>
5:13 pm - Sunday April 19, 5953

ህወሃት ጥገኛ ተውሳክ ነው፦ ንቀሉት! (ስዩም ተሾመ)

“ሃይል” (power) ማለት አንድን ነገር መለወጥ (Change) የሚስችል አቅም ነው፡፡ ሃይል ቀጥተኛ የሆነ (active) እና ቀጥተኛ ያልሆነ (passive) በማለት ይከፈላል፡፡ ቀጥተኛ የሆነ ሃይል ለውጥን የማምጣት አቅም ሲኖረው ቀጥተኛ ያልሆነ ደግሞ ለውጥን የመቀበል አቅም አለው፡፡ ለምሳሌ #እሳት ወርቅን የማቅለጥ ቀጥተኛ አቅም አለው፣ #ወርቅ ደግሞ የመቅለጥ (ለውጥን የመቀበል) ቀጥተኛ ያልሆነ አቅም አለው፡፡ #አፈር የመቅለጥ አቅም የለውም፡፡ ስለዚህ በእሳት ሙቀት እንደ ወርቅ ቀልጦ ቅርፁን በመቀየር ለውጥን አይቀበልም፡፡ አፈር በእሳት ይፈረካከሳል እንጂ አይቀልጥም፡፡ በመሆኑም አፈርን እሳት የምትጥደው ለመፈካከስ እንጂ ለማቅለጥ መሆን የለበትም፡፡ #ኦህዴድና_ብአዴን ኢህአዴግን ለመቀየር የሚያደርጉት ጥረት ህወሃትን ለመቀየር ሳይሆን ለመፈረካከስ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም ህወሃት በኢትዮጲያ ፖለቲካ ውስጥ የማይገባው ጥቅም እያገኘ ያለ ጥገኛ (Parasite) ነው፡፡እስኪ አንድ …እንደው እንድ የህወሃት አመራር ወይም ደጋፊ “የኦህዴድና ብአዴን ጥያቄ ተገቢነት አለው ወይም ተገቢ ምላሽ ሊሰጠው ይገባል” የሚል ነገር ሲናገር ሰምታችሁ ታውቃላችሁ? በጭራሽ የለም! ዛሬ ብቻ ሳይሆን ከ18ኛው ክ/ዘመን በጥባጭ ራስ #ስሁል_ሚካኤል እስከ 20ኛው ክ/ዘመን የህወሃት መስራቹ #ስሁል፣ ከአቦይ ስብሃት እስከ አባይ ፀሃዬ ብትመለከቱ ሁሉም #የትግራይን_የበላይነት ለማረጋገጥ የሚታትሩ ዱኩማኖች ናቸው፡፡ ሁሉም ጥገኞች ናቸው! ጥገኛ ሃይልን ነቅለህ ትጥለዋለህ እንጂ የጋራ ጥቅም (mutual benefit) እንዲኖር አትጠይቀውም፡፡ ምክንያቱም ለጋራ ጥቅም የሚሆን የሚያበረክተው የራሱ የሆነ ነገር የለውም!! አፈርን መፈረካከስ እንጂ ማቅለጥ አይቻልም፡፡ ጥገኛ ተውሳካን መንቀል እንጂ ማባበል አያስፈልግም!! ሺህ አመት ብታባብሉት ህወሃት ከጥገኝነቱና ከራሱ ጥቅም ሌላ ነገር ማሰብ እንኳን አይችልም!!

Filed in: Amharic