>

የኡስታዝ አቡበከር አህመድ የእስር ሁኔታና የዛሬ የፍርድ ቤት ውሎ (በአቡ ዳውድ ኡስማን)

ኡስታዝ አቡበከር አህመድ በጨለማ ክፍል እንዲታሰሩ መደረጉ ተሰማ

አቡ ዳውድ ኡስማን

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በሃሰት በሽብርተኝነት ተወንጅለው በእስር የሚገኙት ኮሚቴዎቻችንን የማረሚያ ቤቱ አስተዳር ሆን ብሎ የማሸማቀቅ እና የማዋከብ ተግባር እየፈፀመባቸው እንደሚገኝ መዘገባችን ይታወቃል::

በማረሚያ ቤቱ ከሚገኙ ህግ ታራሚዎች እና እስረኞች በተለየ መልኩ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በኮሚቴዎቻችን አመራሮች እና አብረዋቸው በታሰሩት ወንድሞች ላይ ትኩረት በማድረግ አቃቂር የ መፈለግ እና ባገኙትም ነገር ጉዳዩን በማግነን ለማሸማቀቅ እና ለማንገላታት የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር አቶ አምባዬ እና የደህንነት ሃላፊ አቶ ኤርሚያስ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸወ የተገለፀ ሲሆን ሲዝቱባቸው በነበረው መሰረትም የህዝበ ሙስሊሙን መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑትን ኡስታዝ አቡበከር አህመድን በጨለማ ክፍል ውስጥ እንዲታሰሩ መደረጉን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

በኮሚቴዎቻን እና በወንድሞቻችን ላይ ልዩ ክትትል በማድረግ በጨለማ ክፍ ውስጥ እንዲሰቃዩ ለማድረግ ከበላይ የደህንንት አካላቶች ትዕዛዝ የተላለፈ ሲሆን ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ድንገተኛ ፍተሸ በማድረግ ማንኛው እስረኛ ጠያቂዎች ሊሰጡት የሚችሉትን ገንዘብ ይዛችሁ ተገኝታቹሃል በሚል ኡስታዝ አቡበከር አህመድን እና ሼህ መከተ ሞሄን የማስፈራራት እና ቃላቸውን እንዲሰጡ የማድረግ እንቅስቃሴ ሲየደርጉባቸው ቆይተዋል፡፡በትላንትናው ዕለት ሃሙስም ኡስታዝ አቡበከር አህመድን በጨለማ ክፍል ውስጥ እንዲታሰር ማድረገቻውን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

ከሌላ እስረኞች በተለየ ሁኔታ ኮሚቴውን የማዋከቡ እና በጨለማ ቤት ለመቅጣት የማስፈራቱ ድርጊታቸው ህገ ወጥ መሆኑን ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ለማረሚያ ቤቱ ደህንነት ሃላፊዎች ሲያሳስቡ ቢቆዩም የማረሚያ ቤቱ ሃላፊዎች ግን ኡታስዝ አቡበከርን በጨለማ ክፍል ውስጥ እንዲታሰር ማድረጋቸው ታውቋል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከህግ እና ክፍርድ ቤቱ ተዕዛዝ ሁሉ የበላይ በሆኑ የደህንነት ሃይሎች በኮሚቴዎቻችን አመራሮች ላይ እና በተወሰኑ ወንድሞች ላይ እየተደረገ ባለው ጥብቅ ክትትል እና የዚህ መሰሉ የጨለማ ቤት ቅጣት የሚፈፀም ከሆነ ኮሚቴዎቸችን ለፍርድ ቤቱ እያቀረቡ የሚገኙትን የመከላከያ ምስክር እስከማቆም ሊደርሱ እንደሚችሉ ታውቋል፡፡ ህግ ተፅፎ ባለበት ሃገር ህጉ እየተጣሰ ንፁሃን እንዲንገላቱ መደረጉ የፍርድ ቤቱን ሚና ከቁብ የማያስገባ መሆኑን የሚያረጋግጥ በመሆኑ በችሎቱ የመቀጠሉ ሁኔታ አጠያያቂ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡

ሼህ መከተ ሞሄ እና ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ላይ በጨለማ ክፍል አስገብተው እንደሚቀጧቸው የማረሚያ ቤቱ ሃላፊዎች ሲዝቱባቸው የቆዩ ሲሆን ዛቻቸውን በተግባር በመለወጥ በጨለማ ክፍል ውስጥ እንዳስገቧቸው ታውቋል፡፡ኡስታዝ አቡበከር አህመድ እየተፈጸመባቸው የሚገኘውን ህገ ወጥ ተግባር ለፍርድ ቤቱ ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ኡስታዝ ሃሰን አሊ ለኮሚቴዎቻችን የመከላከያ ምስክር ቃላቸውን ለፍርድ ቤቱ አሰሙ

አቡ ዳውድ ኡስማን

በኡስታዝ አቡበከር አህመድ የክስ መዝገብ ውስጥ በ 14ኛነት ተከሰው የነበረው ኡስታዝ ሃሰን አሊ በዛሬው ጁምአ ግንቦት 29 በዋለው ችሎት ለኮሚቴዎቻችን የመከላከያ ምስክርነታቸውን ለፍርድ ቤቱ አሰምተዋል፡፡

ኡስታዝ ሃሰን አሊ ከኮሚቴዎቻችን ጋር በማዕከላዊ፣በቃሊቲ እና በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በእስር ከፍተኛ ስቃይ አብረው ያሳለፉ ሲሆን የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ታህሳስ 3 በዋለው ችሎት አቃቤ ህጉ ካቀረበባቸው ክስ ነፃ ናቸው ሲል ከእስር መፈታታቸው የሚታወስ ነው፡፡ ከእስር ከተፈቱም ቡሃላ አቃቤ ህጉ ይግባኝ ጠይቆባቸው የነበረ ቢሆንም በራሱ ጊዜ ይግባገኙን ማንሳቱን አሳወቆ ነበር፡፡

ኡስታዝ ሃሰን አሊ አቃቂ ቃሊቲ በሚገኘው 08 አደራሽ ውስጥ በሚሰየመው ችሎት በመገኘት ለኮሚቴዎቻችን የመከላከያ የምስክር ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡

Filed in: Amharic