>

የጨለንቆውን ጭፍጨፋ በማውገዝ በአምቦ ህዝባዊ ዓመጽ ተቀስቅሳል (በወንድወሰን ተክሉ)

በጨለንቆ የ18ንጹሃን በአግዓዚ መጨፍጭፍ ቁጣን ቀሰቀሰ

የጨለንቆውን ጭፍጨፋ በማውገዝ በአምቦ ህዝባዊ ዓመጽ ተቀስቅሳል


በምስራቅ ኦሮሚያ ጨለንቆ በአግዓዚ ሰራዊት የተፈጸመው አሰቃቂ ጭፍጨፋ በኦሮሚያ በተለይም በኦምቦ ህዝባዊ ዓመጽ መቀስቀሱ ተሰማ።
የአግዓዚ ሰራዊት የጨለንቆ ከተማ ነዋሪ የሆኑትን አስራ ስምንት ንጹሃንን በአሰቃቂ ሁኔታ መጨፍጨፉ የአካባቢውን ነዋሪ ክፉኛ ያስቆጣ ሲሆን በአምቦ የመለስተኛ ደረጃ ተማሪዎች ጥቃቱን በማውገዝና ገዳዮቹን ለፍርድ እንዲቀርቡ በመጠየቅ ሰላማዊ ሰልፍ መውጣታቸውን ለማወቅ ተችላል።

በሌላ በኩል ደግሞ ባለፈው ቅዳሜ በትግራይ አዲግራት ዩንቨርሲቲ የተፈጸመውን ብሄር ተኮር ጥቃት በማውገዝ ሰልፍ በወጡት ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ የአግዓዚ ሰራዊት ድብደባ እንደፈጸመም ኢሳት ዘግባል።

በወልዲያ፣ባህርዳርና በጎንደር ዩንቨርሲቲዎች የአዲግራቱን ብሔር ተኮር ጥቃት አውግዘው በተነሱ ተማሪዎች ላይ አግዓዚው አስቀቂ ድብደባ መፈጸሙን እና በርካታ ተማሪዎችም ለህክምና ሆስፒታል እንደገቡ ለማወቅ ተችላል።

በወልዲያ ህዝቡ ከተማሪው ጋር እንደተቀላቀለ የተገለጸ ሲሆን በውጫሌ የከተማው ነዋሪ የብአዴን አርማና የዳሸን ቢራ ማስታወቂያ ከየስፍራው የለቃቀመ ሲሆን አንድ ንብረትነቱ የህወሃት በሆነ ሰላም ባስ ላይ በተወሰደ ጥቃት መኪናውን ከጥቅም ውጪ በማድረግ ሾፌሩን በደሴ ሆስፒታል እንዲተኛ አድርገውታል ይላል ዘገባው።

በባህርዳርና በጎንደር ዩንቨቲ ተማሪዎች ላይ የተፈጸመውን የአግዓዚ ጥቃት በማውገዝ የሁለቱም ከተማ ነዋሪ ዛሬ [ማክሰኞ] ከፍተኛ ዓመጽ ሲያካሄድ የዋለ ሲሆን በመንግስታዊ ተቃማት ላይ እርምጃ በመውሰድ በድንጋይ ሲደበድቡ እንደዋሉ መረዳት ተችላል።

በወለጋ ዩንቨርሲቲ ሻምቡ ካምፓስ በተገደሉት ሁለት የትግራይ ተወላጅ ተማሪዎች ምክንያት ከመቶ በላይ ተማሪዎች በፖሊስና በአግዓዚ ታፍሰው መታሰራቸውን ለማወቅ ሲቻል በርካታ የትግራይ ተወላጅ ተማሪዎችም በየፖሊስ ጣቢያው ተሰብስበው እንዳሉ ተነግራል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ቅዳሜ በአዲግራት ዩንቨርሲቲ በተፈጸመው ብሔር ተኮር ጥቃት ህይወታቸው በአደጋ ላይ ያሉ በመቶ የሚቆጠሩ የኦሮሞና አማራ ተወላጅ ተማሪዎች ክልሉን እና ዩንቨርሲቲውን ለቀው ለመውጣት ያደረጉት ሙከራ በአግዓዚ ሰራዊት አጋጅነት በግድ በየዶርማቸው ታግተው እንዳሉም ለማወቅ ተችላል።

Filed in: Amharic