>

" እዛም ቤት እሳት አለ " ወዴት አለ ???

ዳ ኪሩቤል ካሳዬ
ያለፉት 27 አመታት ውስጥ እየሆነ ያለውን ሁኔታ እያውቅነው እንደ ማንኛውም የሰው ልጅ ነገ ሊሆን የሚችለውም መገመት ያቃተን በግለኝነት በዘረኝነት እና የዛሬን ብቻ እያሰብን ለምንኖር ወጣቶች ይህን መልክት ልጫጭር ወድጃለሁ :: ግፍ ሲበዛ የሰው ልጅ ደም በገንት እንደምታስተጋባ እንኳን የረሳን : … የሰው ልጅ በብሄሩ እየተመረጠ የግድያ የዘረፋ እና የማፈናቀል ድርጊት በጠራራ ጸሐይ እየተከናወነ ማምረር ላቃተን እና በፍርሐት ሰንሰለት ጠርቆ የያዘንን የወንበዴ አገዛዝ መቃወም ለተሳነን ሁሉ:: ዛሬ በአንዳንድ ቦታወች የተፈጸሙትን በከፊል በፌስ ቡክ እና በተለያዮ ድህረ ገጾች ለምንሰማው ለምናነበው የምንደነቅንም ያጠቃልላል:: በየቀኑ የአማራ ተወላጅ በመሆናቸው ብቻ ለመገደል በቂ ምክንያት የተጣለባቸውን ስናስብ :- በየሆስፒታሉ ታመው እንዲምኖቱ የሚደረጉ ቋንቋቸው አማርኛ ስለሆነ ብቻ ትምህርት እንዳይማሩ የሚደረጉትን የአማራ ብሄር ስለሆኑ ብቻ ከስራ የሚፈናቀሉትን በኢኮኖሚ ትልቅ በደል የሚደርስባቸውን ማሰብ የተሳነን ጥቂት አደለንም::
እኔ በኖርኩባት ጥቂት የእድሜ ዘመን በአፍሪካ ውስጥ የትኛውም መንግስት ደም ሳያፈስ እንዲሁም ያለ ጦርነት ስልጣኑን የለቀቀ ማንም የለም ስልጣን ደግሞ ክፉ መንፈስ ነውና ማንም ስልጣኑን ከሚለቅ አደለም አንድ ታርጌት የተደረገ ሕብረተሰብን ይቅርና አገር ብድሩ ቢጠፋ የስልጣናቸው እድሜ ይርዘም እንጂ የሰወች መገደል መዘረፍ መፈናቀል ጉዳያቸ ያልሆነ እንደ ሕወሃት ያሉ ወንበዴዎች ለምን ሰላም አያመጡም ብሎ መጠየቅም ማሰብም ትርፉ ድካም ነው:: እድሜ ልካችንን ያለፈውን እየከሰስን ባልሰራነው እየተሞካሸን መኖር እማይደክመን ተስፈኞች መሆናችን በጣም ያሳዝናል :: ቢያንስ አንድ ሰው አገር ያስፈልገዋል ሲቀጥል ደግሞ በአገሩ ሙሉ የዜግነት መብት እና የማንነት ክብር ሊነፈግ አይገባምው ነበር::
ሕወሃቶች ሰንቀው የመጡት የዘር ማጥፋት ፕላናቸውን እረስተን እኛም ሳናውቀው ወይንም በጥልቀት ሳንረዳው የወያኔያዊያንን ራእይ የምንተገብርም አልጠፋንም በዘር እና በጎጥ መከፋፈል ደግሞ ፈጽሞ ሊስተካከል የማይጭል የጥፋት እና የእልቂት መንገድ እንደሚያመራን እንዴት ሳንረዳው ቀርተን አሁንም ድረስ የጎጥ እና የዘር ማህበር ያናውጠናል ??
እውን የአማራው ማህበረሰብ ኢትዮጵያ ላይ ያደረሰው ወንጀል አለን ?? ደሙን አፍስሦ አጥንቱ ከስክሶ አገር አቆየልን እንጂ : የሰውን ልጅ የሚያክል ፍጡር እያጋደሙ በመጥረቢያ መግደል ምን የሚሉት የስልጣንና የገንዘብ ልክፍት ነው ??
መንግስት ነኝ ተብዬውስ እንደግመል ሽንት ወደኋላ የምታቆለቁልን አገር እያሳደኩት ነው የሚለን እኛም የምንሰማው እውን መግስት ነው ?? ሲጀመር ወይ ልብ ብለን አልሰማንም ወንም በምን ያገባኛል ህመም ተጠቅተን (ተይዘን) ካልሆነ በቀር ነግረውንስ አልነበር ?? ” አማራን ደግሞ ማጥፋት ቀላል ነው :: ኦርቶዶክስንም ቢሆን አርቀን መቅበር አለብን” አላሉንም ?? እውነት እላችኋለሁ በኢሊባቡር የተፈጸመው ወንጀል በቀላሉ እንዳናልፈው የሚያደርገን አንደኛው ነጥብ ካሁን ወዲያ የሚሞቱትን በማሰብ እና ቀጥሎ ደሞ የት አካባቢ ያሉትን አማሮች ለማጥፋት የተደገሰላቸውን መገመት በቂ ነው:: ስልዚያም አሁን ኢትዮጵያዊነትን ይዘው የሚታገሉትን ለይቶ በማወቅ ያለምንም ቅደመ ሁኔታ የነጻነት ታጋዮችን መቀላቀም ምንም አማራጭ የሌለው ምርጫ ነው:: እንደ ወያኔ ያለ የወንበዴ ጥርቅምን ከሰይጣንም ጋር ተባብሮ ማጥፋት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ግዴታ መሆን አለበት :: ዋናው የወንበዴ አለቃን ለመያዝ በየጥጋጥጉ ተሰግስገው ወሬ የሚራግቡትን የወያኔ ቡችሎች ላይ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል :: ጸቡ የሚረግበው እኮ እዛም ቤት እሳት እንዳለ ሲታወቅ ነው :: ዛሬ የልብ ልብ ያገኙ ጎጠኞች እንዳሻቸው በኢትዮጵያ አንድነት እና አብሮነት ላይ የደንቆሮ መላምት እያዜሙ ዋና ጠላታችንን ህወሃትን መዘንጋት እንደማያዋጣቸው ሊረዱት ይገባል::
ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ ደግሞ….. ኢትዮጵያዊ ነኝ እኔ እንደ አንድ ዜጋ ሙሉ መብት ሊኖረኝ ይገባል ብሎ ለሚያስብ ጤናማ ህብረተሰብ ወያኔን ማውገዝ እና መክሰስ ሳይሆን ወያኔ ህወሃታዊያኖች ባጠቃላይ የገፈቱ ተቃማሽ ማድረግ ያስፈልጋል:: ያኔ ነው እዛም ቤት እሳት አለ የሚለው መልእክት ጠቀሜታው ሊገባን የሚችለው:: አልዚያ ግን በትናንሽ ሰበር ዜናዎች እየተሰባበርን ማለቃችን አይቀሬ ነው :: በከተማ ላይ የሚኖሩ ወያኔያዊ ሕወሃት ላይ ተጽእኖ መፍጠር አንደኛው ሰከን የማድረጊያ ነጥብ መሆን አለበት::

Filed in: Amharic