>

ከመስቀሉ ጀርባ የመሸጉ ስውር ካድሬ

ኢንተላ ኣይነር

ትክክለኛው የሐይማኖት አባት ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ የሰሜን ወሎ እና ከሚሴ ዞን ሀገረ ስብከት ረዳት ጳጳስ” የእነርሱ መዘዝ ነው፤ ወጣቱ አበላሸ የምንለው ነገር የለም…. ወጣቱን ሌላ የፓለቲካ አካል ቀሰቀሰው አሉ፤ ወታደሮቹን ማን ቀሰቀሳቸው?” ሲሉ የበግለምድ የለበሰሱት ቀበሮ፤መስቀሉ ስር የተደበቁት ሽፍታ አቡነ ማትያስ ግነ ያው በወያኔ ቴሌቪዥ ቀርበው “የሰላም ዋጋ ውድ ነው…..ሰላም (ስልጣን ለማለት ነው) ከእጃችን ካመለጠች አመለጠች ነው።” ሲሉ የወከሉትን ሃይማኖት ሳይሆን የተቀመጡለትን የህወሓት ፖለቲካ እንዳይወድቅ በሰላም ስም ሲሰብኩ ታይተዋል፣ ተሰምተዋልም፡፡

ቆይ ቆይ በቃና ዘገሊላ በአል ላይ የትግሬ አጋዚዎች የ12 አመት ህፃን ልጅ በጥይት ሲቀስፉና የስላሴን ህንጻ ሲያፈርሱ፣አወላጅ አባቱ የልጃቸውን ህይወት ለማትረፍ ወደ ሆስፒታል ይዘውት ሲከንፉ መሀል መንገድ ላይ አስቁሞ በጣር ላይ ያለ ህፃን ልጅ ህይወት ሲያልፍ፣ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ትልቅ መገለጫ የሆነውን ክቡር ታቦቱን የተሸከሙትን ቄስ በጢስ ቦምብ መጥተው ቄሱ ራሳቸውን ስተው ሲወድቁና ክቡሩ ታቦት መሬት ላይ ሲወድቅ፣ የንጹሀን ደም በእየቦታው ሲፈስ ይህንን ሁሉ አረመኔያዊ ተግባር የፈጸሙትንና እየፈጸሙ የሚገኙትን አጋዚዎችን ያላወገዘ የሐይማኖት መሪ የሐይማኖት አባት አባት ቀርቶ የሐይማኖቱ ተከታይ ሊባል አይችልምና አቡነ ማትያስ ስልጣኑን ለምእመኑ ማስረከብ አለባቸው፡፡
ይህ ካልሆነ ግነ መታወቅ ያለበት ነገር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሊቀጳጳስ አድርጋ ያስቀመጠችው ሰው የሀይማኖት አባት ሳይሆን የፐለቲካ ካድሬ ነውና ሁሉም ህዝበ ክርስቲያን ድርጊቱን ሊያየውና ሊያወግዘው ይገባል፡፡የኢትዮጵያ ህዝብ እምነቱን በፖለቲከኞች እያስሸረሸረና እያጠፋ መሆኑን ይወቅ፡፡መለስ ዜናዊ አሜሪካ ሄዶ የሰይጣኒዝም ምልክት የሆነውን ኮኮብ ባንዲራ ከቤተ ክርስቲያን ካልገባ ብለው ማስገደዳቸው የሚታወቅ ነው፤ የሞቱት ትግሬው አቡነ ጳውሎስም የሰይጣኒዝም ቁጥር አንድ ተከታይ የሆነችው ቢዮንሴ ስትመጣ ታቦት እንዲወጣ ማድረጋቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታች ነው፡፡
ለማንኛውም ለሐይማኖቱ ተቆርቋሪ የሆነ ሁሉ ህወሓትን ከእነጓዙ(አቡነ ማትያስና መሰሎቻቸው) ማስወገድ ግድ ይላል፡፡ አልያ ሀይማኖቱን ክዶ ፖለተከኞች በሚመሩት መንገድ እየሄደ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡
Filed in: Amharic