ገዢያችን አዴግ ለለውጥ ዝግጁ ያለመሆኑን ከሚያሳይበት መግገድ አንዱ በቅርቡ የምርጫ ቦርድ አድርጎ የሾማቸው ሰዎች ናቸው፡፡ በስታትሰቲክስ ፅ/ቤት መረጃ በተሳሳተ መንገድ በማቀናበር እድሜ ዘመናቸውን ገዢውን ፓርቲ ሲያገለገሉ የከረሙ ሴት፣ አሁን ደግሞ ገለልተኛ ሆነው ምርጫ ይመራሉ ብለን እንድናምን ይፈልጋሉ፡፡ እኚህ ሴት በእውነት ለመናገር ከየትም አገር በተለይ በቁጥር እንኳን እንዳንተማመን ያደረገን መስሪያ ቤት በፍፁም አድርባይነት ያገለገሉ ብቻ ሳይሆን ለዚህ ውለታቸው በአምባሳደርነት ሹመት ያገኙ ናቸው፡፡ ይህን ስናሰበው አዴግ ለመታረም ዝግጁ አይለም እንላለን፡፡ የፖለቲካ ምዕዳር ይስፋ ሲባል ይህን የበሰበሰ ምርጫ ቦርድ የሚባል ተቋም መፍርስ አለበት ማለታችን ጭምር ነው፡፡ ይህ መስሪያ ቤት መታደስ አይደለም መፍረስ የሚበቃው አይመሰለኝም፡፡
ለማንኛውም አዴግ ልብ ቢገዛ ጥሩ ነው፡፡ አሁን ቀና ብሎ የሚሄደው እየበዛ ነው፡፡ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት እያስተጋባ ነው፡፡ ጎርፎ ሆኖ ጠራርጎ ሳይወስደው በዚህ ህገወጥ በሆነ “የፀረ-ሸብር ህግ” ሰበብ የተሳሩ ዜጎችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፍታት፤ የፖለቲካ ምዕዳሩን ከሌሎች ሀይሎች ጋር በመተባበር ለማስተካከል አሳታፊ መልካም እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ በተናጥል የሚደረግ ህገ ወጥ ሹመቶችን የምርጫ ቦርድ ዓይነቱን ማቆም ባፋጣን ለአገራው መግባባት የሚረዳ ሁሉንም ያገባኛል የሚሉ ሀይሎች የሚያሳትፍ ጉባዔ መጥራት ይኖርበታል፡፡ ጉባዔውን ፋና እንደማይጠራው እምነት አለኝ፡፡ እነዚህ ሰዎች እኮ አብደዋል የምንለው ለዚህ ነው፡፡ መፍትሔ የሚፈልጉትን ከጥፋት ቦታ ነው፡፡