>

"ቲም ለማን መደገፍ ትክክል ነበር" (እስራኤል ስቦቃ)

ቲም ለማን መደገፋችን ምንም ስህተት አልነበረውም። አንዳንዶች ተሳስተን እንደነበረና ሂሳችንን እንድንውጥ እየጎተጎቱን ነው። #ቲም_ለማን መደገፋችን ለምን ስህተት እንዳልነበረ ላስረዳችሁ።

1. የለማ ቲም በራሱ ወይንም በኦፒዲኦ ወይንም በህወሃት መልካም ፍቃድ የተፈጠረ ሳይሆን የኦሮሞ ህዝብ ትግል የወለደው ቡድን ነው።
2. የለማ አስተዳደር ላለፉት 27 ዓመታት አይነኬ የነበሩትን የመሬትና የማእድን ዘረፋ ላይ የተሰማሩትን፣ በህገወጥ ንግድና ኮንትሮባንድ ላይ የተሰማሩትን፣ የህብረተሰቡን ጤና የሚያውኩ አሮጌና ምንም መከላከያ ያልተገጠመላቸው ፋብሪካዎችን ማስቆም ችለዋል።
3. አጥጋቢ ባይሆንም የወጣቱን የስራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ ተንቀሳቅሰዋል።
4. የክልሉ ህዝብ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ባአብዛኛው ጅምር ስራዎች ቢሆኑም ትልቅ መነቃቃትን በመፍጠር ሰዎች በራሳቸውም ጥረት ቢሆን ወደ አክሲዮንና መሰል የንግድ ስራዎች እንዲገቡ አበረታተዋል
5. ኦቦ ለማ አንዳንድ ተቋማትን ህዝባዊ አድርገዋል። በምሳሌነት የሚነሱት የክልሉ ሚዲያና የፖሊስ ተቋማት ናቸው።
6. ኦቦ ለማ ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች በተለይም ከአማራው ህዝብ ጋር ለመፍጠር ያሰቡት የአንድነትና የኣብሮነት መንፈስ እንዲሁም ትብብር በብዙ የሀገራችን ህዝቦች ተቀባይነትን አስገኝቶላቸዋል።
7. ከሁሉም በላይ #ኦቦ_ለማ በሚያደርጉዋቸው በአሸናፊነት ስነልቦና የተሞሉ ንግግሮች በተለይም የኦህዴድ አባላትና ደጋፊዎች ከተሸናፊነትና ለሌሎች ከመላላክና እንደ ፈጣሪ ከመመልከት ስነልቦና እንዲወጡ ረድቷቸዋል። በቀደም በፓርላማ የታየውም ይህው ነው። ጥቂት #ሆድ_አደር ድኩማኖች ህዝቡ ላይ ክህደት ቢፈጽሙም አብዛኛዎቹ የምክር ቤቱ የ #ኦህዴድ አባላት በአሸናፊነት ከህዝባቸው ጎን ቆመዋል። ደግሞም አሸንፈዋል። #ሌቦች ድምፅ ገልብጠው የወጁት አዋጅ የነርሱ ጉዳይ አይደለም።
እነዚህንና እዚህ ላይ ያልተጠቀሱትን የኦቦ ለማን እንቅስቃሴዎች ጨምሮ ያመጡዋቸውን ለውጦች ኣይቶ ድጋፍ መንፈግ አሊያም ምንም እንዳልሰሩ መናገር መብት ቢሆንም ግን ውሸታም እንዳያደርገን እሰጋለሁ። አሁን ግን #TeamLemma የሚባል ነገር በነበረው ጥንካሬና ቁርጠኝነት ስለመኖሩ እጠራጠራለሁ። #የሆዳሞችና #የአጎብዳጆች ቡድን ምናልባትም የለማን ቡድን ለማዳከም የተሰጠውን ተልእኮ #በአባዱላ በኩል እየተወጣ ይሆናል ብዬ እገምታለሁ። የለማ ቡድን የተከዳው በ #ብኣዴን ብቻ ሳይሆን በራሱም ሰዎች ጭምር ነው። እኛም የህዝቡ የተለያዩ አካላት እንዲህ ያሉ እድሎች ሲፈጠሩ ልንጠቀምበትና ልንንከባከበው ይገባ ነበር። ስለዚህ የለማን አስተዳደር የደገፍን ሰዎች ከህዝብ ጥቅም አንፃር አይተን እንጂ ከግል ጥቅም ተነሳስተን እንዳልሆነና መደገፋችንም ምንም ስህተት ስላልነበረበት ምንም እንደማይፀፅተን ለመግለፅ ያህል ነው።
#ኦሮሚያ
#ኢትዮጵያ
Filed in: Amharic