>

የታምራት ላይኔ ነገር. . . (አቻምየለህ ታምሩ)

ታምራት ላይኔ የሚባለው የአማራ ሕዝብ ቀንደኛ ጠላት ወያኔ ችግር ውስጥ በገባ ቁጥር ከተደበቀበት እየወጣ ለጓዶቹ «በጎ» የሚለውን ምክሩን እየለገሰ ይገኛል። ትናንትናና ዛሬ በSBS Amharic ከካሳሁን ሰቦቃ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ በአማራና በኦሮሞ መካከል ያለው ቅራኔ መፈታት አለበት ሲል ተናግሯል። ይህ ታምራት ላይኔ መፈታት አለበት የሚለው የአማራና የኦሮሞ ቅራኔ ተደርጎ የተፈጠረውን የፖለቲካ ሽልጦ ከፈጥሩት ጸረ ሕዝብ ነውረኞች መካከል ዋነኛው ታምራት ላይኔ ራሱ ነው። የፋሽስት ወያኔ ሎሌ ሆኖ አዲስ አበባ እንደገባ ወደ ሐረር በማቅናት «ሽርጥ ለባሽ ይሏችሁኋል…በሏቸው» እያለ ሕዝብን በጎሳ ሲከፋፍልና አማራን ሲያፋጅ የነበረው ታምራት ላይኔ ራሱ ነው።

ታምራት ላይኔ በግፈኛነት ዛሬ የሃይማኖት ካባ ካጠለቀ በኋላ ከሚከሳቸው ከፋሽስት ወያኔዎች የሚያንስ አይደለም። አዲስ አበባ ከመግባቱ በፊት የፋሽስት ወያኔ አማርኛ አስተርጓሚ ሆኖ በተለይም በወሎ ክፍለ ሃገር ይንቀሳቀስ በነበረበት ወቅት በንጹሀን ላይ እየፈረደ ሲያስረሽን የነበረ ታምራት ላይኔ ራሱ እንደነበር አቶ ተክለ ማርያም መንግሥቱ የሚባሉ የአይን እማኝ ባለፈው ጥቅምት ወር ከሲሳይ አጌና ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል። በንጹሃን ሕይወት ላይ እየፈረደ ሲያስረሽንና አማሮች በያሉበት እንዲጨፈጨፉ ሲያደርግ የነበረው ታምራት ልይኔ ጭንብል አቀይኖር ዛሬ ፓስተር ቢሆን ወንጀለኛነቱን ሊለውጠው አይችልም።

ታምራት ላይኔ አገርና መንግሥት ሲኖረን በግፍ ላስጨፈጨፋቸው አማሮች፣ በአገራቸው ውስጥ ስደተኛ እንዲሆኑ ላደረጋቸው ሚሊዮን የአማራ ተወላጆችና በአማራነታቸው ብቻ ተወንጅለው እስካሁን ድረስ መድረሻቸው ሳይታወቅ ጠፍተው ለቀሩት ምሁራንና አባቶቻችን ሕይወት ተጠያቂ እንዲሆን እጁ የኋሊት በመጫኛ ታስሮ እውነተኛ ችሎት ፊት ቀርቦ በአማራ ላይ ለፈጸመው ወንጀል ተጠያቁ እንዲሆኑ ከምናደርጋቸው ጸረ ሰዎች መካከል ግንባር ቀደሙ ነው።

ታምራት ላይኔ ባለፈው ሰሞንም ስለ ኤርትራ ተናግሮ ነበር። የማናውቀው መስሎት በኤርትራ መገንጠል አዛኝና ተቆርቋሪ ሆኖ ለመቅረብ ሞክሯል። የምንኖርበት መዋሸት ከባድ በሆነበት ዘመን ነውና ታምራት ላይኔ የወያኔ ባለስልጣን ሆኖ በነበረበት ወቅት ገና የሽግግር መንግሥት የሚባለው የወያኔ ቧልት ከመቋቋሙ በፊት ኤትራን እንደ አገር እውቅና የሰጠው ታምራት ላይኔ ራሱ ነው። ታምራት ላይኔ በሰጠው ቃለ መጠይቁት «There is a defacto provisional government in Eritrea» ሲል የኤርትራን ከኢትዮጵያ የተለየት አገር መሆን ለአለም እውቅና የሰጠው ለይስሙላ የተቋቋመው የሽግግር መንግሥት ገና ሳይመሰረትና ለታይታ የተካሄደው የኤርትራ ሕዝበ ውሳኔ ከነ ጭራሹ ሳይታሰብ ነበር። ታምራት ላይኔ ይህንን ቃለ መጠይቅ የሰጠበት ተንቀሳቃሽ ምስል ከታች ታትሟል።

https://www.facebook.com/achamyeleh.tamiru.3/videos/1739170726104869/

Filed in: Amharic