>

የአቦይና-ራዕይ ቡድኖች በመቀለ ባደረጉት ጨዋታ በአቻ ውጤት ሲጠናቅቁ  ኦህዴድና-ብአዴን 1ኛና 2ኛ ሆነው ወደ ቀጣዮ ዙር አልፈዋል (ስዩም ተሾመ)

 በአንድ በኩል ምርጫውን በማራዘም እስከ ቀጣዩ ጉባኤ ህወሓት በም/ሊቀመንበሩ ዶ/ር #ደብረፂዮን እየተመራ ለማስቀጠል፣ በሌላ በኩል ደግሞ ወ/ሮ ፈትለወርቅን (#ሞንጆሪኖን) የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ ለመሾም ሲደረግ የነበረው የህወሓት ጨዋታ #በአቻ_ውጤት ተጠናቋል፡፡ በመጀመሪያው ግማሽ ጎል ያስቆጠረው #የአቦይ_ቡድንበሁለተኛው አጋማሽ ባደረገው የመከላከል ጨዋታ ሞንጆሪኖን ከዋና ሊቀመንበርነት ወደ ምክትል ሊቀመንበርነት በማውረድ ነጥብ ጥሏል፡፡ በሁለተኛ አጋማሽ አጥቅቶ ሲጫወት የነበረው #የራዕይ_ቡድን ደግሞ ሞንጆሪኖን ጠልፎ በመጣል ደብረፂዮንን ወደ ዋና ሊቀመንበርነት እንዲመጣ አድርጏል፡፡ በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ከተጫዋቾች ጥፋት ተሰርቶብኛል በሚል ጨዋታውን አቋርጣ በመውጣቷ ምክንያት ከጨዋታ የታገደችው በቀጣይ ቅጣቱ ሊነሳላት እንደሚችል ይገመታል፡፡

በጨዋታው ሁለተኛ አጋማሽ ከራዕይ ቡድን ደጋፊዎች ሲሰማ ከነበረው የድጋፍና ተቃውሞ መፈክር ውስጥ፣ <<#የመለስ_ዜናዊ አጥንት ይወጋናል>> የሚል ይገኝበታል፡፡ በተለይ ደግሞ በውጪ የሚኖሩ የራዕይ ደጋፊዎች <<እናከብራችኋለን እንጂ አንፈራችሁም!>> የሚል መልዕክት በስልክና ኢሜል አድራሻዎች በገፍ ሲልኩ እንደነበር ታውቋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ፣ የህወሓት የቢዝነስ ኢምፓየር #በአቦይ_ስብሃት ቤተሰብ ተጠቀለለና “ከEFFORT ያለ አግባብ የወሰድከውን 30 ሚሊዮን ዶላር መልስ” እና “ባለቤት የሌለው መስሎኝ ነው የወሰድኩት” በማለት ሲነታረኩ እንደነበር ውስጥ አዋቂያችን ከስፍራው ዘግቧል፡፡

በዚህ መሠረት፣ ሁለቱም ቡድኖች በሁለት ጨዋታ ተሸንፈው አንድ አቻ ወጥተው በአንድ-አንድ ነጥብ ወደ ቀጣዮ ዙር ሳያልፉ ቀርተዋል፡፡ ከምድቡ 2 ጨዋታ አሸንፎ፣ በአንዱ አቻ የወጣው #ኦህዴድ 7 ነጥብ አንደኛነት ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል፡፡ ወጥ አቋም ማሣየት የተሳነው #ብአዴን፤ በመጀመሪያው ጨዋታ አሸንፎ፣ በሁለተኛው ደግሞ ተሸንፎና በመጨረሻው ዙር ጨዋታ አቻ ወጥቶ በ4 ነጥብ ወደ ቀጣዩ ዙር በሁለተኝት አልፏል፡፡ ሌላኛው ተወዳዳሪ #ደኢህዴን በከፍተኛ ግራ መጋባት ውስጥ በመሆኑ ምክንያት ራሱን ከውድድሩ ማግለሉ ይታወሳል

Filed in: Amharic