>

''ኣርከጻዲቅ የደረሰበት ጉዳት ከፍተኛ ቢሆንም በፍጥነት እያገገመ ነው።''ኣቶ ዳኛቸው ይልማ በቨርጂኒያ በመኪና ኣደጋ ካለቁት ወጣቶች መሃል የተረፈው ልጅ ኣባት

verina ሰሞኑን ጁን 6.2014 ሶስት ኢትዮጵያውያን ኣቤነዘር ቴዎድሮስ ዕድሜ 19 ዓለሙ ኣመሃ (25) ኣቤል ኣየለ (19)፤ በኣሜሪካ ቨርጂኒያ በመኪና ኣደጋ ህይወታቸውን ማጣታቸው ይታወቃል።የሶስቱን ወጣቶች ህይወት የቀጠፈው የመኪና ኣደጋ ውስጥ በህይወት የተረፈው ኣንድ ብቻ ነበር።ከግርጌ ፎቶውን የምትመለከቱት ወጣት ኣርከጻዲቅ ይልማ በኣሁኑ ሰዓት (Bistol Regional Medical Center ውስጥ ህክምናውን በመከታተል ላይ ይገኛል።

Ethioreference.com በኣሜሪካ ሃገር ቨርጂኒያ ነዋሪ የሆኑትና በህይወት ተርፎ ህክምና ላይ ከሚገኘው የ19 ዓመት ልጃቸው ኣርከጻዲቅ ይልማ  ወላጅ ኣባት ኣቶ ዳኛቸው ይልማ ጋር ኣጭር የስልክ ቆይታ ያደረግነው ልጃቸውን አያስታመሙበት ከሚገኙበት ቦታ ሆነው ነው።ኣቶ ዳኛቸው ይልማ ኣሁንም የማይክሮ ሊንክ ኮሌጅ መስራችና ባለ ከፍተኛ ድርሻ ሲሆኑ፤ የቀድሞው የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች ማህበር መስራችና የዜና ኣድማስ ኣሳታሚና ኣዘጋጅ እንደነበሩም ይታወቃል። ኣደጋው ከመድረሱ በፊት ወደየት ሲሄዱ እንደነበርና የልጃቸውና የጉዋደኞቹን ሁኔታ በኣጭሩ የገለጹልን እንዲህ ነበር።

” ሁሉም ወደ የመረጡበት ዩኒቨርስቲ ለጉብኝት እየሄዱ ነበር ኣደጋው የደረሰባቸው። የኣርከጻዲቅ ትምህርት ቤት Eastern Mennonite Universtiy ይባላል። የሚገኝውም ቨርጂኒያ ነው። ከሶስቱ ኣንደኛው ኣቤነዜር ቴዎድሮስ University of Virginaia (UVA) ውስጥ የመጀመሪያ ዓመት ትምህርቱን ጨርሶኣል። ሌሎቹ ኣቤልና ኣመሃ በመኪናው የተጉዋዙ ናቸው። ኣቤል NOVA ኮሌጅ ይማር ነበር። ኣመሃ ግን ከመቀሌ ዩኒቨርስቱ በኮምፒውተር ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪውን ኣግኝቶኣል በትርፍ ጊዘው እየሰራ ይማር ነበር። ኣርከጻዲቅ ዘንድሮ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ኣጠናቆ በሚመጣው የትምህርት ዘመን ዩኒቨርስቲ ለመግባት በዝግጅት ላይ ነው። ብቸኛውና ከኣደጋው የተረፈው እርሱ ነው።”

ኣቶ ዳኛቸው ይልማ ልጃቸው ኣርከጻዲቅ በኣደጋው የደረሰበት ጉዳይ ከፍተኛ ቢሆንም በፍጥነት እያገገመ መሆኑንና ህክምናውን በBistol Regional Medical Center  እየተከታተለ መሆኑን ገልጸውልናል። በኣደጋው ህይወታቸውን ካጡት  ኣቤነዘር ቴዎድሮስና የዓለሙ ኣመሃ ስርዓተ ቀብር ቅዳሜ፣ የሶስተኛው ኣቤል ደግሞ ዕሁድ መካሄዱን ለማወቅ ችለናል።

photo (25)

Filed in: Amharic