>

 "..እየሩሳሌም የአለም ሙስሊሞች ቀይ መስመር ናት!"  ፕሬዚደንት ኤርዶጋን

በአዋዜ ትዩብ

የቱርኩ ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን “እንዳይሆን!የሆነ እንደሆን “አሉ  በቴሌቭዥን በተላለፈ የፓርቲ አባላቶቻቸው ፊት ለሀገሪቱ  ፓርላማ ባሰሙት ንግግር፤ቀጥታ ለአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕና ለእስራኤል የተነጣጠረ ንግግር ነበር።
“እንዳይሆን፤የሆነ እንደሆን ግን የአለም ሙስሊሞች የጋራ ህብረት በጉዳዩ ላይ እንዲነቃነቅ አደርጋለሁ!”ብለዋል። ጭብጨባው ልዩ ነበር።ቱርክ የአለም ሙስሊሞች ምክር ቤት ሊቀመንበር ናት።

“ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ፦እየሩሳሌም የሙስሊሞች ቀይ መስመር ናት! ይህን ለአፍታም አይርሱ ያሉት ፕሬዚደንት ኤርዶጋን ለእስራኤል ደግሞ ከአንቺ ጋር ዲፕሎማቲክ ግንኙነት እስከመበጠስ ድረስ እንሄዳለን ሲሉ ክፉኛ አስጠንቀዋል።

      ትራምፕ ልዕለ ኅያሏ አገራቸው ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ቅድስቲቱንከተማ እንደ አይሁዳዊቷ አገር በመርህ ደረጃ ከማወቅ ባሻገር በዕውቅናዋ መሰረት በቴልአቪቭ የሚገኘውን ኤምባሲዋን ወደ እየሩሳሌም እንደምታዞር ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።/ዝውውሩ ከአሁን በኊላ 6 ወር ሊፈጅ ይችላል።

            እስራኤል ከጠቅላይ ሚኒስትሯ ቢሮ የመነጨ ምላሽ እስካሁን አልሰጠችም ገና።ይሁንና የትምህርት ሚኒስትሩ ናፍታሊ ቤኔት ሲመልሱ”እንዳለመታደል ሆኖ ኤርዶጋን እስራኤልን ለማጥቃት አንድም አጋጣሚ አታልፋቸውም “አሉ በፅሁፍ ባወጡት መግለጫቸው።ሲቀጥሉም” እየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማዋ መሆኗን እንዲታወቅላት ማድረግን ጨምሮ  ዓላማዎቿን ለማሳካት መራመድ አለባት “ካሉ በኊላ ሲደመድሙ፦”ነቃፊዎች ሁሌም ይኖራሉ፤ቢሆንም ከኤርዶጋን እሺታ ይልቅ የተዋሀደች እየሩሳሌም ብትኖረን ይምርረጣል”ብለዋል።

   የእስራኤል የትራንስፖርትና ኢንተሊጀንስ ሚኒስትር እስራኤል ካፅ በበኩላቸው “ቱርክ አታዘንም “ይላሉ።አክለውም “ለ3ሺ ዓመታት የአይሁዳውያን ከተማ የነበረችውን እየሩሳሌምን በእስራኤል መናገሻ ከተማነቷን የማወቅ ያህል ታሪካዊ እርማትና ፍትህ የለም”ካሉ በኃላ ሲያሳርጉ እንዲህ ብለዋል፦” የሱልጣናትና የኦቶማን ዘመን ካበቃለት መቶ ዓመት አስቆጥሯል።”

Filed in: Amharic