>

እዉነት የትግራይ የበላይነት የለምን ??? (ሰልማን መሀመድ)

ሁሌም የሚገርመኝ የክርክር ርእስ አንዱ ” የትግራይ የበላይነት አለ ወይስ የለም “ የሚለዉ ሲሆን
የትግራይ የበላይነት የለም የሚሉት አካላት በሙሉ አንድ የሚያደርጋቸዉ ሰዉን  ለማሳመን የሚጠቀሙት
ዘዴ ተመሳሳይ መሆኑ ነዉ። ሁሌም ስትከራከራከራቸዉ
” ተመልከት የበላይ ሆነብኝ የምትለዉ የትግራይ ህዝብ በድህነት እየማቀቀ ነዉ የሚጠጣዉ ዉሃ የለዉም መሬቱም አያበቅልም ታድያ ይህ ህዝብ እንዴት ነዉ የበላይ የሆነዉ” አይነት ያለፈበት የብልጣብልጥ ጨዋታ በመጫወት የተከራካሪዎችን ልብ በማራራትእና አንጀት በመብላት ክርክሩን በአሸናፊነት ለመደምደም ይሞክራሉ።
ከእነዚህ ሰዎች ጋር ስትከራከሩ አዎ የትግራይ ህዝብ ሁሉም አልተጠቀመ ይሆናል ይህ ማለት ግን የበላይነት የለም ማለት አይደለም በሏቸዉ ለምሳሌ China ካላት 1.5 ቢሊዮን ህዝብ ዉስጥ ከ 87 ሚሊዮን በላይ የሚሆን ህዝብ ከኢኮኖሚዋ አልተጠቀመም ነገር ግን 87 ሚሊዮን ከኢኮኖሚዋ ያልተጠቀመ ህዝብ መያዟ አለም ላይ የቻይናን የበላይነት አላገደዉም። አሜሪካም አዉሮፓም ቤት አልባ ዜጎች አሏቸዉ ግን የበላይ ናቸዉ የበላይ የሆኑት ድሀ ዜጋ ስለሌላቸዉ ሳይሆን ፖለቲካዉን እና ኢኮኖሚዉን ስለተቆጣጠሩት ነዉ።
ለእነዚህ አገሮች ሲሆን ሁሌም የማይደረገዉ ይደረጋል ፣ የማይሆነዉ ይሆናል እነሱ ሲበደሉ ነገሩ ይገናል በተመሳሳይ ወንጀል ሌላዉ ላይ ሲፈፀም ሰሚ የለም ምክንያቱም በፖለቲካዉም ሆነ በኢኮኖሚዉ ዘርፍ ደካሞች ስለሆኑ። የትግራይም እጣ ፈንታ አካሄዱ ከዚህ ብዙም የተለያ አይደለም የትግራይ የበላይነት አለ ለማለት የግድ 5 ሚሊዮን የትግራይ ህዝብ ከድህነት መዉጣት የለበትም ነገር ግን ሂደቱ ወደዛዉ ነዉ።የእነሱ ሎጂክ ሌላዉ ህዝብ እየደኸየ ሁሉም የትግራይ ተወላጅ ከበለፀገ በኋላ ድንገት ተነስታችሁ የትግራይ የበላይነት አለ ብትሉን እናምናለን ነዉ ።
.
በአንድ ወቅት አማራዉ ምን ሆነ መሰላችሁ
.
የቀድሞው የደቡብ ርእሰ አስተዳደር አቶ ሽፈራው ሹጉጤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ጉራፈርዳ 78,000 (ሰባ
ስምንት ሺ) የአማራ ተወላጆችን አፈናቀለ። ለስንት ዘመን ያፈሩትን ንብርት ቤት ወርሶ ሴት አራስ ልጅ
ከቤት አስወጥቶ ጫካ ወረወረ። አዎ አቶ ሽፈራዉ ሽጉጤ የአማራዉ የጉራፈርዳ ነዋሪዎች መዉደቂያ አጥተዉ ከነልጆቻቸዉ ጎዳና ላይ እንዲጣሉ በመወሰን ለጌታቸዉ ታማኝነታቸዉን አረጋገጠ አዛዡም ጨካኝ ታዛዡም ጨካኝ በመሆናቸዉን አሳዩን ዛሬ ድረስ የአማራ ህዝብን የማፈናቀል ፍዳና መከራ አላቆመም።
አቶ ሽፈራዉ ሽጉጤ  አማራን በማፈናቀሉ እድገት አገኘ ከክልል ወደ ፌደራልም መጣ ምኞቱም ተሳካለት
ዛሬ ወሮ በላ የTplf አፈ ቀላጤ ሁኗል  ስርአቱ እንዳይናድ ትልቅ የፕሮጋንዳ ሥራ እየሰሩ ካሉት ዋነኛውና
አንዱ ነው ።

በአንድ ወቅት ትግሬዎች 

ምን ሆኑ መሰላቹህ የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ሊጀመር አካባቢ በኢትዮጵያ ይገኙ የነበሩ ኤርትራውያን ኢትዮጵያ እንዲወጡ ሲታዘዝ በወቅቱ የደቡብ ክልል አስተዳዳሪ የነበረው አባተ ኪሾ በክልሉ የሚገኙ ኤርትራውያንን የሚያስወጣ ግብረኃይል አቋቁሞ ኤርትራውያንን ማባረር ሲጀምር በርካታ የትግራይ ተወላጆችም ኤርትራዊ ተብለው ከክልሉ እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ይደርሳቸውና ለተቃውሞ ተሰባስበው ወደ አባተ ኪሾ ቢሮ በመሄድ “እኛ ኢትዮጵያውያን ትግሬዎች እንጂ ኤርትራዊ አይደለንም” በማለት ተቃውሞ ሲያሰሙ በሁኔታቸው የተገረመው አባተ ኪሾ “እኔ ኤርትራዊ ሁኑ ኢትዮጵያዊ ትግሬ መለየት ስለማልችል አዲስ አበባ አራት ኪሎ ቤተመንግሥት ሄዳችሁ መለስ ዜናዊ እየለየ ይላክልኝ” በማለት ጠራርጎ ያባርራቸዋል፤ በዚህ የተናደዱት የሕወኃት አመራሮች አባተ ኪሾን በሙስና ወንጅለው ወደእሥር ቤት ወርውረውታል።ወህኒ ቤት ዉስጥ የቀድሞ አባተ ኪሾ፣ ስዬ አብርሃ፣ ዶ/ር ታዬ ወ/ሰማያትና ታምራት ላይኔ በእስር እያሉ ያወጋሉ። አባተ ኪሾ እንዲህ አሉ፥ « መለስ ዜናዊ የተናገረኝን መቼም አልረሳውም፤.. እንዲህ ነበር ያለኝ፤“አባተ አንተና የአዲስ አበባ ቆሻሻ ማፍሰሻ ቱቦ አንድ ናችሁ።!”..ማለታቸውን አንደኛው እስረኛ ነግሮኝ ነበር። የአባተ እንደ ወንጀል የተቆጠረበት ትግሬን ከኤርትራዉያን መለየት አለመቻሉ ነበር።በነገራችን ላይ አባተ ኪሾ ላይ የፈረደው ዳኛ ሁለተኛ ዲግሪውን መቀሌ ዩኒቨርስቲ ሲማር ፕረዘንቴሽን እንዲያቀርብ መምህሩን ሲጠይቀው “ይቅርታ መምህር ዛሬ ጉንፋን ስለያዘኝ በእንግሊዘኛ ማቅረብ አልችልምና በትግርኛ ይፈቀድልኝ?”
.
እና ምን ለማለት ነዉ ትግራይ ፖለቲካዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ የበላይነቱን እንደ ነብር ጭራ ይዛ አልቅም ብላለች። ይህ ታሪክ የተመዘገበ የትግራይ ፖለቲካዊ የበላይነት እንዳለ ቀላሉ ማሳያ ነዉ። የክልሎች እኩልነት ቢኖር በአንድ ክልል ተመሳሳይ ወንጀል ለፈፀሙ ሁለት ሰዎች ለአንዱ የእድገት ለሌላኛዉ የዉርደት ፍርድ አይኖርም ነበር። የአማራን ህዝብ ያፈናቀለዉን ሽፈራዉ ሽጉጤን እድገት ሰጥተዉ (የትምህርት ሚ/ር ፕሬዝደንት) ትግሬዎችን ያፈናቀለዉን አባተ ሻኪሶን እስርቤት ባልወረወሩት ነበር።

Filed in: Amharic