>
3:19 pm - Tuesday February 24, 3159

Archive: Amharic Subscribe to Amharic

‹‹ሥልጣንን መግራት!›› ( ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

  በአሰፋ ሃይሉ – የፕሮፌሰሩን ድንቅ ምክር ሁልጊዜም እናስታውስ – ትልልቅ ሰዎች የማይበቅሉበት ሃገር ትልቅ ሃገር ሊሆን አይችልም። ስለሥልጣን...

የጠገቡት "ሀጎሶች" በተራቡት "ሀጎሶች" እየተፈራሩቁ በአጥንት ያስቀሯት

ባለቤት አልባዋ የኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን (አቻምየለህ ታምሩ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከስድስቱ ጥንታዊ የኦርየንታል ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክሪስቲያናት ማለትም ከኮፕት (ግብጽ)፣ ህንድ፣ ሶርያ፣ አርመንና ኤርትራ አንዷ ናት። ኢትዮጵያ በመጽሐፍቅዱስ ከ፵ ጊዜ በላይ የተነሳች ሲሆን ከክርስትና በፊት የብሉይ ኪዳንን እምነትና ባህል ተቀብላ እግዚአብሔርን ታመልክ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። ይቺ ቤተ ክርስቲያን ቀለም በጥብጣ፣ ብራና ፍቃ፣ ብዕርቀርፃ፣ጉባኤ ዘርግታና ትምህርት አስፋፍታ ልጆቿን እያስተማረች፣ እውቀታቸውን እያተደላደለች፣ ለሕዝብና ለአገር የሚጠቅም በርካታ ስራ ሰርታለች። በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ረገድም ልጆቿን በዘርና በቋንቋሳትለይ፤ በመወለድና በቋንቋ ሳትመዝን ልጆቿን በብቃትና በችሎታ፤ በመክሊታቸውና እንደየ ጥበባብቸው መጠን እየመደበት ከተራ የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ እስከ ሊቀ ጳጳስ ስትሾም ኖሯለች። በዘመነ ወያኔ ግን ታፍራና ተከብራ የኖረችው ዘረኝነትን የምትጠየፈው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቤተክህነት ቤተክህደት ሆኖ ከፓትሪያርክ ጀምሮ እስከ ደብር አለቆች ድረስ ያለው መንፈሳዊ ሹመትበትግራይ ተወላጆች ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ ተደርጓል። ወያኔ አንድ የቀረው ነገር ቢኖር የቤተክርስቲያኒቷን ሃይማኖታዊ ቀኖናን መቀየር ብቻ ነው። ወያኔ በሥልጣን ላይ ከቆየ ይህንንም ከማድረግ የማይመለስ መሆኑንበእስልምና እምነት ላይ ተግባራዊ እያደረገ ካለው መገንዘብ ይቻላል። ልክ እንደ ክርስትናው ሁሉ ወያኔ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን (መጅሊስ) በራሱ ካድሬዎች ሞልቶት ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮታል። እስልምና ላይ ግን የሃይማኖት ተቋማትን ከመቆጣጠር አልፎበቀኖና ጉዳይ በመግባት የራሱን “ምርጥ እስልምና” እያስተዋወቀ ነው። ይህ ነገር ዛሬ በሙስሊሞች ላይ የመጣው ነገ በክርስቲያኖችም ላይ የሚመጣውን አመላካች ነው። ብዙ ሰው ኢሕአዴግ በሚባለው የማታለያ ጭምብል ውስጥ ስላለው የወያኔ የበላይነት እያወራ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስላለው የሲኖዶስ መከፈል እንጂ ስላለው የትግራይ የበላይነትየዘነጋነው ይመስላል። እንደሚታወቀው «አቡነ» ማቲያስ የሚባሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ በዜግነት አሜሪካዊ ናቸው። ለወትሮው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ከርስቲያንፓትሪያርኮች ከግብጽ አሌክሳንደሪያ ይሾሙ ነበር። በዚህ ዘመን ግን የኢትዮጵያ ገዳማትና አድባራት ብቁ ጳጳሳትን ማፍራት ያቆመች ይመስል የወያኔዋ ኢትዮጵያ ጳጳስ ከአሜሪካ አስመጥታ ፓትሪያርክ አድርጋለች። አቡነ ማቲያስ ሱዳን በነበሩበት ወቅት የመንገሻ ስዩም ቃል አቀባይና የኢዲዩ የፕሮፓጋንዳ ጋዜጠኛ ነበሩ። አሜሪካ ገብተው ማተባቸውን ቆርጠው አሜሪካዊነትን ከተቀበሉ በኋላ በሀገረ ኢየሩሳሌም የታሪካዊቷየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን «ሊቀ ጳጳስ» ሆነው ተሹመው «አጎታቸውን» ፓትሪያርክ ጳውሎስን እስከተኩበት ጊዜ ድረስ በነበራቸው የኢየሩሳሌም ቆይታቸው ሙስናን ተቋማዊ አድርገውት ነበር። አንዳንድሰዎች «በብዝሀነት» ሲመዘን «እየሩሳሌም ካለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር መቀሌ ያለው የአቡነ አረጋዊ ደብር ይሻላል፤ ቢያንስ የተወሰኑ የኢሮብ ሰዎች አሉበት» ሲሉ ጽፈው ነበር። የማቲያስ ጉድ ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም። ወያኔ ሻዕብያን ተከትሎ አዲስ አበባን በተቆጣጠረ ማግስት ሎስ አንጀለስ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ለሁለት ከፍለው የትግራይና የኢትዮጵያበሚባሉ ሁለት ቤተ ክርስቲያኖች እንዲፈጠሩ ያደረጉ የዛሬው የወያኔ ፓትሪያርክ «አቡነ» ማቲያስ ናቸው። ማቲያስ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ መንግሥት ነኝ ባዩ ነውረኛ ቡድን ወያኔ ያዘጋጀውን የወያኔ ምስረታ ድግስ ለመታደም የአመቱን የቁልቢ ገብርኤል የንግሥ በዓል ሳያከብሩ የቀሩ ብቸኛ የኢትዮጵያኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን «ፓትሪያርክ» ናቸው። የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው የሆኑት ተራ ምዕመናን ከሩቅ ቦታ ሳይቀር በመጓዝ የአመቱን ገብሬል ለማክበር ወደ ቁልቢ ሲተሙ እሳቸው ግን «ብርሀንከጨለማ ጋር ህብረት የለውምና ተለይ» የሚለውን «አባታዊ» ቡራኬ እና ቃለ ምዕዳን ተገኝተው ለምዕመኑ ይሰጣሉ ተብሎ ሲጠበቅ «አመንዝረው» በገብርዔል ፈንታ ከአቦይ ስር ሸራተን ዋሉ። ኢትዮጵያ ውስጥክርስትና ለመጀመሪያ ጊዜ የከበረው በተራ ምዕመን ደረጃ ብቻ ሳይሆን በአለማዊው መንግሥት በንግሥተ ነገሥታት ሕንደኬ አቃቤ ንዋይ ጭምር ነበር። በመንፈሳዊነት በከሰረችዋ በወያኔዋ ኢትዮጵያ ግን ክርስትናመርከስ የጀመረው ከላይ የቤተ ክርስቲያኗ ራስ ነን በሚሉ ሰዎች ሆነ! የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን በመንፈሳዊነት ያከሰሯት ሙሰኛ «አቡን»፤ የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ቤተ ትግሬ አድርገዋታል። ይህንን በሚመለከት «ብጹእ» እየተባሉ በሀይማኖት ካባየሰሩትንና እየሰሩ ያሉትን ወንጀል፣ ሙስናና ዘረኝነት፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ቤተ ክርስቲያን በማን ቁጥጥር ስር እንደዋለችና እየተካሄደ ያለውን ከፍተኛ የገንዘብ ብክነትና የዘረፋ ድርጊት በተጨባጭ ማስረጃዎችለማቅረብ እንሞክራለን። በቅድሚያ የምናቀርበው ማስረጃ ባለፈው ሰሞን የአዲስ አበባን ሀገረ ስብከትን በጠራራ ጸሀይ ዘርፈው እንዲነሱ የተወሰነባቸውን ሶስት የትግራይ ሌቦች በነማን እንደተኳቸው የሚያሳይ ዶሴ ነው። «አቡነ» ማቲያስበተለይ ጠርቀም ያለ አስራት በኩራት የሚሰበሰብበትን የአዲስ አበባን ሀገረ ስብከት የበላውና የጠገበው ዘመዳቸው ሄዶ የራበውና ሁሉ ብርቁ የሆነ ዘመዳቸው የሚተካበት የትግራይ ርስት አድርገውታል።ብጹዕነታቸው እየተባሉ የሚጠሩት ግን ተግባራቸው በተቃራኒው የሆነው ወያኔ በፓትሪያርክነት የሾማቸው የተከዘ ማዶ ሰው የቀድሞዎቹን የበሉና የጠገቡ ሶስት «ሀጎሶችን» ወደሌላ ቦታ አዛውረው በነሱ ቦታየተኳቸው አዲሶቹ የአዲስ አበባን ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት ሹመኞች የሆኑት ሶስቱ የራባቸውና ሁሉ ብርቁ «ሀጎሶች» 1ኛ፡ምህር ጎይቶች ያይሄ፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ፤ 2ኛ፡ መጋቢጥበብ ናሁ ሰናይ በለጠ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ ኃላፊና 3ኛ አቶ ገብረ ሕይዎት አስገዶም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሒሳብና በጀት ዋና ክልፍ ኃላፊ ናቸው። ልብ በሉ! ይህ በትግራይ ተወላጆች ብቻየተሞላው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መምሪያ ሀገረ ስብከቱ ባሉት የኃላፊነት የስራ መደቦች ሙሉ ነው። እንቀጥል። በአዲስ አበባ ውስጥ ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስትያናትና አድባራት በሶስት ደረጃዎች ይከፈላሉ። አንደኛ ደረጃ የሚባሉት አብያተ ክርስትያናት እጅግ ብዙ ገቢ የሚያስገኙና ገቢሊያስገኙ የሚችሉ ሱቆች፣ ትምህርት ቤት፣ የመቃብር ቦታ ወዘተ ያለባቸው አብያተ ክርስትያናት ናቸው። እነዚህም አብያተ ክርስትያናትና አድባራት ብዛታቸው ሀያ ነው። አራዳ ጊዮርጊስ፣ ቦሌ መድኃኔዓለም፣ ኡራኤል፣ልደታ ለማርያም፣ ቅድስት ሥላሴ፣ አማኑኤል፣ አዲሱ ሚካኤል፣ እንጦጦ ኪዳነ ምህረት፣ ቅድስት ማርያም፣ ወዘተ አንደኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ አብያተ ክርስትያናት ናቸው። በወያኔ ቤተ ክህነት ቋንቋ አንድ ሰው«ተሾመ» የሚባለው በነዚህ አድባራት ውስጥ ሲሾም ነው። እነዚህ አንደኛ ደረጃ በመባል የወያኔ ቤተ ክህነት የመደባቸው አድባራት ውስጥ ጸሐፊና አስተዳዳሪው ሆነው በአባ ማቲያስ የሚሾሙት ከዘጠ አምስት በመቶ በላይ የትግራይ ሰዎች ናቸው። እነዚህ አንደኛ ደረጃበመባል በሚታወቁት አብያተ ክርስትያናት በአባ ማቲያስ የሚሾሙት የትግራይ ሰዎች ሁሉም የድርጅት አባላት ናቸው። ይህ ማለት እነዚህ ሰዎች ሲሾሙ የአገዛዙ ይሁንታ አለበት ማለት ነው። እነዚህ በትግሬነታቸውተደራጅተው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን የወረሷት የትግራይ ሰዎች የቤተ ክርስቲያን ዘረፋ እጅግ የሚዘገንን ነው። እነዚህ ሰዎች ቤተ ክርስቲያኗን የሚዘርፏት በሚሊዮን በሚቆጠር ገንዘብ ነው።ዘራፊዎቹ የትግራይ ሹመኞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መብደር በወያኔ ፈቃድ የተቀመጡ ስለሆኑ ስለዝርፊያቸው አይከሰሱም። ቢከሰሱም ቅጣቱ በትንሹ ይዘርፉበት ከነበረው የበለጠወደሚዘረፍበት ቦታ መዘዋወር ነው። የወያኔ የቤ ተክርስቲያን አስተዳደር ሁለተኛ ደረጃ አድባራት ብሎ የሰየማቸው መለስተኛ ገቢ የሚገኝባቸውን ቤተ ክርስቲያንን ሲሆን እነዚህም ቦታ አስተዳዳሪና ጸሓፊ የሚመደቡት ከዘጠና በመቶ በላይ ከትግራይሰዎች ነው። ቅዱስ ማርቆስ፣ ቁስቄም፣ ገነተ ኢየሱስ፣ ቂርቆስ፣ ወዘተ በዚህ ደረጃ ከሚካተቱት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስትያናትና አድባራት መካከል ናቸው። በሶስተኛ ደረጃነት የተቀመጡት ደግሞ የአዲስ አበባ አድባራት ከተማው ራቅ ያሉና ራሳቸውን ለመቻል የሚቸገሩ አዳዲስና ነባር አብያተ ክርስትያናት ናቸው። በእነዚህ አድባራት ውስጥ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነውየሚሾሙት በአብዛኛው የሌሎች ብሔረሰብ አባላት ናቸው። ሆኖም ግን የነዚህ አድራባራትም ቢሆን የጸሀፊውና የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ ኃላፊ ቦታ በትግራይ ሰዎች የተያዘ ነው። ወረድ ብለን የምናቀርበው የዝርፊያ ዶሴ በማህበረ ለስብሐት ልደታ ማሪያም ቤተ ክርስቲያን አባ ማቲያስ የሾሟቸው ሁሉም የትግራይ ሰዎች የሆኑ ዘራፊዎች ቤተ ክርስቲያኗን የገፈፏትን በርካታ ሚሊዮን ብርየሚያሳይና በአባ ማቲያስ ቁጥጥር ስር ያለው ቤተ ክርስቲያን አምኖ ካሳተመው ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ላይ የተገኘ የውስጥ ማስረጃ ነው። ከታች ስማቸው የተጠቀሰው ስድስቱ የአባ ማቲያስ ሌቦች ከአንድ ቤተ ክርስቲያ ብቻ በአንድ ወቅት በርካታ ሚሊዮን ብሮችን ዘርፈዋል። ከዚህ ተነስተን «በአቡነ» ማቲያስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶቤተክርስቲያን ከአንድ ቤተ ክርስቲያን ይህንን ያህል ሚሊዮን ብር የሚሆን የቤተክርስቲያን ሀብት ከዘረፋ በአጠቃላይ ቤተክርስቲያኗን እንዴት ግጠው ጨርሰው በአጽሟ እንዳቆሟት መገመት አይከብድም። የሆነው ሆኖ በትግሬነታቸው ተቧድነው ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ራቁቷን ያስቀሯት የአባ ማቲያስ ሹሞች የሆኑት የትግራይ ሌቦች ከአንድ ቤተ ክርስቲያን ዘረፉት ተብሎ ክስ የቀረበባቸው ሰዎችስምና ዝርዝር እነሆ፤ 1. ወ/ሮ አብረኸት ተክሉ የደብሩ ገንዘብ ያዥ፤ 1,...

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ድንጋጌው ህገወጥነትና የፓርላማው ሀላፊነት (ከ”anonymous”)

ስዩም ተሾመ ባለፈው ሳምንት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንግጓል። መከላከያ ሚኒስትሩ እንደተናገሩት ከሆነ በህገ መንግስቱ የተጠበቁ...

“ክርስቲያኗ” አሜሪካ የውጭ ፖሊሲዋን በ“ደጉ ሳምራዊ” መርህ ቀርጻ አታውቅም (ፋሲል የኔዓለም)  

የአሜሪካ ማስጠንቀቂያ ወደ አሜሪካ ለመኮብለል የሚጣደፈውን ባለስልጣን ቁጥር ይጨመረዋል። ጌታቸው አሰፋ የባለስልጣናትን ጉዞ የሚያግድ ህግ ሊያወጣ...

የጠቅላይ ተጠቅላይ ጨዋታ (ኤርሚያስ ለገሰ)

ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቀጥሎ የኢትዬጲያን የፓለቲካ አየር የሞላው የሚቀጥለው ” ጠቅላይ/ ተጠቅላይ” ማን ይሆናል የሚለው ነው። ይህንን ጉዳይ ሰዎች...

የታምራት ላይኔ ነገር. . . (አቻምየለህ ታምሩ)

ታምራት ላይኔ የሚባለው የአማራ ሕዝብ ቀንደኛ ጠላት ወያኔ ችግር ውስጥ በገባ ቁጥር ከተደበቀበት እየወጣ ለጓዶቹ «በጎ» የሚለውን ምክሩን እየለገሰ...

ህዝቡ አሁን በአዋጁ ምክንያት የሚያጣው ዴሞክራሲያዊ መብት የለውም (አብርሀ ደስታ)

የኢህአዴግ መንግስት የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ አውጇል። በህገመንግሥቱ መሰረት አዋጁ በሚኒስትሮች ምክርቤት ይወጣል፤ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ይፀድቃል።...

ኃይለ ማርያም ደሳለኝና ሥልጣን (ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም)

  ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በፈቃዱ ከባለሥልጣንነት ተሰናበተ፤ ብዙ ሰዎች አስተያየታቸውን በቴሌቪዥን ሲገልጹ እንደሰማሁት ከጠቅላይ ሚኒስትርነት በፈቃዱ...