>

ብረትን መቀጥቀጥ እንደ ጋለ ነው (አቻምየለህ ታምሩ)

ጀግኖቻችን ከጠባቡ የፋሽስት ወያኔ የማሰቃያ ቤት ወጥታችሁ ሁላችን ወደታሰርንበት ሰፊው የኢትዮጵያ እስር ቤት በመቀላቀቃችሁ ደስ ብሎኛል። እንኳን እንደሁላችንም በእኩል አብራችሁ ለመታሰር ወደ ሰፊው እስር ቤት ለመቀላቀል አበቃችሁ! የጀግኖቹ ከጠባቡ ማሰቃያ ቤት ወደ ሰፊው እስር ቤት መለቀቅ የፋሽስት ወያኔን የግፍ አገዛዝ መልክ አይለውጠው።

አገር በንጹሐን እንጂ የግፍ ክብረ ወሰን በተቀዳጁ ወንጀለኞች እስከተገዘገዘች ድረስ በጠባብ ማሰቃያ በግፍ የታጎሩ ሰዎች ወደ ሰፊው እስር ቤት መለቀቅ የትግሉ ግብም፤ የመጨረሻ ድልም አይደለም። የአገራችን ሰው እንደሚለው ብረትን መቀጥቀጥ እንደ ጋለ ነው። በዚህ ወቅት መደረግ ያለበት የጎደለውን መሙላት፤ የላላውን ማጥበቅ፤ የተኙትን መቀስቅሰ፣ የነቁትን ይዞ ወደፊት መሮጥ እንጂ እየታሰርንለት ያለው አላማ የተፈታ ይመስል ትኩረታችን የጋለውን ብረት ከመቀጥቀት ክንዳችን መዛል የለበትም።

Filed in: Amharic