>

የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ስብሰባ ኣጫኣጭር መረጃዎች (ኣስገደ ገብረስላሴ መቀለ)

የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ጭንቀት የተሞሏበት እና ኣንድ ኣንድ ማእከላይ ኮሚቴ ታመናል ብለው ወደ ኣመሪካ የሸሹ ፣ታመምን ብለው ተደብቀው በሰው ቤት የሚተኙ ፣የስብሰባ መድረክ ረግጠው የወጡ ( የሸሹ ) ፣ በስብሰባ ውስጥ ገብተው የሚጣሉ ፣ በኣጠቃላይ ስብሰባው ጠብ ፣መናናቅ ፣በቂም በቀል ብድር መማላለስ የተሞሏበት ሆኖዋል ። ከነዛ ምክንያት እየፈጠሩ የሚወጡ ፣ኣንድኣንድ የውስጥ ኣዋቂዎች እንደነገሩን ፣

1ኛ ብርሃነ ኪዳነማርያም (መራት) ታመምኩ በማለት ኣመሪካ መግባቱ ተሰማ ።

2ኛ በየነ ሞኩሩ በመሱና ተባላሽታሀል የሚል ከባድ ሂስ ከተሰጠው በኃላ በተጨማሪ ከደብረጽዮን በመድረክ ላይ በተደጋጋሚ ስለተጣሉ ከመድረክ በህመም ምክንያት በመፍጠር ወጥቶ ከቤቱ ውጭ በጓዶኞቹ ቤት ተኝቶ ተገኝቶ ተለምኖ ወደ ሰብሰባ ገባ ።

3ኛ ኣዜብ መስፍን በሙሱና ተባለሽተሻል ስለተባለች ሁለተኛ ኣባይ ወልዱ በጸረ ዲሞክራሲ ፣በትግራይና በገንደር ግጭት ምክንያት ስለሞቱት የትግራይ ተወላጆች ፣ስለወደመ የህዝብ ሀበት እና ስለግጭቱ በዋናነት ኣባይወልዱ ተጠያቂ መሆኑ ስለተነገረው ፣ በትግራይ ክልል በሚሊዮን የሚቆጠር የህወሓት ኣባል ከኣባልነት በመፍረሱ ፣ቡዙ የመንግስት ሰራተኛ በኣባይ ወልዱ ጸረ ዲሞክራሲ ምክንያት ከክሉሉ በሙሉ ስለወጡ በማድረጉ ፣ የትግራይ ህዝብ የፍትህ ግልጋሎት የህግበላይነት የማህበራዊ ኣገልግሎት ባለማግኜቱ ፣ በክልሉ የለለ የልማት እድገት የውሸት ዳታ በማቅረቡ ከባድ ሂስ ስላኣረፈበት ።ኣዜብ መስፍን እንደ ኣባይ ያለ የመለስ ረኣይ ስትራተጂ እና ፖሊሲ ያስፈጸመ ኣባይ በሆነ መስፈርት ሂስ ማረፍ የለበትም ብላ ስለተጣበቀች ከተሰብሳቢዎች ቡዙ ዘለፋ ስለደረሰባት ፣ ስለኤፈር ኣማራር ውድቀት ስላብጠለጠሏት ክብሬን ተነካ ብላ ከመድረክ ከወጣች በኃላ ከቀናት በኃላ በጀነራል ሳሞራ የኑስ ኣስታራቂነት ይቅርርታ ጠይቃ ልትመለስ ተደርጎ ስትመለስ ፣በደብረጽዬን ገብረሚካኤል እና ቡዱኖቹ ፣ኣዜብ መስፍን የድርጅታችን መተዳደሪያ ደንብ ረግጣ ስለወጣች ኣትመለስም ። ካሁን በፊትም የህዋሓት ማእከላይ ኮሚቴ ኣንጃዎች የፓርቲው መተዳደርያ ደንብ በመጣሳቸው ነው። የተባረሩ ፣
በመሆኑም ኣዜብ መመለስ የለባትም በማለት ከኣቋማቸው ኣልተቀየሩም በመጨረሻ ኣዜብ በድምጽ ኣብላጫ ይቅርታ ጠይቃ በመድረኩ ገብታ በሂስ እየተመታች በጭንቀት ውስጥ ትገኛለች

4ኛ ኣለም ገብረዋህድ ፣ ኣዲስኣለም ባሌማ ፣ሚኪኤለ የኣክሱም ዞን ኣስተዳዳሪዎች በከባድ የሙሱና ብለሽት ከባድ ሂስ እያረፈባቸው ይገኛል ። በተለይይ ቡዙሀብት በምዝበራ እንደኣካማቹ ተነግሮዋቸዋል ።

5ኛ ኪሮስ ቢተው ፣የእርሻና የተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ሀላፊ በትግራይ የለለ የእርሻ ምርት የውሼት ዳታ በማቅረብ ።የተፈጥሮ ደን ሽፋን የመስኖ ልማት ሽፋን የውሼት ዳታ መሆኑ ኪሮስን ቢተው የሚነካ ሂስ ኣርፎቦታል ። ይህ እንዳለ ሆኖ ኪሮስ ቢተው የወሼት ልማት ዳታ በማቅረቡ ፣እርዳታ ይሰጡን ለነበሩ ለጋሽ ኣገሮችም የእርዳታ እጃቸው እንዲስቡ ኣድርጓል በማለት ከባድ ሂስ ኣርፎቦታል ።

6ኛ እነዛ ኣንጋፋ ሙሶኞች የህወሓት ከፍተኛ ኣማራር የነበሩ ገና ሂስ እስኪሚያርፍባቸው በሩቅ ሆነው ምንም ገበና እንደሌላቸው ኣመካሪዎች ፣ ኣስተያዬት ሰጭዎች ሆኖው ጸፍ ጭልጥ ብለው ቃላት እየወረወሩ ይታያሉ ።እኒህ ኣዛውንቶች ኣሁን ጭዋ እና ንጹሃን ይምሰሉ እንጅ ኣስቀድመው የዚህ ሀገርና ህዝብ ኣንጡራ ሀብት ዘርፈው ዘርዘራቸው በሁለገብ ያቋቋሙና ልጆቻቸው ያዳላደሉ ናቸው ።

7 በ1993 ዓ / ም ከህወሃት ተገንጥለው የወጡ ማእከላይ ኮሚቴ የነበሩ ገብሩ ኣስራት ፣ስዬ ኣብርሀ ፣ኣውዓሎም ወልዱ ሲቀሩ ሌሎች ማ / ኮሚቴ ነበር ይመለሱ ኣይመለሱ ክርክር ተደርጎ ኣባይ ወልዱና ጥቂት ቡዱኖቹ ሲቃወሙ ሌሎች ግን ተስማምቷል ።

8ኛ በኣጠቀላይ በስብሰባው ተጠምዶና ተጨንቆ ያለው የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ በቡዙ ቡዱኖች ተከካፋፍለው ከርመው በኣሁኑ ጊዜ በጥቅማቸው ተሳስረው ወደ ሰወስት ጠንካራ ቡዱናኖች እና ሰወሰት ደካማ ቡዱኖች ወርደዋል ። ወና ዋናዎቹ ፣

8 ,1 , የኣባይወልዱ የትግራይ ማእከላይ ከሚቴ የሚባል በኣባይ ወልዱ ኣዲስ ኣለም ባሌማ በየነ መኩሩ ፣ኣለም ገብረዋህድ ፣ኣባይ ጸሀዬ ፣አለም ገበረወህድ ሓገስ ጤና ጥበቃ ፣ኪሮስ ቢተው ፣ እና ሌሎች እንደሮቦት በሪሞት የሚነዱ ሆነው ትልቅ ቡዱን ነበሩ ። ኣሁን ግን ኣባይወሉና ኣባይጸሀዬ ኣዜብ መስፍን ፣ሀጎስ እና ጥቂት ሰዎች የመለስ ረኣይ ነክሰው ሲቀሩ ።

8, 2ይህ ቡዱን የኣርከበ እቁባይ በመጠኑ ለነደብረጽዮን እና ጌታቸው ኣሰፋ የሚደግፍ ሰልጣናችን ለሀቀኛ እና ቡቁ የሙሁራን ትወልድ እናስ ረክብ ፣እስከኣሁን በስመሙሁር በማእከላይ ኮሚቴና ሌላ የስልጣን ቦታ ሰጥተናቸው የነበርን ሌቦችና ለሆዳቸው ኣዳሪዎች በይ ነው ይህ ቡድን በብዛቱ ጥቂት ነው ።

8, 3 ሰብሀት ነጋ የያዘው ቡዱን ህወሓትን እናድን ነባር ተጋዮችና ኣማራር ፣ኣባልት እንሰብስብ ይላል እንደኣርከበ በዱንም ወደነ ደብረጽየን እና ጌታቸው ኣሰፋ ያዘነብላል ።

8, 4 እነ ብርሀነ ገብረክርስቶስ ያሉባቸው ጥቂት ሰዎች ደግሞ የህዝብ መእበል ወላፈን እንዳያኣቃጥላቸው ማኸል ሰፋሪ ሆነዋል ።

8,5 ኣዲስ ተምረዋል የሚባሉ ወጣት ማእከላይ ከሚቴ ደግሞ በማኸል ሆነው በበላት እና ባካበታት ትንሽ ገንዝ ሳይበሏት በስጋት እያዋጀቁ ኣጎላጉል የቆሙ ናቸው ።

ኣለም ገብረዋህድ ኪሮስ ቢተው ፣ ኣዲስ ባሌማ በየነ መኩሩ የያዙ በርከት ያሉ የሂስ ድላ ካረፈባቸው በኃላ ለሌላው ቡድን ፈርተው ወደ እነ ደብረጽዮን እና ጌታቸው ኣሰፋ እንደወገኑ ከህወሓት ስብሰባ መረጃው ኣፈትልኳል ።

8 ,6 ከላይ እንደጠቀስኩት ደብረጽዮንነ ጌታቸው ኣሰፋ እነኪሮስ ቢተው ኣስከትሎ ለኣባይ ወልዱና ጓደቹ በከባድ ሂስ ከሰራ ውጭ እያደረገ ያለ ትልቅ ቡዱን ነው ። ጀነራል ሳሞራ የኑስም በውጭ ሆኖ ለኣባይ ወልዱ እና ኣዜብ ፣ኣባይ ጸሀዬ እንደሚደግፍ የወጡ መረጃዎችን ይጠቁማሉ ።።

በመጠቃለል የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ በኣሁኑ ጊዜ በውስጡ ኣንድነቱ ተበጣጥሶ ታክሞ ሊድን በማይድንበት ሁኔታ ነው የሚገኜው ።በኣሁኑ ጊዜ እነዚህ ፍጡራን ለሀገርን ህዝብን ፍተህ ሰላም
ለማስፈን ኣቅማቸው እደተጨረሰ ኣምነው ስልጣናቸው ለማህበረሰብ ኣስረክበው ፣ገበና ካላቸው ወደ ህዝብ ቀርበው ፍረደን እንደማለት ፈንታ ከስልጣን ጋር የሙጡኝ ብለው መያዝ ኣያዋጣቸውም ።

ከላይ የተቀመጠው የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ከተባላሸው ስብሰባ ተያይዞ በመቀለ ከተማ ካሁን በፊት ያልነበረ የጸጥታ ሀይሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት የድህንነት ፣ ኢንሳ ከኖሬሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት በስብሰባው ኣካባቢ እያንጃበቡ ከባድ ጥበቃ እያደረጉ ይገኛሉ ።ተራ የስለላ ወይ ድህንት ሃይሎች ፣ፈደራል ፓለስ የትግራይ ልዩ ሀይል በሙሉ መቀለ ከተማ ነው ያለው ። የመከላከያ ሀይልም ከወትሮው የተለዬ ኣለ ።

Filed in: Amharic