>
5:13 pm - Tuesday April 19, 2816

አክሱምን ታዘብኳት (በዕውቀቱ ሥዩም)

ይህን ጽሑፍ በአዲሱ መጽሐፌ (ከአሚን ባሻገር) ሁለተኛውን ምዕራፍ ሰጥቼው ነበር። ለአታሚዎች ልስጥ ስሄድ ደመነፍሴ እንዳስቀረው ነገረኝ፤ እየሄድኩኝ ገንጥየ አወጣሁት። ደመነፍስ ማለት ሌላ አይደለም፤ ባጭሩ ምክንያታዊ አስተሳሰብ ማለት ነው። ዘፋኞች የሙዚቃ አልበም ያሳትማሉ፤ ሌላ ጊዜ ነጠላ ዜማ ይለቃሉ። እኛ ደግሞ መጽሐፍ አሳትመን ሌላ ጊዜ መጣጥፍ እንለቃለን። መጽሐፍና ሙዚቃ አንድ የሚያደርጋቸው በአዟሪዎች መሸጣቸው ሲሆን የሚለያዩት ደግሞ አንዱ በዓይን ሌላው በጆሮ መግባታቸው ነው።
አክሱምን የምጎበኝበት ምክንያት ሁለት ነው። የመጀመሪያው ለ1700 ዓመታት አንገቱን ገትሮ ከቀይ ባሕር እስከ ሕንድ ውቅያኖስ አላፊ አግዳሚውን ሲታዘብ የኖረውን ሐውልት ለመዳሰስ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ስለአክሱም ሲወራ አስም እንዳይሆንብኝ ነው።
ጥያራው ለማረፍ ከፍታውን እየቀነሰ ነው። ከሰማይ ላይ ሐውልቱን አየሁት፤ ከወንድሞቹ ጋር ቁሟል። በአውሮፕላኑ በቀኝ መስኮት በምስራቅ በኩል አማተርኩ። አውሮፕላኑ መሬት ለመንካት በግምት 30 ሜትር እስከሚቀረው ድረስ ከአድማስ ወዲያ ወዲያ ማዶ እስከ ቀይ ባሕር ድረስ ምንም የሚጋርድ ተራራ የለም። ወዲያው አንድ ምስጢር ተገለጠልኝ። ለጓደኛዬ ገብረኪዳን እንደደረስኩ ከመደወሌ በፊት ሐውልቱ ጋር መድረስ እንዳለብኝ ወሰንኩ።
ከኤርፖርቱ ወጥቼ አንዱን ባለታክሲ ሐውልቱ ጋር እንዲያደርሰኝ ጠየኩት። ” ዋይ ኣብዚ ታክሲ ለቱሪስት ኢዩ፤ መንገዱን ተሻገርና ባጃጅ ፈልግ” አለኝ። ቱሪስት አለመሆኔን እንዴት አወቀ እያልኩ ስሄድ ወዲያው ቱሪስት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ተረዳሁ፤ አብረውኝ ከአዲስ አበባ የመጡ ሁለት ፈረንጆችን አስገብቶ የታክሲውን ሞተር ሲያስነሳ አየሁት። ብዙ ሰው የሚያስበው እንደሹፌሩ ነው። ቱሪስት ማለት ፈረንጅ ነው፤ የጥቁር ቱሪስት የለም። ጥቁር አገር ለቆ ከሄደ ስደተኛ እንጂ ጎብኝ አይደለም።
ሐውልቱ ጋር ደረስኩ። ተጠግቼ አየሁት። እሱ ግን እኔን ሳይሆን አድማሱን ተሻግሮ ይመለከታል። ከእያንዳንዱ በር እና መስኮት ቅርጽ ስር ወጣ ወጣ ያሉ በዝናብና በፀሐይ ምክንያት የተሸራረፉ ጉጠት መሰል በግራና በቀኝ በኩል ተቀርፀውለታል። መወጣጫ ደረጃ እንደነበሩ ገመትኩ። ደረጃዎቹ እስከ ሐውልቱ ጫፍ መሰደራቸው ግምቴን አፀናው። የጥንት ቻይናዎች ቴሌስኮፕ ይሰሩ ነበረ። የጥንት አክሱሞችም ቴሌስኮፑን ገዝተው ሐውልቱ ላይ ተንጠላጥለው ከላይኛው ቀይ ባሕር እስከ ሕንድ ውቅያኖስ ይመለከቱ ነበር ማለት ነው። በሐውልቱ አናት በግራና በቀኝ ገባ ገባ ያሉት ደግሞ የቴሌስኮፑ ማስቀመጫ መሆናቸው ነው። በዚህ ዘዴ ይመስላል የአባ ፍሬምናጦስ መርከብ ቀይ ባሕር ላይ ስትንጎማለል ከአክሱም ላይ እንድትታገት የተወሰነባት።
ይህ ተግባር ግን አልቀጠለም። በተለይ በጣም ረጅሙ ሐውልት በ550 ዓም ከወደቀ በሗላ ቅዱስ ያሬድና ከሶርያ የመጡት ዘጠኙ ቅዱሳን ተመካክረው የአፄ ካሌብን ልጅ አፄ ገብረመስቀልን ከእንግዲህ በሗላ መስራት ያለበት ሐውልት ሳይሆን ቤተመቅደስ እንዲሆን እንዳሳመኑት የቅዱስ ያሬድ ዜና መዋዕል ይተርካል። በዚህም አክሱም ጺዮን ቤተከርስቲያን፣ ጣና ቂርቆስ ገዳም እና ደቡብ ጎንደር የሚገኘው ዙር አምባ ገዳም ተገነቡ።
ወደ አክሱም ሙዚየም አመራሁ። በስተቀኝ በኩል ካለው መስታወት ውስጥ እንዴት አጠር ቀጠን ያለች ሽመል ተቀምጣለች። አስጐብኝው ሕሉፍን ምንድን ናት ስለው “ቅዱስ ያሬድ ዜማዎቹን ለመጻፍ የተጠቀመበት ብዕር ነው ” አለኝ። እውነት ከሆነ ሽመሏ እንደ ብዕር ብቻ ሳይሆን እንደ ዱላም ታገለግል ነበር ማለት ነው።
ቅዱስ ያሬድ ድንቅ ሰው ነው። ፕሮፌሰር አየለ በከሪ ‘Ethiopic, An African Writing System: Its History and Principles’ በሚለው ድንቅ መጽሐፋቸው “ቅዱስ ያሬድ በዓለም ዜማን በጽሑፍ ያስቀመጠ የመጀመሪያው ሰው” ብለውታል። Gebrella Scelta ደግሞ The Comparative Origin and Writing Of Geez writing system of Ethiopia በሚለው መመረቂያ ጽሑፏ ላይ “ሀበሾች ፊደላትን የቀረጹት ተፈጥሮን እያዩ ነው” ትላለች። በዚህም “ዐ”ን ከዓይን ቅርጽ፣ “በ”ን ከቤት ቅርጽ፣ “መ”ን ከማዕበል ቅርጽ ፣”ገ”ን ከግመል ቅርጽ ነው ትላለች። ፊደሎቹ የተፈጠሩት ከቅዱስ ያሬድ በፊት ቢሆንም ያሬድ አንዳንዶቹን አሻሽሏቸዋል ትላለች። ግደይ በላይ 1992 ባሳተሙት “The Ethiopian Civilization” በተሰኘ መጽሐፋቸው ቅዱስ ያሬድ አምስት ድርሳናት ማለትም ድጓ፣ ጾመድጓ፣ ዝማሬ፣ ምዕራፍ እና መዋሲትን እንደደረሰ፤ እያንዳንዳቸውን በግዕዝ በአዝልና በአራራይ ዜማ እንደሚያንቆረቁረው ጽፈዋል። በዚሁ መጽሐፋቸው ለእያንዳንዱ ዜማ የዜማ ምልክት ማለትም ይዘት፣ ደረት፣ ርክርክ፣ ድፋት፣ ጭረት፣ ቅናት፣ ሂደት፣ ቁርጥ፣ ድርስ፣ አንብር እንዳስቀመጠላቸው አሳይተዋል። ይህንኑ እውነት “The Origin of Black Music” በሚለው መጽሐፋቸው ዶክተር አሸናፊ ከበደም አስነብበዋል።
በተለይ የዜማ ምልክቶቹን ስመለከት የአማርኛ ቃላት መሰሉኝ። ጓደኛዬ ገብረኪዳንም እነዚህ ቃላት አብዛሀኛዎቹ በትግርኛ እንደማይታወቁ ነገረኝ። ቅዱስ ያሬድ ግዕዝን( ግዕዝ ራሱ ገዥ ከሚለው ቃል የወጣ ነው) ወደ አማርኛ ማስረፅ የጀመረ የመጀመሪያው ሰው እንደሆነ ተረዳሁ። እርግጥ ነው ስም ማንነትን ይገልፃል፤ ማን ነህ የሚለውን ባይገልፅም። ለምሳሌ አንዱን ሙስሊም በስሙ ሙስሊም እንደሆነ ትገምታለህ። አንድ ፈረንጅ ስሙ ላይ ቪች ወይም ኮቭ የሚል ቅጥያ ካለው ከራሺያ ወይም ከምሥራቅ አውሮፓ መሆኑን መጠርጠር አለብህ። እንዲሁም ያሬድ የሚለውን ስም ከትግሬዎች ይልቅ አማራዎች ሲጠቀሙበት እያለሁ። ለዚህ ምክንያቱ ሁለት ነው። አንድም አማራዎች ከትግሬዎች በላይ ያሬድን ይወዱታል፤ አሊያም ደግሞ ያሬድ ራሱ የነሱ ነው። ግን ጣና ቂርቆስ ሦስት ዓመት መቀመጡ፣ ጋይንት ዙር አምባ ገዳም አራት ዓመት ማስተማሩ ፣ አሰከ ዕድሜው ፍጻሜ ድረስ ሰሜን ተራራ መኖሩ፣ በ66 ዓመቱ ሲያርፍ ስርአተ ቀብሩም እዚያው መፈፀሙ ያሬድ ከመረቦቹ ይልቅ የአባዮቹ ይመስላል።
ከአክሱም ሙዚየም እንደወጣን ሕሉፍ “ቀጥለን የአክሱም ነገሥታት የመቃብር ሥፍራን እንጎበኛለን” አለ ። ከሐውልቱ ጀርባ ራቅ ብሎ የሚገኘውን የመቃብር ሥፍራ እየጎበኘን እያለ አስጎብኝው ” ይህ ቦታ በጥንት ጊዜ ነፋስ ማውጫ እንደሚባል ተመራማሪዎች አረጋግጠዋል” አለ። ትክክል ነው፤ በ1959 በቦታው ቁፋሮ ያካሄደው እውቁ የፈረንሳይ አርኪዮሎጂስት Henry De Contenson ቦታውን ካገኘ በሗላ የጥንት ስሙም “ነፋስ ማውጫ” እንደሚባል አረጋግጧል፤ ነፋስ ማውጫ። ከመቃብር ቦታው ወጥተን ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ስንሄድ አንድ የፈራረሰ ክብ ግንብ ጋር ደረስን ።የግንቡ ድንጋዮች መካከል ክፍተት አለ። ይሄውም ግንቡ ከመፍረሱ በፊት መቃጠሉን ያሳያል። ሕሉፍ ” ይህ በ950 ዓም ዮዲት ጉዲት ያፈረሰችው ቤተክርስቲያን ነው፤ እርጉም ናት። እንዴት ሰው ቤተክርስቲያን ያቃጥላል” አለ። ከጎብኚዎች አንዱ ” ታዲያ ነገስታቱ ወዴት ሄዱ” ብሎ ሕሉፍን ጠየቀው። “እነሱማ ሸሹ፤እንደገናም አልተመለሱም ” ሕሉፍ መለሰ። በ10ኛዉ ክፍለዘመን አጋማሽ በቦታው የነበረ የአረብ ታሪክ ፀሐፊ ኢብን ሀውካል በሴት የሚመራ ወራሪ ጦር የአክሱሙን ንጉሥ አፄ ድል ናዖድን አነደገደለ፣ የከተማዋን ሕንጻዎች እንዳፈራረሰ፣ ቤተክርስቲያናትን እንዳቃጠለ Stuart Munro Hay — Aksum
An African Civilisation of Late Antiquity በተሰኘው ድንቅ መጽሐፍ አስፍሯል። የትግራዩ የታሪክ ተመራማሪ ግደይ በላይ ከሰላሳ ዓመት በፊት በፃፉት Ethiopian Civilization መጽሐፍ ላይ አክሱም በ950 ዓም ስትሸነፍ ሕዝቡ በደቡብ በኩል ወደተራራማ ሀገር እንደሸሹ ገልጿል። የተቃጠሉትም ቤተክርስቲያናት በተመሳሳይ ጊዜ እንደሆነ አብራርቷል። በዚህም ሴቲቱ ለየመኑ የሳባ ንጉሥ ስጦታ እንደላከች Munro Hay ጽፏል። ሪቻርድ ፓንክረስት ደግሞ በመጀመሪያው ሚሌኒየም አክሱም ላይ ይኖሩ የነበሩት ProtoAmhara እና ProtoTigrean ሕዝቦች ናቸው ብለዋል። እኔ ሳይኮሎጂ ስማር ‘በማንኛውም ህብረተሰብ ውስጥ አንድ መሪ የሆነ አስተሳሰብ ወይም ማንነት አለ’ የሚል ጽንሰሃሳብ አለ። ስለዚህ እስከ አሥረኛው ክፍለዘመን ድረስ አክሱም ላይ መሪ አስተሳሰብ ወይም መሪ ማንነት የነበረው የየትኛው ነው ? የአማራ ወይስ የትግሬ ? እስኪ አንለይ፤ እንመርምር።
(ሀ). የሸዋው ይኩኖአምላክ የላስታውን ነአኩቶለአብን “ሥልጣን ልቀቅ፤ እኔ የመጨረሻውን የአክሱሙን ንጉሥ የድል ናዖድን መንግሥት የማስቀጥል የሰለሞን ዘር ነኝ” የሚል ደብዳቤ እንደላከለት እንግሊዛዊው Monro Hay በመጽሐፉ አስነብቧል። ግን በዚህ ወቅት ማለትም በ13ኛው ክፍለዘመን ” እኔም ሥልጣን ይገባኛል የሚል ድምፅ ከትግሬዎች አልወጣም።
(ለ). ትግሬዎች ለሌላ ሰው የማይናገሯት አንዲት ባህል አለቻቸው። “አስወድቀኒ!!” አንዲት ትግሬ አንዱን ወንድ አስወድቀኒ ካለች ጥግህን ፈልገህ መለጥለጥ ነው፤ መዋሰብ ነው። ይሄ የትግሬዎች ባህል አሁን በየድራማው እንደምናየው የዘበኛ እና የገረድ አይነት ፍቅር ነው። ባጭሩ “አስወድቀኒ” ማለቷ ብ*ኝ ማለቷ ነው። ገብረኪዳን እንደነገረኝ አንዱ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ መምህር “አስወድቀኒ ከህንዶቹ kama sutura ስለማያንስ ይፋ እናርገውና Guinness Book ላይ እናስመዝግብ” እያለ ነው አሉ። እንዲህ አይነት የገረድና የዘበኛን የፍቅር ሥነልቦና ባህሉ አድርጎ የያዘ ማህበረሰብ እንዴት የአክሱም ነገሥታት ወራሽ ነኝ ማለት ይደፍራል?
(ሐ). ሳባ የሚለው ስም። አንዲት ሴት ስሟ “ሳባ” ከሆነ ትግሬ የመሆን ዕድሏ ከ95% በላይ ነው። ለመሆኑ ይህ ስም ከየት መጣ? የመን ውስጥ ከነበረ ሳባ ከሚባል ሀገር!! እስከአሁን ድረስ ከምፅዋ ወደብ በስተደቡብ የየመን ነጋዴዎች ማረፊያ ሳባ የሚባል ቦታ አለ። ሲሳይ ለጋሃሬ የሚባል ጓደኛዬ ድሬዳዋ እንድመጣ ጋብዛኝ ነበር። ድሬዳዋ ገንዳ ቆሬ፣ ኮኔል፣ ከዚራ፣ ጎሮ፣ ቀፊራ፣ ሳቢያን የሚባሉ ሠፈሮች አሏት። ለመሆኑ ሳቢያን ማለት ምንድን ነው ብየ ሲሳይ ለጋሀሬን ጠየኩት ። እሱም “የመኖች ናቸው የሰየሙት።እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ እዚህ አካባቢ ነበሩ። እነሱ ሲሄዱ ስማቸውን ትተውልን ሄዱ ። የግመል ማሰሪያቸውን ሜዳ ኳስ ሜዳ አድርገን ይሄው ሳቢያን ወይም ሳባውያን ሜዳ እንለዋለን ” አለኝ። ማክዳ ቀይ ባህርን ተሻግራ የመንን ወይም የሳባውያንን አገር ስላስገበረች የነሱም ገዥ መሆኗን ለማሳየት “ንግሥተ ሳባ” ትባላለች እንጂ ” ንግሥት ሳባ” ተብላ አታውቅም። ዮዲት ጉዲትም የአክሱሙን ድል ናዖድን ካሸነፈች በሗላ የመን ላለው የሳባ ንጉሥ ስጦታ የላከችው አክሱም ያሉት የሳባ ሰዎች(የአሁኖቹ ትግሬዎች) ቢያንስ ቢያንስ በስለላ ሰለረዷት ነው ብሎ ማሰብ ይቻላል። ለዚህም ነው የአክሱሙ ጦርነቱ ባጭሩ የተጠናቀቀው። ለዚህም ነው ዮዲት ጉዲት ከተገደለች በሗላ “ሀገራችን በከሐዲዎች ተወሯል” ብለው የአክሱም ነገሥታት ወደ አክሱም ሀገራቸው መመለሱን ትተው ሸዋ ላይ የቀሩት።
(መ). አማራዎች ሲጨፍሩ ፊትለፊት እየተያዩ ነው። ልክ በማህሌት ሰዓት እንደሚታየው ዝማሬ። ትግሬዎች ሲጨፍሩ ግን ክብ ሰርተው ነው። በአንትሮፖሎጂ ሳይንስ መሠረት ፊትለፊት መጨፈር የጨፋሪዎቹ ሀገር ማንነት፣በራስ መተማመን፣ ስብዕና የራሳቸው እንደሆነ ያሳያል። ክብ ሰርቶ መጨፈር ግን መሃል ያለውን እያጀቡ ነው የሚሆነው። በዚህም ክብ ሰርተው የሚጨፍሩ ጨፋሪዎች ሁለተኛነታቸውን፣ ስደተኝነታቸውን ወይም መጤነታቸውን ያሳያል።
(ሠ). “አፄ ዮሐንስ” በሚለው የማሞ ውድነህ መጽሐፍ ላይ አፄ ዮሐንስ “እኔ የማወራው በአማርኛ ነው ምክንያቱም የጥንት አክሱማውያን ቛንቛ አማርኛ ስለሆነ ማለታቸው።
(ረ). መለስ ባንድ ወቅት አረብ ሀገራትን ሲጎበኝ “እኔ ‘ኮ የመናዊ ነኝ” ማለቱ።
(ሰ). አሁንም መለስ “እኔ ወርቅ ከሆነ ሕዝብ ነው የተገኘሁት” ብሎ የአክሱም ሐውልት ከሮም እንዳይመለስ ወይም ግዴለሽነቱን ለማሳየት ግን “የአክሱም ሐውልት ለወላይታ ምኑ ነው” ማለቱ።
(ረ). ልጅ እያሱ በ1909 የመስቀል ዕለት እዚያው የደመራው ቦታ እሱም ፓትርያርኩም እና መሳፍንቱም ባሉበት የተነበበው ክስ፤ የልጅ ኢያሱን “ወንጀሎች” ይዘረዝርና መጨረሻ ላይ ” ከቀዳማዊ ምኒልክ እስከ ዳግማዊ ምኒልክ ያለውን የሥልጣን ተዋረድ ሊያፈርስ” የሚል ጽሑፍ መኖሩ ።
አክሱም የአማራዎች ጥንተ ርስት እንደነበረች ያመለክታል።
አጠቃላይ ሰለ ቀደምት አክሱማውያን ከአሁኖቹ አማራዎች ይልቅ የአሁኖቹ ትግሬዎች የተሻለ እንደሚያውቁ ያሳያል። ግን እውነቱ ተደብቋል።
አስጎብኛችንን ሕሉፍን ተሰናብቼ ገብረኪዳን ጋር ወደተቀጣጠርንበት ቦታ ለመድረስ ባጃጅ ያዝኩ። ጥሩ ነገሩ አክሱም ላይ ያሉ ታሪካዊ ቦታዎች በሚገባ ተይዘዋል። ይህን እያሰብኩ ሳለ የእንጦጦው ትዝ አለኝ። የእንጦጦ ሙዚየም። ባንድ ወቅት ዮሐንስ ሞላ ጋር ወደዚያው ሄደን ነበር። የእንጦጦ ታሪክ የሚጀምረው ከአፄ ምኒልክ ጀምሮ እንደሆነ ለማስመሰል የተለፋ ይመስላል። የአፄ ምኒልክ አልባሳት፣ አልጋ፣ አድዋ የተዋጉበት ጦር መሣሪያ፣ አድዋ የዘመተው ነጋሪት፣ የእቴጌ ጣይቱ ልብስ፣ ድስት ጠባቧ የእንጦጦ ሙዚየም ውስጥ ተደርድረዋል።ከሙዚዬም ውጭ የዛሬ 600 ዓመት አፄ ዳዊት ያሠሩት ዋሻ ከዚያም በሗላ የአፄ ልብነድንግልን የቤተመንግስት መሠረት አየነው። ደህና አጥር እንኳ የለውም። አስጐብኝው እንደነገረን ይህን ቦታ መንከባከብ አማራው “ለካ ከጥንትም ጀምሮ ከማንም በፊት የአባቶቼ ነው” ብሎ ያስባል ተብሎ ይፈራል።
ገብረኪዳን ጋር ተገናኘን። ወደ አንድ ሆቴል ለምሳ አመራን። ምሳ አዘን እንደተቀመጥን ከፊትለፊታችን አስተናጋጇ አነደቮሊቦል ኳስ ካበጠው ገንፎ በትንሽ በትንሹ በእጇ ስትቆራርጥ አየኋት። በአንድ አጇ የተቆራረጡትን ገንፎዎች በሌላኛው ደግሞ ወጥ በትንሽ ሳህን እና ከወስፌ ረዘም ረዘም ያሉ ሁለት እንጨቶች ይዛ መጥታ ከጎናችን ለተቀመጠው ሰው አቀረበችለት። ሰውዬውም በእንጨቶቹ የተቆራረጡትን ገንፎዎች ወጋ አድርጎ እያነሳ በወጡ እያጠቀሰ ሲበላ አየሁ። ገብረኪዳን “በወቄ ምን ታፈጣለህ ከፈለክ አንድ ጥህሎ እንጨምር እንዴ ” አለኝ። ይሄ ምግብ ስሙ ጥህሎ ነው። ትግሬዎች አማራዎችን አምሐሩ ብለው እንደሚጠሩ ሁሉ ጣልያኖችን ደግሞ ጣህሎ ብለው ነው የሚጠሯቸው። የዚህ ምግብ ስምም የመጣው በዚህ አይነት ነው፤ “እንደ ጣልያን” ለማለት ፈልገው ነው። አስመራ ላይ ጣልያኖች መኮረኒ በሹካ ሲበሉ አይተው ይሄው አክሱም ላይ ገንፎ በወስፌ እንጨት እየበሉ ነው። ጥሩ ነው ዘመናዊነት። ግን በደንብ ኮፒ ፔስት አልተደረገም።
ስንት የታሪክ ትዝታ የያዘች አክሱም ለኔ ግን ትዝብትን አተረፈች።

Filed in: Amharic