>

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አይፈታም (የዝዋይ እስር ቤት ሀላፊዎች) [በታሪኩ ደሳለኝ]

Tariku Desalegn

መንግስት የፈረደውን የፍርድ ቤት ሙሉ የ3 አመት እስር ያለ አመክሮ ዛሬ የጨረሰው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በእራሳቸው ፍርድ አሰጣጥ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ዛሬ መፈታት ሲኖርበት የዝዋይ እስር ቤት ሀላፊዎች ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን አልፈታም በወሏል። ይህ ሁኔታ ቀድሞም የተመስገን እስር ፖለቲካ እንደነበር ተጨማሪ ማረጋገጫ ነው።

ትላንት ጥቅምት 2/2010ዓም ተሜን ጠይቄው ስወጣ እግረ መንገዲን እስረኛ አስተዳደር ገብቼ እስሩን ስለሚጨርስ ሰው ላናግራችሁ ነበር ስል አንዱ ሰው “ላጣራልህ” ብሎ ሲነሳ “ስሙን ልንገርህ” ስለው “አቃለሁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አይደል” ብሎኝ ወጣ አይ ያውቀዋል ያቁኝል ማለት ነው ብዬ አጣርቱ እስኪመጣ ጠበኩት። ይህ ሰው የስራ ሀላፊነቱን የማላውቀው ጊጡ የተባለ ሰው ነው። እንደመጣ እያየኝ ተመስገን ነገ ነው የሚፈታው አለኝ ሰምቼው ወጣሁ። ለነገሩ ባይለኝም ቢለኝም የተፈረደበትን ሙሉ 3 አመት የሚጨርሰው ነገ ጥቅምት 3 ነው አለኝ።

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ መንግስት በፍርድ ቤቱ የወሰነበትን እስር ቢጨርስም አሁን ደግሞ የእስር ቤቱን ሌላ እስር ጀምሯል።
እንግዲህ የተመስገን ህይወት በተመለከተ የዝዋይ እስር ቤት አስተዳደሮች ሀለፊነቱን ይወስዳል ነው። ተመስገን ላይ የሚደርሰው ነገርስ ሁሉ ያሳስበናል።
ዝዋይ እስር ቤት

Filed in: Amharic