>

ገዳዩ ለቅሦ ደራሽ (ስለሺ መላቱ)

በወገኖቼ ላይ እየደረሠ ያለውን ስቃይና እልቂት ባሠብኩት ቁጥር በጨካኙ ገዳይ የትግራይ ሕወሐት ላይ ያለኝ ጥላቻ፣ ንዴትና አልሕ ይሕ ነው ብዬ በቃላት መግለፅ ይሣነኛል። ይሕ ፍዳና ስቃዩ አላልቅ ያለውን ምሥኪን ወገኔን በረሐብ የሚያሠቃዩት አልበቃ ብሏቸው ይሕንኑ የስቃይ ኑሮውን በሠላም እንዳይገፋ ተወልዶ ያደገበት ወልዶ የተዋለደበት ቀየው ድረስ በመሔድ ሙሉ ቤተሠብን ያካተተ ጅምላ ጭፍጨፋ እየፈፀሙበት እነሆ አመታት ወደ ኋላ ተቆጠሩ።
አሁንም ገና ደም የማፍሠሥ ሡሡን ያልተወጣው ይህ የትግራዩ ገዳይ ቡድን በሁሉም ላይ የፈፀመው ግድያ እንዳለ ሆኖ ሠሞኑን በኦሮሞና በሶማሌ ብሔረሰቦች መካከል ሆን ብሎ ደም አፋሣሽ ፀብ በመጫር መልሶ እሱው እራሡ በመከላከያ ሀይሉና አሰልጥኖ ባስታጠቃቸው የአካባቢ ሚሊሻዎች አማካይነት መግደሉንና ማፈናቀሉን ሥራዬ ብሎ ተያይዞታል፤ ወደፊትም ይቀጥላል።
ያም ሆኖ ያ ሁሉ ሕዝብ ሢያልቅ ከመጤፍ ባለመቁጠር በዝምታ ሢመለከቱ ከቆዩ በኋላ አንድም ቀን እራሡን ሆኖ ያላየነው ጠ/ሚ/ር ተብዬው በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ብሎ ለቅሶ ሊደርሰንና ሊየፅናናን ሲሞክር ባየሁ ጊዜ ከሞታችን ይበልጥ ሢቃ ተናነቀኝ። ይህ ለኔ ስላቅ ነው፤ ከሆነስ ሆነና ሰሞኑን ይሕ ሁሉ ሲጨፈጨፍ የት ነበር? ምናልባትም አልሠማ ይሖን? ይሕ የሚያሣየው እነዚሕ ሰዎች ለኛ ያላቸው ንቀት እስከ ምን እንሆነ ነው። ወይስ ለማፅናናትም የሙት ኮታ ይኖራቸው ይሖን? ከዚሕ በፊት ሺ ያሕል ሠው ገለው አጣሪ ቡድን ተብየው”ተመጣጣኝ ግድያ ነው” ማለቱን ያስታውሷል።
የሆነስ ሆነና እነሡው ዕየገደሉ መልሰው ለቅሶ የሚደርሡን እንዴት አይነት ሹፈት ነው? ሁሉም የሠማው ስለሚሆን ሠውዬው የተናገረው ላይ ትንታኔ መሥጠት ባያስፈልግም ይሕ በሕዝብ ላይ ማቀርሸት መሆኑን ግን አስረግጬ መናገር እፈልጋለሁ። ደግሜ ደጋግሜም እላለሁ ሕወሐት ያለበትን የደም ሒሣብ እሥኪያወራርድ አንተኛም፤ የወገኖቻችን ደም እየተጣራ ከቶም ሊያስተኛን አይችልምና። ሕወሐት ብሔረሰብ ሳይለይ ተራ በተራ እየገደለን ነውና አንድ ላይ ሆነን ከታገልን የማንጥልበት ምንም ምክንያት አይኖርም።
ሞት ለትግራዩ ሕወሐት!

Filed in: Amharic