>

የአማርኛ ታፔላ ነቀላ በኦሮሚያ (ግርማ ካሳ)

ኦሮሚያ የሁሉም አትዮጵያወያን ነው ሲሉን ነበር እነ ኦቦ ለማ መገርሳ። እኛም እስየው፣ ብራቮ ብለን የሌሎች ማህበረሰባት መብትን ማክበሩን፣ አማርኛን ከኣፋን ኣሮሞ ጋር የክልሉ የስራ ቋንቋ ማድረገን የመሳሰሉ ተግባራዊ ስራዎችን ጠበቅን። ሆኖ የጠበቅነው ሳይሆን ያልጠበቅነው እያየን ነው። በተለያዩ የንግድ ቦታዎች በአማርኛ የተፃፉ ታፔላዎችን መንቀሉን ተያይዘዉታል። በዚህ ምስል ላይ የምታዩት በሰበታ ነው።

ታዲያ ይሄ አማርኛን ጥላቻ ካልሆነ ምን ሊባል ይችላል ? የአማርኛ ታፔላዎች እንዳለ ተነቅለው፣ ኢትዮጵያ በተለይም በኦሮሚያ ፊደል እንደሌላቸው እንደ ኬኒያ፣ ሴነጋል ..ልትመስል ትንሽ ነው የቀራት፤ በላቲን ፊደል አሸብርቃ።

ይገባኛል ላለፉት 25 አመታት የነበረን በሽታ በአንድ ጀንበር መፈወስ አይቻልም። ሆኖም ግን ቢያንስ ከንግግር ያለፈ ትንሽም ቢሆን በተጨባጭ መሰረታዊ ለዉጥ ሊመጣ እንደሚችል ምልክቶች ማየት ነበረብን።

የኦህዴድ ባለስልጣናት ስለአማራን ስለኦሮሞ ትብብር ሲያወሩ ይመስለኛል ትብብር የሚሉት በአማራው ክልል እና በኦሮሚያ ክልል መካከል ነው፤ እንጂ በኦሮሚያ ውስጥ ያሉ ሌሎች ማህበረሰባትን የሚመለከት አይመስለኝም። ለምን ቢባል በኦሮሚያ የሚኖሩ ሌሎች ማሀረሰባት አሁንም መብታቸው እንደተረገጠ ነው። አሁን የመኖር ዋስተናዎች እንደተገፈፈ ነው። አሁንም ፈርተው ነው የሚኖሩት።

Filed in: Amharic