>
5:13 pm - Thursday April 19, 9088

የኋሊዮሽ ጉዞ (ዮሐንስ ደሳለኝ - ከጀርመን)

ሶስተኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የነበሩት ቶማስ ጀፈርሰን እንዲህ ብለው ተናገሩ “When a government fears the people ,there is liberty, when the people fear the government ,there is tyranny “
“መንገስት ህዝብን ሲፈራ ወይም ለህዝብ ይሁንታ ሲሰጥ ነፃነት አለ ወይም ተፈጥሯል አሊያ በምትኩ ህዝብ መንግስትን ከፈራ አምባገነንነት ተሰራፍቷል ወይም ተፈጥሯል”

ከዛሬ አስርተ ዓመታት በፊት ግፍ በዛብን ተጭቆንን ባሉ ጥቂት ሰዎች ተመስርቶ የኋላ ኋላ ድል ቀንቷችው ከተነሱበት ጠባብ አስተሳሰብ (ትግራይን ብቻ ነፃ የሚለው)ለግዜው የተላቀቁ በማስመሰል ህዝቡንም የብሄር ብሄረሰብ ነፃነት፣ የመፃፍ፣ የመናገር፣ በነፃ ሃሳብን ማንሽራሸር መብት ተቀዳጅተሃል እልል በል ብለው ነጋሪት ጎሰሙ አስጎሰሙም ይህ ሁኔታ እውነት እንዲመስል አንዳንድ ሚዲያዎችን ሰው በነፃነት እንዲጠቀምባችው የፈቀዱ አስመሰሉ በተፈጠረውም አጋጣሚ ብዙ የተባ ብዕር ያላችው ሰዎች ብቅ ብቅ ማለት ጀመሩ። በተለይ ሁላችንም የማንረሳው 1997(በፈረጆቹ 2005) የምርጫ ሰሞን የነበሩት ጋዜጠኞችን ጋዜጦችን እንዲሁም ጦማሮችን በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እንደዛ ግዜ ነበረ ለማለት እስከማንደፍረ ድረስ የራሳቸውን አሻራ ትተው አልፈዋል፣ ሆኖም ግን ይህ ውልደቱም ሆነ ዕድገቱ በአመጽ የሆነ የወያኔ ቡድን ታግያለሁ ላለው የብሄር ፣የመፃፍ፣ የመናገርና ሃሳብን በነፃ የመግለፅ ነፃነት አንድ በአንድ መግፈፍ ጀመረ ።

ከላይ የተገለጹት መብቶችና ገርበብ ብሎ የተከፈተው የፖለቲካ ምህዳር ፈፅሞ እንዳይዘጋ የጠየቁና በተለይ እንደ ሙልጌታ ሉሌና እስክንድር ነጋ ያሉና መሰል ጋዜጠኞችን ቅርጥፍ አድረጎ ከበላ በኋላ ቅርሻቱን በህዝብ ላይ ማራገፍ ጀመረ ይህን ገና ከወታደራዊ አገዛዝ ማነቆና ተፀዕኖ ያልተላቀቀ ህዝብ ይባስ ብሎ ወደ ኋላ ወደ ጋርዮሽ ዘመን ውስዶ ያኔ በፈራረሰችው ራሻ እንደነበረው የአንድ ሚዲያ ብቻ ተጠቃሚ ለማድረግ ከዋናው የመንገስት ልሳን ውጭ እንደነ ፋና ኤፍኤም፣ እንደነ ዘሚት 97፣ የመሳሰሉትን በራሱ ወጭ ከከፈተ በኋላ ሁሉንም የህትመትና ዲጅታል ሚዲያ አሽመድምዶ ዛሬ ላለንበት ሁኔታ በቃን።

አሁንስ ሁኔታው ምን ይመስላል?

ከላይ ቶማስ ጀፈርስን እንዳሉት አዎ ህዝብ መንግስትን ከፈራ በትክክል አምባገነንነት ይፈጠራል ይህ ደግሞ የወያኔ ጉጀሌውን መንግስት ይወክላል በአሁን ሰአት ህዝቡ ርስ በርሱ እንዳይተማመን በአንድ ለአምስት በማደራጀት ዕድሜያችውን ለማራዘም ጥረት ላይ ናቸው ሌላው አሁን አለም እየተጠቀመበት ያለውን ማህበራዊ ሚዲያ እንደ ፌስ ቡክ፣ ዋትሳፕ፣ ትዊተር፣ ቫይበርና የመሳሰሉትን በመዝጋት በአንድ ወቅት አለም በግሎባላዜሽን ምክኒያት አንድ መንደር እየሆነች ብሎ ሲያቅራራ የነበረው ሟቹ መለሰ እሱ ዘርግቶላቸው በሄደው ከፋፍለሀ ግዛው ፖሊሲ እንኩዋን ከሌላው አለም ልንገናኝ ይቅርና አገር ውስጥ እንኩዋን በስልክ መነጋገር አልተቻለም ሌላው አለም አስር እጥፍ ወደፊት እኛ ደግሞ እንደግመል ሽንት ወደኋላ ያሳዝናል!!!

ይህ ነው እንግዲህ በታሪክም እንዳየነው እንደሰማነው የአምባገነኖች ባህሪይ አንዲት አገር በተለይ ደግሞ በዚህ ግዜ ኢንፎርሜሽን ገንዘብ በሆነበት አለም የእኛዎቹ ጉዶች ሰልጣናችውን ለማራዘም ሁሉንም ሚዲያ ዘጋግተው ህዝቡንም በነዛ አደንቋሪና ለዛ ቢስ የመንግስ ሚዲያዎች ነጋ ጠባ ያላዝኑበታል ይህም ሁኔታ ሲመረውና ሲያንገሽግሽው ሰው አደባባይ ወጣ ምንም እንኳን የእነሱ ምላሽ ጥይት ቢሆንም አዎ ለጥቂት ግዜ ብዙሃኑን ማታለል ይቻላል ነገር ግን ሁሌ እያታለሉ ግን መኖር አይቻልም አድገዋል የሚባሉት አገራት እኮ እዚህ ደረጃ ለመድረሳችው ዋናው ምክኒያት በስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች ጋዜጦኞችና ጦማሪያን ገና በማለዳው ምን አሉ ኣያሉ ስለሚያነቡና ስለሚሰሙ እኮ ነው ምክኒያቱ የሚስተጋባው የህዝብ ድምፅ ስለሆነ ነገር ግን እነዚህን የህዝብ አይንና ጆሮ የሆኑትን የብዙኋን መገናኛ ማፈን ውጤቱ በአንድ ወቅት አቶ ኃይለማሪያም እንዳሉት አገርን የሚያህል ነገር በገምት መምራት ይጀመራል ፣ይህም የግምት አመራር አሁን ላለንበት የኑሮ መመሰቃቅል ፣የፖልቲካውና የማህበራዊው መተጋብሮ ውሉን ማጣት ፣በየቦታው የህዝቦች ድምጻችን ይሰማ ምክኒያት ነጻ ሚዲያ አለመኖርና ይሄው ቡድን መስማትና ማዳመጥ የሚፈልገው የራሱን ካድሬና የደህንነት ሰዎች ብቻ ስለሆነ የነሱ መረጃ ደግሞ ውጤቱ ይሄው ዙሪያ ገባውን በህዝብ አመፅ መናጥ ሆነ።

መፍትሄው ምን መሆን አለበት?

ከተቻለ የጉጀሌው መንግስት ሹማምንት ተመካክረው የግል ህትመቶችንንና ሚዲያዎችን መልቀቅ በርገጥ ከወያኔ ባህሪይ ስንነሳ ይህን ማሰብ ጅልነት ነው ነገር ግን በአሁን ሰአት በተለያዩ የአገሪቱ ክልል የፈነዳው ለውጥ የሃይል ሚዛኑን አስጥቶት አንዳንድ ነገሮችን ለመወያየት የክጀለውን ውያኔን እኛ በውጭ የምንኖር በተለያዩ ሚዲያዎች ስራችውን ከምንግዜው በበለጠ በማጋለጥ መፈናፈኛ ማሳጣት አለብን ወገኖች መረጃ ወሳኝ ነው።

በተለይ በአሁን ሰአት ተዘግቶ ያለውን የኢንተርኔት አገልገሎትና ከሱም ጋር ተያይዞ የታፈኑትንና የሚሰለሉትን የማህበራዊ ሚዲያዎች ከመቸውም ግዜ በይበልጥ ማጋለጥና ውያኔን ራቁቱን ማስቀረት አለብን አገር ቤት ያለውም ህዝብ እንዴት መረጃ ማግኘት እንዳለበት መዝየድ አለብን ካልሆነ አፋኙ ቡድን እንደሆነ የኛን መዘናጋት ካየ በያዘው አቋም ከመቀጠልና አገር ከማበላሸት የሚያግደው የለም።

እነሱ እንደሆነ በአንድ ወቅት አንድ ሰው የገጠመውን ግጥም አይነት ባህይ ነው ያላችው እኔ አውቅልሃለሁ ይሉና እኔንትህን ያጠፉታል። እነሆ ጀባ ግጥሙን

እንዲህ የምሆነው ላንተነው እያለ
እንዲህ የማደርገው ላንተነው እያለ
መኖሬም መሞቴም ላንተነው እያለ
እኔነቴን ሁሉ እሱው ጠቀለለ
ድሮስ ላንተ ስል ውስጥ እኔነት የታል?
ላንተ ነው
ላንተ ነው
እያለ ሲነጥቀኝ
እያለ ሲዘልፈኝ
እያለ ሲገርፈኝ
እያለ ሲያስከፋኝ
እያለ ሲገፋኝ
በስተመጭረሻ
እኔም ከሱ በቀር “እኔ”ምለው ጠፋኝ

 

Filed in: Amharic