>

የዕልቂቱ ድግስ የማን ነው? (ሃብታሙ አያሌው)

ማን ማንን እያጠፋ ነው ? የዚህ ጥያቄ መልስ ወጥና ሁሉንም አንድ የማያደርግ ሊሆን ይቸላል ነገር ግን ሁለት እውነት የለም፤ እውነቱ አንድ ነው። ለዩነት የሚኖረን አመክንዮ (ትንተናው) ላይ ይመስለኛል። እየሆነ ያለው ድንገት የሚከሰት ሳይሆን በዕቅድ የሚከወን መሆኑን መረዳት ነገራችንን ግልፅ ያደርገዋል። ዛሬ በባሌ የተፈፀመው ሰቆቃ ንፋስ አመጣሽ ወይም ወፍ በረር አይደለም። የበደኖ፣ የአርባ ጉጉ፣ የጉራ ፋርዳ፣ የወልቃይት…ቀጣይ ክፍል ነው። ይሄንን ደግሞ የስሜን ያህል እርግጠኛ ሆኜ መናገር እችላለሁ። በህወሓት እቅድ እና እምነት አማራው ሳይጠፋ የኢትዮጵያ አንድነት ሊሸነፍ አይችልም። ኢትዮጵያን ለማዳከም እና ከፋፍሎ እየዘረፉ አገዛዝን ለማፅናት ኦርቶዶክስን እና አማራውን ማጥፋት የግድ አስፈላጊ ተደርጎ አቋም የተያዘበት ጉዳይ ነው።

በ1984 ዓ/ም በበደኖ እና አርባጉጉ የተደረገው ዘግናኝ ጭፍጨፋ በኦነግ ወቶአደሮች ቢሆንም ያለህወሓት የይለፍ ፈቃድ የሚታሰብ አልነበረም። የጉራ ፋርዳውም እንደዚያው መለስ ዜናዊ ፓርላማ ቀርቦ “ሞፈር ዘመት” እያለ መዘበቱን ማስታወስ ጠቃሚ ይሆናል። በአሁኑ ወቅት በአማራው እና በኦሮሞው መካከል እየተፈጠረ ያለውን መተማመን አደፍርሶ አጀንዳ በማስቀየር ትግሉን በኦሮሞና በአማራ መካከል ለማድረግ ህወሓት ሞት ደገሰልን። ወገኖቻችን በአያቶቻቸው ምድር በርስታቸው በኢትዮጵያ ላይ እንደ ከብት ታረዱ።
ትላንት የትግራይን ህዝብ ከጎኑ ለማሰለፍ የሀውዜን ጭፍጨፋን እንዳደረገ ሁሉ ዛሬም ለርካሽ የፖለቲካ ጥቅሙ ሲል በዘመነ ደርግ ሰሜናዊ ኢትዮጵያን እረሃብ ሲፈታው በሰፈራ ከወሎና ከትግራይ የሄዱ ሰፋሪዎችን ህወሓት በሜንጫ አሳረዳቸው።

የዚህ ሰቆቃ አላም የኦህዴዶቹ እነ ለማ መገርሳ የእንቦጭ አረም በመንቀል፤ የብአዴኖቹ እነ ንጉሱ ጥላሁን በቦረና ለተከሰተው ድርቅ እህል በመስፈር የፈጠሩትን መቀራረብ በአሰቃቂ ሞት ዜና ቀይሮ የትግራይና የአማራ ሰፋሪዎችን በእልቂት ስጋት በጥላቻ ለማስተባበር የተፈፀመ ሴራ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው። ስንት በጎ ነገር እያለ ህዝብን በእልቂት አቧድኖ የፖለቲካ ካርታ መያዝ ከጭካኔ ሁለ የከፋ ጭካኔ ነው።

በክልሉ የሚኖሩ ዜጎችን መጠበቅ የኦህዴድ ኃላፊነት እንደሆነ ግልፅ ነው። አላማው ይሄ ጥያቄ እንዲነሳና ስሙር የተባለለት መቀራረብ እንዲደፈርስ በመሆኑ ይህ ለህወሓት ስኬት ነው። እኛም ልማድ ያረግነው ይሄንኑ መርህ አልባ ጩህት ነው፤ አረም ነቀሉ ብለን ከበሮ ስንመታ ነበር፤ አሁን ደግሞ ወደ ጠላት ነው ጩህት ልንመለስ ነው። ሼህ አላሙዲን ከገዳይ ጋር ዛሬም እየተባበረ ያለ በመሆኑ ስናወግዝ ኢትዮጵያን እየዘረፈ ነው ብለን ክስ ስንደረድር ነበርን። አሁን ደግሞ እንቦጭ አረምን ለመንቀል ብር ሰጠ ብለን አባታችን ሆይ እያልን ነው። ለመርገምና ለመመረቅ ችኮላችንን ብንተወው ጥሩ ይመስለኛል።

በየሳምንቱ ህወሓት ሲሸነቁረን መድፈን አጀንዳ ሲሰጠን ማራገብ ሞት ሲደግስልን ጭዳ መሆን ትተን፤ የችግራችንን ሁሉ ምንጭ ህወሓትን ለማስወገድ እንተባበር።

እባካችሁ የእርስ በእርስ እልቂት አትጥሩ። ሁሉም በያለበት ኦሮሞ አማራ ትግሬ ጉራጌ ሳይል ተደራጅቶ እራሱን ይከላከል አንዱ ሌላውን ይጠብቅ ሰይጣናውያን የህወሓት መልዕክተኞች ፀብ ለኳሽ ደህንነቶች ለጥላቻ ለሜንጫው ዘመቻ ተልከናል የሚሉ ቄሮዎችን በሚጋባ ህዝቡ አንድ ሆኖ እንዲታገል። ወደ በጎና ወደ ድሉ አቅጣጫ እንምራ። የህወሓት ጭንቅላት ይመታ ጭንቅላቱ ከፈረሰ ኦህዴድ ብአዴን የሚባሉ ሎሌዎች ይሞታሉ። የዕልቂቱ ድግስ የህወሓት ነው ትግል ሁሉ ወደ ህወሓት!!

Image may contain: text
Filed in: Amharic