>

የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! ህወሀት ፈሊጥህን ነቅቶብሀልና ንቃ! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

ህወሀቶቹ ለፈጸሙት ግፍ በደልና ክህደት ሁሉ ነገ ከባድ ዋጋ መክፈላቸው የማይቀርላቸው መሆኑን እየተገነዘቡ መምጣታቸው ጭንቀትና ሥጋት ውስጥ ከተታቸውና እንዳበደ ውሻ አድርጓቸው ባልጠበቅነው ቦታና ሰዓት ሁሉ የትም እየተናከሱ እንደሆነ እያየን እየሰማን ነው፡፡ ከውጤቱ ምንም ሊጠቀሙ እንደማይችሉ እያወቁ በተስፋ መቁረጥ ስሜት እየተገፉ ሕዝብን ለማስቆጣት፣ ለማሳመፅ ሕዝብን በመዝለፍ፣ ልጆቹን በመግደል ትንኮሳ እየፈጸሙ ጫና እያሳደሩና እየገፋፉ ይገኛሉ፡፡

እርግጥ ነው ህወሀቶች ሲባሉ ሲበዛ አቅለ ቀላል መሆናቸውን፣ አርቆና አስፍቶ ማሰብ የሚባል ነገር የማያውቃቸው መሆናቸውን፣ ትንሽ ሲበሉ ጥጋብ የሚሠሩትን አሳጥቶ የሚያሳብዳቸው መሆናቸውን፣ ቅሚያ ንጥቂያ ዝርፊያ በደማቸው ውስጥ ያለ ባሕርያቸው መሆኑን፣ ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ የማይታዩዋቸው ጎጥና ዘር አምላኪዎች መሆናቸውን፣ የአስተሳሰባቸው ማዕከል “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል!” መሆኑን ወዘተረፈ. እናውቃለን፡፡

ይሄንን የህወሀቶችን ሰብእና አስቀድመን የምናውቅ ብንሆንም ቅሉ እነኝህን ችግሮቻቸውን ባስተዋልንባቸው ቁጥር ዘወትር መገረም መደነቃችን ግን ቀርቶ አያውቅም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ እነኝህን ችግሮቻቸውን ልብ በማለትም ልክ ሕፃን ልጅ እጅ ላይ ወይም የአእምሮ ሕመምተኛ እጅ ላይ ያለን ተሰባሪ ዕቃ “አባብሎ በደኅና ለመቀበል መሞከር ነው እንጅ ካልሆነማ ዕቃው ይሰበራል!” በሚል እሳቤ “እነዚህ ሰዎች ፈጽሞ ኃላፊነት የሚሰማቸው ስላልሆኑ ታግሰን ብናሳልፍና ቀስ ብለን አባብለን ሀገራችንን ከእጃቸው ብንቀበል ይሻላል!” ብሎ በመታገሱ በነዚህ 27 ዓመታት ምን ያህል እየተጎዳ፣ ምን ያህል እየተሰቃየ፣ ምን ያህል ፍዳ ሰቆቃ እየቆጠረ፣ ምን ያህል እየተዘረፈ፣ ምን ያህል ብሔራዊ ጥቅሙን እያጣ ታግሶ እንደቆየ ሁላችንም እናውቃለን፡፡

ህወሀቶችም እንዲህ ብለን አስበን አይሆኑ ሆነን፣ የማይቻለውን ሁሉ ታግሰን ችለን እያሳለፍን መሆናችንን አውቀውብንና እንዲህ ማሰባችንም ተስማምቷቸው “ምንም አያመጡም!” በሚል እሳቤ ፈጽሞ ይሆናል ይደረጋል ተብሎ በማይታሰብ መልኩ ፍጹም ኃላፊነት በጎደለው መልኩ ግፍ እየፈጸሙብን ይገኛሉ፡፡ አንዳንዴም ሲበዛብን፣ ሲያንገሸግሸን ወደ ማመፁ ስንሔድ ፍጹም ኃላፊነት የማይሰማቸው መሆናቸውን ሊያሳይላቸው የሚችል ድርጊት በመፈጸም አርፈን ብንቀመጥ እንደሚሻለን ለማሳወቅ ጥረት ሲያደርጉ፣ እኛም በድርጊታቸው እየደነገጥን “ኧረ ይሄ ነገር!” እያልን መልሰን ትተነው ስብስብ በማለት እስከዚህች ቀን ዘልቀናል፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! ህወሀቶቹ ምን ብለን፣ ለምን እንደታገስናቸው ባያውቁ ኖሮ ፈሊጥህ ለውጤት መብቃቱ ምንም የሚያጠራጥር አልነበረም ነበር፡፡ በማወቃቸው ግን ነገሩን እንዳይሆን አድርጎ አበለሻሽቶታል፡፡ ከታሰበው በላይ ምን ያህል ዋጋ እያስከፈለን እንዳለም እያየኸው ነው፡፡ በመሆኑም አባብሎ የመቀበሉ ዘዴ ስለተነቃብን ፈሊጣችን እንደከሸፈና እንደማይሠራ አውቀህ፣ የመጨረሻ እርምጃ አለመውሰዳችን በሀገርና በሕዝብ ላይ እንዳይደርስ የምንፈራውን አደጋ ሊያስቀረው ስላልቻለ የአደጋ ሥጋት (risk) ተጋፍጠን በሕፃኑ ወይም በአእምሮ ሕመምተኛው እጅ ያለውን ተሰባሪ ዕቃ ከዓይን ጥቅሻ በፈጠነ ቅልጥፍና ዘለን ለመንጠቅ ለመውሰድ ከመሞከር ውጭ አማራጭ የለንምና ለዚህ እርምጃ እራስህን አዘጋጅ!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com

 

Filed in: Amharic