>

ስንት ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች አሉ? (ውብሽት ሙላት)

የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ብዛት በተለያዩ ጊዜያት፤

ቅድመ-ደርግ፥

ብሔሮች፣ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች መኖራቸው ቢታወቅም፣በተለያዩ ገድላት፣ዚና መዋዕላት፣በውጭና በኢትዮጵያዊያን ጸሐፍት ድርሳናት ስለ ብዙዎቹ ቢጻፍም በትክክል ቁጥራቸው አይታወቅም፡፡

በደርግ፥

የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ጥናት ተቋም ጥናት ውጤት ላይ መረዳት እንደሚቻለው 89 ናቸው፡፡ ነገር ግን ጥናቱ 89 ብቻ አለመሆናቸውን ያስረዳል፡፡ ታሪካቸው በአጭሩ የተጻፈው የ75ቱ ብቻ ሲሆን የሌሎቹ ግን ስማቸው ብቻ ተዘርዝሯል፡፡

በሽግግር ወቅት፥

በ1984 ዓ.ም. በወጣው አዋጅ ቁጥር 7/84 ላይ 63 ብቻ ተዘርዝረዋል፡፡

በ1987 ዓ.ም. በተደረገው ሕዝብ ቤት ቆጠራ እና የፌደሬሽን ምክር ቤት

በሕብና ቤት ቆርራው ሪፖርት መሠረት 84 ተቆጥረዋል፡፡

የፌደሬሽን ምክር ቤት መቀመጫ የነበራቸው ደግሞ 67 ብቻ ነበሩ፡፡

ከ1993  ጀምሮ በነበረው የፌደሬሽን ምክር ቤት ደግሞ ወደ 76 ከፍ ያለ ሲሆን፤ በ2008 ዓ.ም ሥራውን የጀመረው የፌደሬሽን ምክር ቤት ደግሞ መቀመጫ ያላቸው 77 ናቸው፡፡

በ1999 ዓ.ም. በተደረገው ሕዝብና ቤት ቆጠራ
በዚህ ጊዜ በተደረገው ቆጠራ ደግሞ 85 ሲሆን በ1987 ላይ ከተጠቀሱት ውስጥ አምስቱ ያልተካተቱ ሲሆን ሌሎች ስድስት ግን ተጨምረዋል፡፡ አምስት “ሞተው” ስድስት “ተወልደዋል” ማለት ነው።

መብታቸውን መልሻለሁ የሚል መንግሥት ያላት፣ የአብዝኃኛው አገራዊ እና መንግሥታዊ መዋቅሮቻችን መሠረታት ብሔር የሆኑባት አገር፤  የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን የምታከብር ነገር ግን ብዛታቸውን እንኳን የማታውቅ  ኢትዮጵያ!!!!!!!

ስንት ብሔሮች፣ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በኢትዮጵያ ይገኛሉ?ቢባል በትክክል ማንም መመለስ የሚችል ያለ አልመሰለኝም፡፡
…….
ጥያቄ ለትህነግ እና አጋፋሪዎቻቸው:-

1. ላለፉት 40 አመታት “ብሄር:ብሄረሰቦች እና ህዝቦች” እያላቹ ስታደርቁን ቆያቹ ምስኪኑንም ህዝብ ውጣ እና ጨፍር እያላቹ ስታንገላቱት ይሀው 25 አመታት አለፉ:: ነገር ግን በኢትዮጵያ ውስጥ ማን “ብሄር” እንደሆነ ማን “ብሄረሰብ” እና ማን “ህዝብ” እንደሆነ እስካሁን ግልፅ አላደረጋቹህም:: መመዘኛቹም ምን እንደሆነ አትናገሩም ግን ግልፅነት ስላልለመደባቹ አንጠብቅም:: በያመቱ በግድ ስለምታስጨፍሩት ምስኪን ህዝብ ስትሉ ግን ማን “ብሄር” ማን “ብሄረሰብ” እና ማን “ህዝብ” እንደሆነ እንድታስታውቁን ስንል በ እለተ “ብሄር/ብሄረሰቦች/ህዝቦች” ቀን እንጠይቃለን:: በየትኛው መስፈርት እንደሆነ ሀረሪ “ክልል” ተሰጥቶት ለምሳሌ ሲዳማ ወይንም ወላይታ “ክልል” ያልተሰጣቸው? ወይንስ ሁሉም “ብሄሮች” እኩል ቢሆኑም አንዳንዶቹ የበለጠ እኩል ናቸው?

2. መቼስ አምባገነን መንግስት እንኳንስ የ “ብሄር/ብሄረሰብ/ህዝብ” ቁጥር አይደለም ህዝቡ የሚተነፍሰውን አየር እና ንፋስ በ 1 ለ 5 መዋቅርም ይሁን ሌላ ይቆጣጠራል በጥብቅ ያውቃል:: እንግዲህ ጥርሱን በ “ብሄር/ብሄረሰቦች/ህዝቦች” ፖለቲካ የነቀለና ላለፉት 27 አመታት በፍፁም አምባገነንነት የተቆጣጠረ “መንግስት”: እስከመቼ ድረስ አሁንም በ ኢትዮጵያ ውስጥ ከ 80 በላይ “ብሄር/ብሄረሰቦች/ህዝቦች” አሉ እያሉ ግን ትክክለኛ ብዛታቸውን ሳትነግሩን የምትቆዩት? ትህነጎች እና አጋሮቻቸው እባካቹ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን “ብሄር/ብሄረሰቦች/ህዝቦች” ትክክለኛ ቁጥራቸውን ንገሩን እስከመቼ ትክክለኛ ቁጥራቸውን ትደብቁናላቹ?

3. በመጨረሻ ከተቀላቀለ “ብሄር/ብሄረሰቦች/ህዝቦች” የተወለዱትን መቼ ነው እንደሰው ቆጥራቹ በግድ አንዱን ወገናቸቸን መርጠው ሌላውን ክደው ሳይሆን እንደሰው ኢትዮጵያዊ እንዲሆኑ የምትፈቅዱላቸው?

መቼስ በታሪክ አምባገነን በመሳሪያ ተሸንፎ ካልተንበረከከ በስተቀር የህዝብን ጥያቄ እንደማይሰማ አውቃለሁ ግን በቃ ለማስታወስ ያህል ነው::

የአፓርታይድ ስርአት አስፍሮ እኩልነት አመጣን ብሎ ህዝብን በግድ ወይንም በጥቅማጥቅም እያስጨፈሩ በህዝብ ማላገጥ ምን ቢዘገይ አንድ ቀን ያስጠይቃል::

The post above is the question I have for TPLFites when they celebrate “ብሄር/ብሄረሰቦች/ህዝቦች” day though TPLF doesn’t know their number yet after 27 years in power and talking about “nations/nationalities/peoples” for the past 40 years

Filed in: Amharic