>

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቶ በቀለ ገርባ በዋስ እንዲፈቱ አዘዘ

ፋና ኤቢሲ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሽብር ወንጀል ተከሰው የነበሩት የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ዋስትና ተፈቀደላቸው።
በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ የወንጀል ችሎት በሽብር ወንጀል ተከሰው ጉዳያቸው ሲታይ የነበረው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ባቀረቡት የዋስትና የይግባኝ ጥያቄ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተቀብሎ አፅድቆታል።
አቶ በቀለ ገርባ በዚሁ ችሎት የመከላከያ ምስክር ለማሰማት በቀጠሮ ላይ ያሉ ሲሆን፥ በተደጋጋሚ ባቀረቡት ይግባኝ የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ በመደረጉ ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አንደኛ ይግባኝ ሰሚ ወንጀል ችሎት ይግባኝ ብለው ነበር።
ይህንን የይግባኝ ጥያቄያቸውን የመረመረው ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በ30 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ አዟል።
ነገር ግን የመከላከያ ምስክር የማሰማት ሂደቱ የሚታይ ይሆናል ተብሏል።
፠፠

Filed in: Amharic