>
5:13 pm - Thursday April 18, 5805

የገና አባት የሚባለው ''ቅዱስ-ኒኮላስ'' ወይስ ''ሳንታ-ክላውስ'' ?

እንደ Worldbook Encyclopediaመረጃ መሰረት ወፍራሙና ዘናጩ ሰው ቅዱስ ኒኮላስ(ሳንታ ክላውስ) ወይም በተለምዶ የገና አባት የሚባለው የጥንት የስካንዲኒቪያን አገሮች ኖርዌጂያን ቋንቋ ተናጋሪ ህዝቦች ዘንድ የባእድ ( pagan) አምልኮ ታሪክ ያለው ሲሆን ለምሳሌ በጥንት ኖርዌጂያኖች እምነት መሰረት ሳንታ ክላውስ በቤት ውስጥ ባለ የእሳት ጭስ መውጫ (ቼሚኒ) በኩል ይገባል የሚል እምነት ስላላቸው የጥንቶቹ ኖርዌጂያኖች የቤታቸውን ጭስ ማውጫ ቼሚኒ በጣም ትልቅ አድርገው ይሰሩ ነበር:: በተጨማሪም “ሐርታ” የሚባል አማልክት ያላቸው ሲሆን ይህ አማልክት በቤታቸው ባለ እሳት ማንደጃ አካባቢ በላይ ቢመጣ ለቤታችን ጥሩ እድል ይሆናል ብለው ያምናሉ::

እንደ እውነቱ ከሆነ ብዙ ሰዎች ትክክለኛው “ሳንታ ክላውስ” በቅዱስ ኒኮላስ ስም በኤሽያ በ4ኛው ክ/ዘመን ላይ የኖረ ጳጳስ ነበረ ብለው ያምነሉ:: ይህ ግን እውነት አይደለም ሀሰት እንጂ እንደ እውነቱ ከሆነ ጥቂት የሚባሉ የሮማ ካቶሊክ ጳጳሶች “ቅዱስ ኒክ” በሚለው ስም ስያሜ ተጠቅመዋል:: ትክክለኛው “ኒኮላስ” የሚባለው አንዱ ብቻ ነው:: እርሱም ታላቁ የአመጽ እና የጥፋት ሰው “ናምሩድ” ሲሆን እርሱም “አንዱና ሀያሉ እግዚያብሔርን ተቃዋሚ” ይባላል:: “ኒኮላስ” የቃሉ ፍቺ “አንዱ የሀያሎች ሀያል” ማለት ሲሆን ዋና ባህሪውም አማልክትነት ይወክላል::

“ኒኮላስ” ከአንድ ሺህ አመት በፊት ኤሺያ ለሚገኘው ለታናሹ ጳጳስ የሚያምር አረንጓዴ ቅጠሎች ያለበት የለመለመ ዛፍ በስጦታ አበርክቶለታል::
በእስካንዲቪያን በአምላካቸው “ኦዲየን” ወይም “ግንዱ” የተባለው የጸሐይ አምላክ ልዩ ስጦታ በ “ዩል” በአል ግዜ አገሩን ሁላ በአረንጓዴ ዛፎች ይሸፈናል:: በዛፎቹ አማካኝነት አምላካቸውን ያገኛሉ:: በተጨማሪም ለአምላካቸው ዛፎቹን ማስታወሻ ያደርጋሉ::

ቶኒ ቫን ሪንተርገም የተባለ ጸሐፊ እንዲህ ይላል “ሳንታ” ማለት “#ዲያብሎስ” ማለት ነው ይለናል:: በጥንት ግዜ በመጀመሪያ “ሳንታ ክላውስ” እና የገና ዛፍ አንድ ላይ ተገኙ ይለናል ቶኒ ቫን

“ቅዱስ ኒኮላስ” ማለት ንጉስ “ናምሩድ” ማለት ሲሆን : እግዚያብሔር ስለ ናምሩድ እንዲህ ነበር ያለው “ኩሽም ናምሩድን ወለደ፤ እርሱም በምድር ላይ ኃያል መሆንን ጀመረ።እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ኃያል አዳኝ ነበረ፤ ስለዚህም። በእግዚአብሔር ፊት ኃያል አዳኝ እንደ ናምሩድ ተባለ። የግዛቱም መጀመሪያ በሰናዖር አገር ባቢሎን፥ ኦሬክ፥ አርካድ፥ ካልኔ ናቸው።” የመጽሐፍ ቅዱስና የጥንታዊ ስነ ቅርስ አጥኝዎች እንደሚያስረዱት ናምሩድ እጅግ ግዙፍ ተክለ ሰውነት ያለው ሲሆን በተጨማሪ ከሰው ተፈጥሮ ማንነት በላይ የሆነ እጅግ የተለየ ማንነት ያለው ናምሩድ የኔፍሌምስ (የወደቁት መላእክት) ወይም የዲያብሎስ ዘር ነው ይሉናል ጥናቱን ያጠኑት የመጽሀፍ ቅዱስ አጥኚዎች :: በቅጽል ስሙ የጥፋት ሰው የሚባለው ናምሩድ የታላቋን ባቢሎንን ከተማ የገነባ ታላቅ የዓለማችን ጥቁር ንጉስ ነው:: በተጨማሪም የአለም መንግስታቶች አሁን የሚጠቀሙበትን ህግ ያረቀቀ ታላቅ የጥፋት ሰው ነው ናምሩድ:: በመጽሐፍ ቅዱስ እግዚያብሔር ስለ ናምሩድ ታላቅ አዳኝነቱ ሲነግረን የሚያድነው የጫካ እንሰሳ ሳይሆን ህዝቦችንና አገሮችን ሲሆን እንደ መጽሀፍ ቅዱስ አጥኝዎች አገላለጽ ናምሩድ ታላቅ የምድራችን ሀይለኛ ጦረኛ ሰው ጭምርም ነው :: ናምሩድ የጥፋት ሰው ከጥፋት ውሀ ቡኋላ ለመጀመሪያ ግዜ በምድር ላይ እግዚያብሔር መንፈሱ የሚጸየፋቸውን የጥንቆላ : የአስማት : የመተት ድግምት ስራዎች እንዲሁም የጣኦት (የሰይጣን) አምልኮ ያስጀመረ ታላቅ የጥፋት ሰው ነበረ:: ናምሩድ ሌላው የሚመሰለው የጸሐይ አምላክ ሲሆን ሚስቱ ደግሞ ሰመራሚስ “የሰማይ ንግስት” (Queen of Heaven) : “የእግዚያብሔር እናት” (Mother of God) እንዲሁም የጨረቃ አምላክ ነች:: ሰመራሚስ ለናምሩድ እናቱም ሚስቱም ነች::

Inline image 2

“ዲሴምበር 25” እና እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ደግሞ “ታህሳስ 29” የሚከበረው የልደት በአል የማን የውልደት ቀን ነው?
ሁላችንም የ “ዋርነር ኪለርን” “Werner Keller’s book The Bible as History” መጽሐፍ ስናነብ ስለ “ገና” “Christmas” በአል ሚስጥር ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር እያስተያየ በጥሩ አገላለጽ ከነ ሙሉ ታሪኩ ጽፎታል:: እኔም ዋና ዋና የሀሳቡን ጭብጥ ለማስረዳት አሳጥሬው እንደሚከተለው አዘጋጅቼዋለሁ::እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ዲሴምበር 25 የሚከበረውን የ“ገና” “Christmas” በአል ምክንያት በማድረግ በተደረገው የታሪክ ጥናት እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር A.D. 324 ላይ ለመጀመሪያ ግዜ የ“ገና” “Christmas” በአል እንደተከበረ መረጃዎች ተገኝተዋል::

በሮማውያን አገዛዝ በዘመነ በባዛንታይን ስርወ መንግስት በግዜው አብዛኛውን የአለም ክፍሎች በመግዛት የሚያስተዳድረው ንጉስ “ጁስቲኒያን” Justinian [A.D. 527-565] በይፋ የገና “Christmas” በአል እንዲከበር አወጀ::

ዲሴምበር 25 በጥንት በሮማውያን “ድል ያልነሳው የልደት ቀን” ( ‘Dies Natali Invictus,’ ‘the birthday of the unconquered,’ ) በበረዶው የክረምት ወራት ጸሐይ በምትጠፋበት ግዜና አብዛኛው የአውሮፓና ከፊል የሰሜን አሜርካ እንዲሁም ከፊል የኤሽያ አገሮች ቀኑ በጨለማ በሚዋጥበት ግዜ የሮማውያን ወታደሮች ለ “ፀሐይ አምላክ” ዲሴምበር 25 ላይ አምልኮና በአል ያደርጉ ነበር በጣም የሚገርመው ነገር የ “ክርስትያን ቤተክርስትያንም” ዲሴምበር 25 መሱሁ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት ቀን ነው ብለው አምነው ሲያከብሩ መታየታቸው ምን ያህል የዲያብሎስ እርኩስ የሀሰት መንፈስ ቤተክርስትያንን በክርስትና የሐይማኖት ስም እንደያዛት በግልጽ ያሳያል::

የእግዚያብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደው በእውነት ዲሴምበር 25 ነውን? በነጽሐፍ ቅዱስ ስለ መሲሁ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ውልደት በጥንቃቄ የጻፈው ቅዱስ ሉቃስ እንዲህ ይላል ሉቃ 2:8 “የበኵር ልጅዋንም ወለደች፥ በመጠቅለያም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው። በዚያም ምድር መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩ እረኞች ነበሩ።” ይህ የሚያሳየው ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደበት ግዜ ወቅቱ ክረምት ሳይሆን በጋ እንደነበረ የሚያሳይ ሲሆን እስከ ዛሬ ድረስ ጌታ ኢየሱስ በተወለደባት በቤተልሄምና በአካባቢው ባጠቃላይ በክረምት ወቅት እንኳን እረኞች ከብቶችና በጎች ከቅዝቃዜው የተነሳ ወደ ውጭ አይወጡም:: ለዚህም ደግሞ ማረጋገጫው እስከ ዛሬ ድረስ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደባት በቤተልሄምና በአካባቢው ባሉ አገሮች ውስጥ ያለው የክረምቱ የቅዝቃዜ መጠን ሲለካ እንደ ሜትዎሮሎጂ መረጃ መሰረት እነደሚከተለው ይሆናል::

ዲሴምበር -2.8 : ድግሪ ጃንዋሪ -1.6 ድግሪ ፌብሩዋሪ – 0.1 ድግሪ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራቶች በተጨማሪ ሀይለኛ መጠን ያለው ዝናብ በእነዚያ በክረምት ወቅቶች በየአመቱ ይመዘገቡበታል:: በግምት ዲሴምበር ላይ 6 ኢንች እና ጃንዋሪ 8 ኢንች ከፍተኛ የዝናብ መጠን በቤተልሄምና በአካባቢው ባሉ የእስራኤል አገሮች ከከፍተኛ ቅዝቃዜ ጋር ያላቸው ሲሆን ይህ የአየር ንበረት መረጃ ከ2000 አመት በፊት ያለውና አሁን ያለው ተመሳሳይና አንድ አይነት የሆነ ዘመናዊ የአየር ንብረት መረጃ ስብስብ ውጤትን ያሳያል::

በ“ገና” “Christmas” በአል በቤተልሄም በአሁን ሰአት እንደ ጥንቱ በጣም ሀይለኛ የቅዝቃዜ ውርጭ ያለው ሲሆን በምድሩ ላይ ምንም አይነት የቤት እንስሳና ሰው አይታይም:: እንዲሁም በተጨማሪ በእስራኤልና ፍልስጤምን ጨምሮ 8 ወር ሙሉውን የበጋ ወራት ጊዜያቶች ያላቸው ሲሆኑ በክረምት ማንኛውም የቤት እንሰሳም ሆነ ሰው ከቤት ውጭ አይታይም::
በ“ገና” “Christmas” በአል ወቅት አካባቢ በፍልስጤምም ሁለቱም ማለትም እረኞችም ሆኑ የቤት እንሰሳዎችም ሁሉ በክረምት ከቤት አይወጡም::
ቅዱስ ሉቃስ በወንጌል መልእክቱ ምንድ ነው የሚነግረን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደው ክረምት ከመግባቱ በፊት እንደሆነ እረኞችን ጠቅሶ አስረድቷል::
“ሽሽታችሁ በክረምት እንዳይሆን ጸልዩ! ” ማር 13:18

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት እውነተኛው ቀን የቱ ነው?

በብዙ ሚሊዮን የይስሙላ “ክርስቲያን” እና የስም “ክርስቲያን” የሀይማኖት ተቋሞችን ይከተላሉ:: አብዛኛዎቹ የይስሙላና የስም ክርስቲያኖች ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ቀን እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ዲሴምበር 25 እና እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ደግሞ ታህሳስ 29 የሚከበረውን አባል በሆኑባቸው በሀይማኖት ድርጅቶች አማካኝነት ትክክለኛ ቀን ነው ብለው ያምናሉ:: ብዙ ባህላዊ የክርስትያን የሀይማኖት መሪዎች : ሰባኪዎችና ቄሶች በተሳሳተ የሐይማኖት አምልኮ ግንዛቤ ሰዎችንም እያሳሳቱ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት ቀን ይህ ነው በማለት “ፀሐዩ አምላክ” “ናምሩድ” የተወለደበትን ቀን ያመልካሉ ያስመልካሉ:: ጌታ ኢየሱስም እነዚህን ሰዎች እንደዚህ ነው ያላቸው:: “የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ተብሎ እንደ ተጻፈ በእውነት ትንቢት ተናገረ። የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትታችሁ ጽዋን ማድጋንም እንደ ማጠብ የሰውን ወግ ትጠብቃላችሁ፥ ይህንም የመሰለ ብዙ ሌላ ነገር ታደርጋላችሁ። ማር 7:7_8

2:-የማቴዎስ ወንጌል በድጋሚ ይህ የሰው ሀሳብና ስርአት የሆነው የ “ገና” “Christmas” በአል እንዲህ በማለት ይደግመዋል:: “እናንተ ግብዞች፥ ኢሳይያስ ስለ እናንተ። ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤ የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ብሎ በእውነት ትንቢት ተናገረ። ማቴ 15:7_9

የኢየሱስ ክርስቶስ ትክክለኛውን የውልደት ቀን እርግጠኛ ሆኖ ለመናገር አይቻልም:: ነገር ግን ቅዱስ ሉቃስ ከጻፈው የወንጌል መልእክት በመነሳት መገመት ይቻላል:: “በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ፥ ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ። መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ። ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት።” ሉቃ 1:26_28

ከላይ ቅዱስ ሉቃስ እንደገለጸው ኤልሳቤት በጸነሰች በ6 ወር ወደ ጌታ ኢየሱስ እናት ማርያም እንደመጣ እና የምስራቹን እንዳበሰራት እናነባለን ከጽሁፉ እንደምንረዳው በ6ኛው ወር ከተባለ ከአመቱ የመጀመሪያው ወር ጀምረን እየቆጠርን እስከ 6ኛው ወር ስንመጣ የምናገኘው ወር “ጁን” ሲሆን ድንግል ማርያም የምስራቹን የተነገራት የመጀመሪያው ወር “ጁን” ቢሆን ተብሎ ቢታመንና እላዩ ላይ 9 የእርግዝና ወሮችን ብንደምርበት የምናገኘው ወር “ማርች” ወይንም “አፕሪል” ሊሆን ይችላል:: ምክንያቱም በ6ኛ ወር ተባለ እንጂ ቀኑን በትክክል አልተገለጸምና ስለዚህ ትክክለኛው የጌታ ኢየሱስ ልደት “ማርች” ወይም “አፕሪል” ሊሆን ይችላል:: እንጂ የእግዚያብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ቀን እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ዲሴምበር 25 እና እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ደግሞ ታህሳስ 29 አይደለም !

“ዲሴምበር 25” እና እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ደግሞ “ታህሳስ 29” የሚከበረው የልደት በአል የማን የውልደት ቀን ነው?

Filed in: Amharic