውጥ አምጥተዋል፣ ትግሉን ፓርላም አግብተዋል፣ አድዋን በሚነሶታ ተቀባይ የጋራ ታሪክ መሆኑን አስረግጥዋል፣ ምንሊክን፣ ባልቻን፣ ጎበናን የጋር ጀግኖቻችን መሆናቸውን እስረግጠዋል፡፡
በትግል ካሳለፍኳቸው 40+ አመቶች ዛሬ ለድል የቀረብኩ መስሎ ይሰማኛል፣ የዛሬ አርባ፣ ሃምሳ አመት ኢትዮጵያዊንት የሙት ልጅ ነበር፣ የሚንከባከብለት፣ የሚዘምርለት፣ የሚተርክለት … አልነበረም – በደርግ ግዜም ጭምር። ነጻነትም እንደዚሁ። ዛሬ ተቀይሯል። ሁላችንም ኢትዮጵያ እያልን ነው፣ በመልኳ እየተከራከርን ቢሆንም።
እንኳን ሰማይ ላይ ባንዲራሽን አይቶ 
ኢትዮጵያ ሲባል ማን ዝም ይላል ሰምቶ
Filed in: Amharic