>

ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ከተናገሯቸው ታሪካዊ ንግግሮች በጥቂቱ!

በጌጡ ተመስገን

– ሰው ሁሉ እኩል ስለሆነ ማንም ሰው ሰውን ባሪያ አይበል ።

– ሁሉም ሰው በየኃይማኖቱ ይደር ።

– ድኻ እወደደበት ቦታ ይቀመጥ ። በዘር ፣ በወገን ልዩነት አይከልከል ።

– የመሬት ጥያቄ ላቀረቡ የውጭ አገር ሰዎች ንጉሡ የሰጡት መልስ፡- ‹‹ የኛ አገር ፍትሐ ነገሥት ልዑሎች መሬት ይሽጡ አይልም ። ያገሬ መሬት ባለቤቱ ሌላ ነው ። ከአባቶቻቸው እየተቀበሉ ያቆዩት መሬት ነው ።… መሬቱ የሁሉም ስለሆነ አይሸጥም ። ማንም ሰው መሬቱን ሊሸጥ አይችልም ። መሬትን መሸጥ፣ መስጠትም የሚችለው የመሬቱ ጌታ ነው ››

– ለመንግሥት ተሿሚዎች የሰጡት መመሪያ፡- ‹‹… እንቅልፍ ሳትወዱ ፣ መጠጥ ሳታበዙ፣ ገንዘብን ጠልታችሁ ተግታችሁ ሥራችሁን ፈጽሙ ። እኔ እናንተን ስለአመንኩ እናንተም የምታምኑትን ፣ ገንዘብ የማይወደውን፣ ድኻ የማይበድለውንና የሚረዳችሁን ሰው እያመለከታችሁኝ ከሥራው በመግባት መንግሥታችንን እርዱ ››

– በጣም ወደኋላ የቀረን ሕዝቦች ነን ። ገና የሚሠራ ብዙ ሥራ ስላለ ወጣቶቻችን መማር አለባቸው ።

– አባት ያለህ የአባትህን እሰጥሀለሁ፤ አባትህን መርቅ ። አባት የሌለህ አባትህ እኔ ነኝና ደጅ ጥናኝ ።

– እኔ ቤት እንጀራ የለም ። እንጀራ ያለው ትምህርት ቤት ስለሆነ ፤ እሠራሁት ትምህርት ቤት ልጆቻችሁም እያስገባችሁ አስተምሩ ።

– የኔ ርስት ኢትዮጵያ ናት ፤ የግል ርስት አልፈልግም ። ደግሞስ የተሾምነው እርስት ከተካፈልን ለሕዝቡ ማን ያካፍለዋል?

– ሐገራችን አንድትለማ የሚቀርቡንን ሁሉ በታላቅ ደስታና በአክብሮት እንቀበላቸዋለን ። በሌላ ለሚመጡብን ግን ፤ ሁላችን ሳናልቅ ሀገራችንን ለባዕድ አሳልፈን እንሰጥም ።

– የሚጠሉህን ሰዎች ከማጥፋት ፤ የሚጠላብህን ማጥፋት እንዲሉ ፤ የሸፈቱባቸውን ፣ የወጉአቸውንና ያሤሩባቸውን ሰዎች በጋብቻ ፣ በዝምድና ወይም ወዳጅ አድርገው ያቀርባሉ እንጂ ክፉን በክፉ መመለስና መበቀልን አይሹም ።

– አንድ የፈረንሳይ ዜጋ የቦታ ግዥ ፈቃድ ሲጠይቃቸው ምኒልክ በሰጡት መልስ ፡- ‹‹ ያገሬ መሬት የሁሉም 
ኢትዮጵያዊ ስለሆነ ፤ መሬት መሸጥ መለወጥ የሚችለው ሕዝቡ ነው ። ደግሞስ የውጭ ዜጎች መሬት እንዲገዙ ከፈቀድኩና ባለመሬት ከሆኑ ፤ ለኔ ምን ቀርቶ እገዛለሁ ? ›› አሉ ።

ምንጭ ፡- የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ መጽሔት ቁጥር 1. ነሐሴ 1992 ዓ.ም

Filed in: Amharic