>
5:13 pm - Sunday April 19, 0871

በስመ ‹‹ፕራይቬታይዜሽን!›› የእንግዴ ሜቴክ ሚሊየነሮች! (ፂዩን ዘማርያም)

የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (Metals and Engineering Corporation (METEC)፣ የህወሃት የጦር አበጋዞች መንግስት፣ በመከላከያ ሚኒስትር ስር የተዋቀረው የእንግዴው ልጅ ብኢኮ/ሜቴክ፣ ከደርግ ወታደራዊው መንግስት፣ መከላከያ ሠራዊት የተወረሱ ፋብሪካዎች ሥራ የጀመረ የእንግዴ ድርጅት ነው፡፡ ሜቴክ በ2010 እኤአ በአስር ቢሊዩን (10,000,000,000) ብር መነሻ ካፒታል ተመሠረቶ ሥራ ሲጀምር ከደርግ መከላከያ ሠራዊት የተወረሱ አስራሁለት ሜካናይዝድ ፋብሪካዎች ሥም በመቀየርና በወታደራዊ ሣይንስ የተካኑ የሠራዊቱ አባላቶች ዕውቀትና ልምድ ማርኮ የተዋቀረ እንግዴ የወያኔ ድርጅት ነው፡፡ በአሁኑ ግዜ በህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ዘመን እንግዴው ሜቴክ ተንሰራፍቶ፣ ከስባ አምስት እስከ መቶ ፋብሪካዎች በላይ ያሰባሰበ ድርጅት ለመሆን ችሎል፡፡ የህወሃት ሜቴክ ጀነራል ማኔጀር ብርጌደር ጀነራል ክንፉ ዳኘው ሲሆኑ እንዲሁም ምክትል ጀነራል ማኔጀር ኮለኔል ጠና ኩርንዲ ይባላሉ፡፡ ሜቴክ ኮርፖሬሽን ከ13000 ሠራተኞች ሲኖሩት ከነዚህ ውስጥ 1000 ዎቹ ማሃንዲሶች ናቸው ይሉናል፡፡ የጀነራል ሳሞራ ዮኑስና ብርጌደር ጀነራል ክንፉ ዳኘው ሚስቶች እህትማማቾች ሲሆኑ፣ ሌሎቹም ‹‹ጀነራል መኮንኖችና ሹሞች›› የትዳርና የዘር ትስስራቸው እንዲሁ ነው፡፡ ‹‹የሜቴክ ሚሊየነሮች!!!››

(1) ጀነራል ሳሞራ ዮኑስ ሶፍያ ሞል ፎቅ ገንብቶል ሠፈረ ቺቺኒያ ሌላ ፎቅ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡
(2) ብርጌደር ጀነራል ክንፉ ዳኘው ፎቅ ገንብተው ሆቴል ቤት አድርገውታል፡፡
(3) ጀነራል አበበ ተከለሀይማኖት ቦሌ ፎቅ ገንብቶል
(4) ለጀነራል ፃድቃን ገብረ ትንሳይ ቦሌ ፎቅ ገንብቶል፣ የሌሎቹን የኢትዮጵያ ህዝብ ይቁጠረው፡፡
በኢትዮጵያ ‹‹ወታደራዊ የመንግስት የልማት ድርጅቶች›› ነቀላና ተከላ የተኮላሸው ለዚህ ነው፤ ከደርግ ወታደራዊ መንግሥት ወደ ዘረኛ የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥት ተሸጋገረ፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ መከላከያ ሠራዊት ተቆማቶች በወያኔ ጠባብ ዘውጌ ሠራዊት ከተተካ 26 ዓመታት ተቆጠረ፡፡ ከነዚህ ‹‹ወታደራዊ የመንግስት የልማት ድርጅቶች›› ውስጥ በህወሃት/ ኢህአዴግ መንግስት የመከላከያ ሚኒስትር ስር የተkkመው፣ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ስም ከወታደራዊ መንግስት ንብረትነት ወደ ሕወሃት መንግስት ንብረትነት ሽግግር በስመ-ፕራይቨታይዜሽን ስም የተሸጋገሩ ዋና ዋናዎቹ የህዝብ ኃብቶች ቀጥሎ በዝርዝር ይቀርባሉ፡፡
በኤሌትሪክ ዥረት ኃብታችን ገዳዩን የወያኔ ሜቴክና አግአዚ ጦር ቆመን እራት አናበላም!!!
(1) የደጀን አቨየሽን ኢንጂነሪንግ ኮምፕሌክስ (Dejen Aviation Engineering Complex (DAVEC) በወታደራዊው መንግስት በ1984 እኤአ በኢትዩጵያ አየር ኃይል የተመሠረተው የአውሮፕላን ማደሻና መመርመሪያ ማዕከል በመሆን ከፍተኛ የአየር ኃይል አውሮፕላን ጥገናና እድሳት ሥራ በማድረግ ይታወቃል፡፡ ከአዲስአበባ 47 ኪሎ ሜትር ርቀት በደብረዘይት ከተማ የሚገኘው ኢንደስትሪ በስሩ፣ ስምንት የነበሩ ፋብሪካዎች በማደራጀት የማይንቀሳቀስና ተንቀሳቃሽ የአውሮፕላን ክንፍ ማምረቻ ፋብሪካዎች፣ ኤሮስፓስና ሜካኒካል ፋብሪካ፣ አቪዩኒክስ ሲስተም ኢንቲግሬሽን ፋብሪካ፣ ፓወር ፕላንት ፋብሪካ፣ የአውሮፕላን አካልና መቃን አቆም/ስትራክቸር ፋብሪካ፣ ዩኤቪ ምርቶች ፋብሪካና የአውሮፕላን ጥራትና ችሎታ መፈተሻ ማዕከል ፋብሪካዎች በህብረ-ብሄራዊው ሠራዊት ተገንብቶ ነበር፡፡ የቀ.ኃ.ሥና የደርግ ዘመን ‹‹ወታደራዊ የመንግስት የልማት ድርጅቶች›› ዛሬ በወያኔ የዘር ነቀላና ተከላ ተካሄደበት፡፡ በ2010እኤአ በህወሃት/ ኢህአዴግ መንግስት ዘመን ድርጅቱ ዳቦ ሳይቆረስ ደጀን አቨየሽን ኢንድስትሪ ተብሎ በ(ብኢኮ) ንብረት ሆኖ ተወረሰ፡፡ የኢትዩጵያ አየር ኃይል ቤዝ ከደብረዘይት/ብሸፍቱ ተነቅሎ ትግራይ ውቅሮ መዘዋወሩን ልብ ይበሉ፡፡ በአሁኑ ግዜ ጀነራል ማናጀሩ ሌተናል ኮነሬል ኪዱ ፀጋዬ እና ሜጀር ሃይለ ገብረ ጊዮርጊስ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡

(2) የጋፋት ኢንጂነሪንግ ፋብሪካ (Gafat Engineering Factory) በወታደራዊው መንግስት በ1989እኤአ ኤኬ-47 እና አርፒጂ ቀላል መትረየስ ጠመንጃ በማምረት ይታወቃል፡፡ ፋብሪካው ከአዲስአበባ ደቡብ ምስራቅ 65 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ሲገኝ፣ ፋብሪካው በ4,412 ስኮየር ኪሎሜትር ቦታ ላይ የተገነባ ነበር፡፡ፋብሪካው በተጨማሪ ኤኬ 103፣ 40 ሚሊሜትር የቦንብ አውዘግዛጊና ሌሎች አቶማቲክ መሣሪያ በጦር መኪናዎችና በሂሊኮፕተር ላይ የሚገጠሙ ላውንቸር፣ ማኑፋክቸሪንግ የጦር መሳሪያ መለዋወጫና ብረት በማቅለጥና ምስል መቅረፅና በመጫን ምርቶችን አምርቶ ለገበያ የማቅረብ አላማ አካቶ ፋብሪካዉ ያመርት ነበር፡፡ የጋፋት የመሳሪያ ኢንደስትሪ ስድስት ፋብሪካዎችን ያካትታል እነሱም፣ አነስተኛ የነፍስ ወከፍ መሣሪያ ማምረቻ፣መካከለኛ ካሊበር ማምረቻ ፋብሪካ፣ሮኬት ላውንቸር እንዲሁም ሞርታርስ ፋብሪካ ማምረቻ እና ከባድ መሳሪያ የመድፍ ማምረቻና ቅርብ ርቀት የሚተኩስ ጠመንጃ ፋብሪካ ማምረቻ ፣እንዲሁም የመሣሪያ መለዋወጫ ማኑፋክቸሪንግ ፋብሪካዎችና በህብረ-ብሄራዊው ሠራዊት ላይ ወያኔ የዘር ነቀላና ተከላ አካሄደ፡፡ በ2002እኤአ በህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ዘመን ካንፓኒው ስሙን በመቀየር ጋፋት የመሳሪያ ኢንደስትሪ (Gafat Armament Industry) በመባል የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ) ተወረሰ፡፡ በአሁኑ ግዜ ጀነራል ማናጀሩ ሜጀር ግሩም ገብረኪዳንና ሜጀር አፅብሃ ገብሬ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡

(3) የናዝሬት የትራክተር መገጣጠሚያ ፋብሪካ (Nazareth Tractor Assembly Plant (NTAP)በወታደራዊው መንግስት በ1984እኤአ ከአዲስ አበባ ከተማ 90 ኪሎ ሜትር ርቀት በናዝሬት ከተማ ውስጥ በ114,388 ስኩየር ሜትር ባታ ላይ የተገነባ ነው፡፡ ፋብሪካው ትራክተር በመገጣጠም፣የውሃ መርጫ ማጠጫ/ፓምፕ እንዲሁም የተለያዩ የግብርና መሣሪያዎች መገጣጠሚያና መለዋወጫ ምርቶች በመስራት ይታወቅ የነበረ ነው፡፡ በ2010እኤአ በህወሃት/ ኢህአዴግ መንግስት ዘመን ስሙ ተቀይሮ የአዳማ የግብርና ማሽነሪ ኢንደስትሪ (Adama Agricultural Machinery Industry (AAMI) ተብሎ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ) ተወረሰ፡፡ የናዝሬት የትራክተር መገጣጠሚያ አራት ፋብሪካዎች ስብስብ ነበር፣ ወታደራዊው ፋብሪካና ህብረ-ብሄራዊው ሠራዊት ላይ ወያኔ የዘር ነቀላና ተከላ አካሄደ፡፡ በአሁኑ ግዜ ጀነራል ማናጀሩ ሻንበል ሚኪያስ ሜጋ ይባላሉ፡፡

(4) የናዝሬት የልብስና ጨርቃ ጨርቅ ኢንደስትሪ በወታደራዊው መንግስት በ1987እኤአ፣የልብስና ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ፣የልብስ መስፍያ ፋብሪካ፣ፓራሹትና የዕቃ ማንሸራተቻ ፋብሪካ፣የጫማና የእጅ ጎንት ፋብሪካና የቤት ዕቃዎች ማምረቻ ፋብሪካ የመሳሰሉትን በማምረት ይታወቃል፡፡ ፋብሪካው ከአዲስ አበባ ከተማ 105 ኪሎ ሜትር ርቀት በናዝሬት ከተማ ውስጥ ይገኛል፡፡በ2010እኤአ በህወሃት/ ኢህአዴግ መንግስት ዘመን የአዳማ የልብስ ኢንደስትሪ (Adama Garment Industry (AGI) ተብሎ በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ) ተወረሰ፡፡ ወታደራዊው ፋብሪካና ህብረ-ብሄራዊው ሠራዊት ላይ ወያኔ የዘር ነቀላና ተከላ አካሄደ፡፡ በአሁኑ ግዜ ጀነራል ማናጀሩ ሜጀር ከተማ አብዲ ይባላሉ፡፡

(5) የአቃቂ መሠረታዊ ብረታ ብረት ኢንደስትሪ (Akaki Basic Metals Industry (ABMI) በወታደራዊው መንግስት በ1989እኤአ በመባል ልዩ ልዩ ከፍተኛና ዝቅተኛ መገጣጠሚያና ማኑፋክቸር መለዋወጫዎች እንዲሁም የካፒታል ጉድስ ማለትም የስካር ማምረቻ ወፍጮ ፍብሪካ፣የስካር ማቀነባበሪ ማፍያና መቀቀያ መለዋወጫዎች፣የብረት ካሶችና የብረት ሠፌዶች፣የጉድጎድ የብረት ክዳኖችና መቃኖች እና ተንቀሳቃሽ የብረት ዘንጎች በማምረት ይታወቃል፡፡ፋብሪካው ከአዲስ አበባ ከተማ 25 ኪሎ ሜትር ርቀት በአቃቂ ከተማ ወጣ ብሎ ይገኛል፡፡በ2010እኤአ በህወሃት/ ኢህአዴግ መንግስት ዘመን የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ( Privatization and Public Enterprises Supervising Agency ) አማካኝነት በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ) ተወረሰ፡፡
ፋብሪካዎችና በህብረ-ብሄራዊው ሠራዊት ላይ ወያኔ የዘር ነቀላና ተከላ አካሄደ፡፡ በአሁኑ ግዜ ጀነራል ማናጀሩ ሜጀር ጀማል አብዲልከድር እና ሻንበል ሙሳ ይማም ይባላሉ፡፡

Filed in: Amharic