>

"ይህ ስፍራ የተማረክንበት ሳይሆን የተባረክንበት ነው" ፊት አውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ 

ፈቃደ ጫኔ
ንጉስ ምንሊክ የኢትዮጲያን ግዛት እያቀኑ ፣ እያስገበሩ ቀጠሉ፡፡ በተመሣሣይም የሌሎች የገበሩ አገሮች ህዝቦችንና ባላባቶችንም ወደ ሸዋ እያመጡ እንዲሠፍሩና እንዲኖሩ አደረጉ በዚህም ወጣ ባለና ባልተመደ መልኩ የህዝቦችን አንድነት ማጠናከር መቻላቸው ብልህነታቸውን ለማስታወስ አንድ ማስረጃ ነው፡፡
የሩቅ አገር ግዛት ሕዝቦችን አምጥተው በክብር እያሳደጉ ፣ የተማረኩ ባላባቶችን ግዛትና ሹመት እየሰጡ በነገድ ተለያይቶ የነበረውን ሁሉ በጋብቻ ፣ በባህልና ሐይማኖቱ ተሳስሮና ተቻችሎ በአንድነትና በፍቅር እንዲኖር አንዱ ያንዱን ጎሳና ሃይማኖትሣይንቅ አክብሮና አስከብሮ በሰላም ተስማምቶ እንዲኖር አደረጉት፡፡ የአንድነቱን ውጤትም ወደ በሃላ የድል ፍሬንም ለቅመውበታል፡፡
“በወጣትነታቸው ደጃዝማች ባልቻንና ፊት አውራሪ ሐብተጊዮርጊስን ንጉስ ምንሊክ አምጥተው ካሳደጓቸው በሃላ ለታላቅ ማእረግ አበቋቸው፡፡ ከእለታት አንድ ቀን ሁለቱ መኳንንት መንገድ እየተጓዙ ሳለ የተማረኩበት ቦታ ላይ ሲደርሱ ደጃች ባልቻ “ይኸውሎ የተማረክንበት ቦታ” ብለው ለፊት አውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ አስታወሷቸው ፊት አውራሪም “ይህ ስፍራ የተማረክንበት ሳይሆን የተባረክንበት ነው” አሏቸው ይባላል፡፡ 

ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ከተናገሯቸው ታሪካዊ ንግግሮች በጥቂቱ !! 

( አፄው ጭንቅላት ላይ ከነጫማችሁ እየወጣችሁ ላላችሁ ሁሉ መልስ ይሆናል!!!!)

* ሰው ሁሉ እኩል ስለሆነ ማንም ሰው ሰውን ባሪያ አይበል !!

* ሁሉም ሰው በየኃይማኖቱ ይደር !!

* ድኻ እወደደበት ቦታ ይቀመጥ !! በዘር ፣ በወገን ልዩነት አይከልከል !!

* የመሬት ጥያቄ ላቀረቡ የውጭ አገር ሰዎች ንጉሡ የሰጡት መልስ፡-
“የኛ አገር ፍትሐ ነገሥት ልዑሎች መሬት ይሽጡ አይልም፣ ያገሬ መሬት ባለቤቱ ሌላ ነው ከአባቶቻቸው
እየተቀበሉ ያቆዩት መሬት ነው !!… መሬቱ የሁሉም ስለሆነ አይሸጥም!!ማንም ሰው መሬቱን
ሊሸጥ አይችልም !! መሬትን መሸጥም፣ መስጠትም የሚችለው የመሬቱ ጌታ ነው!!”

* ለመንግሥት ተሿሚዎች የሰጡት መመሪያ፡-

“… እንቅልፍ ሳትወዱ ፣ መጠጥ ሳታበዙ፣ ገንዘብን ጠልታችሁ ተግታችሁ ሥራችሁን ፈጽሙ !! እኔ እናንተን ስለአመንኩ እናንተም የምታምኑትን ገንዘብ የማይወደውን ድሀ የማይበድለውንና የሚረዳችሁን ሰው እያመለከታችሁኝ ከሥራው በመግባት መንግሥታችንን እርዱ!!”

* በጣም ወደኋላ የቀረን ሕዝቦች ነን !! ገና የሚሠራ ብዙ ሥራ ስላለ ወጣቶቻችን መማር አለባቸው!!

* አባት ያለህ የአባትህን እሰጥሀለሁ፤ አባትህን መርቅ !! አባት የሌለህ አባትህ እኔ ነኝና ደጅ ጥናኝ !!

* እኔ ቤት እንጀራ የለም !! እንጀራ ያለው ትምህርት ቤት ስለሆነ እሠራሁት ትምህርት ቤት ልጆቻችሁን እያስገባችሁ አስተምሩ !!

* የኔ ርስት ኢትዮጵያ ናት !!የግል ርስት አልፈልግም !! ደግሞስ የተሾምነው እርስት ከተካፈልን ለሕዝቡ ማን ያካፍለዋል??!!

* ሐገራችን አንድትለማ የሚቀርቡንን ሁሉ በታላቅ ደስታና በአክብሮት እንቀበላቸዋለን!! በሌላ ለሚመጡብን ግን ሁላችን ሳናልቅ ሀገራችንን ለባዕድ አሳልፈን እንሰጥም !!

* የሚጠሉህን ሰዎች ከማጥፋት የሚጠላብህን ማጥፋት እንዲሉ የሸፈቱባቸውን የወጓቸውንና ያሤሩባቸውን ሰዎች በጋብቻ ፣ በዝምድና ወይም ወዳጅ አድርገው ያቀርባሉ እንጂ ክፉን በክፉ መመለስና መበቀልን አይሹም !!

* አንድ የፈረንሳይ ዜጋ የቦታ ግዥ ፈቃድ ሲጠይቃቸው ምኒልክ በሰጡት መልስ ፡-

” ያገሬ መሬት የሁሉምኢትዮጵያዊ ስለሆነ መሬት መሸጥ መለወጥ የሚችለው ሕዝቡ ነው !! ደግሞስ የውጭ ዜጎች መሬት እንዲገዙ ከፈቀድኩና ባለመሬት ከሆኑ ፤ ለኔ ምን ቀርቶ እገዛለሁ??!!”

ምንጭ ፡- የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ መጽሔት ቁጥር 1. ነሐሴ 1992 ዓ.ም
ከገጽ 16 እስከ 17

Filed in: Amharic