የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ የተነሳ ሰሞን ባወጣሁት “
“100% የሚባለውን አሰቃቂ ክስተት “የምርጫ ውጤት” በሚል ሰርግና ምላሽ እየተደረገ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው። በዞንና ወረዳ ደረጃ ያሉትስ አይፈረድባቸውም። በፌዴራልና ክልል ደረጃም ተመሳሳይ አቋም የሚያራምዱ ባለስልጣናት ካሉ ግን በጣም አስገራሚ ነው የሚሆነው ። ይሄ 100% ተብዬ ነገር’ኮ ባለፉት 20 አመታት ውስጥ ሀገሪቱ በዲሞክራሲ ረገድ ያሳየችውን ለውጥና መሻሻል ወደ ኋላ የቀለበሰ፣ ህዝቡ ሰላማዊ ፖለቲካ፣ በሕግ የበላይነት እና በሌሎች ዴሞክራሲያዊ እሴቶች ላይ ያለውን እምነት ሽርሽሮ በመናድ ዴሞክራሲን በጭቅላቱ ዘቅዝቆ ያቆመ፣ ልክ እንደ ደርጉ ቀይ-ሽብር ህዝብን በፍርሃት ቆፈን የሚቀፈድድ እጅግ አስቀያሚ ድርጊት ነው።”
በተለይ ባለፉት አስር አመታት የኢህአዴግ መንግስት፤ በፀረ-ሽብር ሕጉ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችን፣ በሚዲያና የመረጃ ነፃነት ሕጉ ነፃና ገለልተኛ ሚዲያዎችን፣ እንዲሁም በበጎ አድራጎት ድርጅቶች ማቋቋሚያ አዋጅ የሲቪል ማህበራትን አጥፍቷቸዋል። የኢህአዴግ መንግስት እነዚህን የዴሞክራሲ ተቋማት ከማጥፋቱ በተጨማሪ፣ የተለየ ሃሳብና አመለካከት ያላቸውን የራሱን አመራሮች “በሃይማኖት አክራሪነት፣ ብሔርተኝነት ወይም ትምክህተኝነት” እየፈረጀ የተወሰኑትን ለእስርና ስደት ሲዳርጋቸው፣ የተቀሩት ደግሞ ሃሳባቸውን ከመግለፅ እንዲቆጠቡ አድርጓቸዋል።
በአጠቃላይ፣ በአንድ ሀገር ውስጥ ጠንካራ ተቃዋሚ የፓለቲካ ድርጅቶች፣ ነፃና ገለልተኛ ሚዲያ እና የሲቭል ማህበራት ከሌሉ፣ እንዲሁም ገዢው ፓርቲ የተለየ ሃሳብና አመለካከት የማስተናገድ ባህል ከሌለው ሕገ-መንግስታዊ ዴሞክራሲ (Constitutional Democracy) አብቅቶለታል። በተቃራኒው፣ ከ2008 ዓ፣ም ጀምሮ ባለው ግዜ ውስጥ ብቻ በሕዝቡ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ላይ የታየው ለውጥ የሩብ ምዕተ አመታት ያህል ሰፊ ነው። ሕዝቡ የሚያነሳቸው ጥያቄዎችና እያሳየ ያለው የለውጥ ፍላጎት ከእለት-ወደ-እለት እየተቀያየረና እየጨመረ መጥቷል። በዚህ ፈጣን የለውጥ ሂደት ውስጥ
በ2008 ዓ.ም
የህዝቡ ጥያቄና እንቅስቃሴ ተፈጥሯዊ የለውጥ ሂደትን ተከትሎ የመጣ እንደመሆኑ አይቀሬና አስገዳጅ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ፣ የህዝቡ ኑሮና አኗኗር እየተለወጠ፣ በተለይ ደግሞ የመረጃ አቅርቦትና አጠቃቀም እየተሻሻለ በሄደ ቁጥር፣ አብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍል መብትና ግዴታውን ይበልጥ ያውቃል፥ ይጠይቃል። በልማትና ዴሞክራሲ ረገድ ህዝቡ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች ይበልጥ እየሰፉና እየተወሳሰቡ መሄዳቸው እርግጥ ነው።
ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ እየታየ ያለው ተቃውሞ ህዝቡ በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ መብቱን ለማስከበር የሚችልበት አማራጭ መንገድ በማጣቱና ብሶትና ምሬቱን የሚተነፍስበት ትንሽ ቀዳዳ ባለመኖሩ የተከሰተ ነው። በአንድ በኩል ህዝቡ በፍትህና የመልካም አስተዳደር እጦት ምክንያት እየተሰቃየ ነው። በሌላ በኩል፣ ለአስር አመታት የተጠራቀመ ብሶቱንና ምሬቱን የሚያስተነፍስበት ቀዳዳ ሲያጣ፣ አመፅና ተቃውሞ ብቸኛ አማራጭ ይሆናሉ። በተለይ ደግሞ፣ ቀልጣፋ አገልግሎትና ፍትህ ያልሰፈነበት ምክንያት ሌላ ሳይሆን መንግስት የአስተዳደርና ፍትህ ሥርዓቱን ማሻሻል ስለተሳነው እንደሆነ በበቂ መረጃ ላይ የተመሰረተ ግንዛቤ ሲኖረው ህዝብ ይቆጣል፣ ህዝባዊ አመፅ ይቀሰቀሳል።
ከዚያ በመቀጠል “
ከላይ በተጠቀሰው
የኢህአዴግ ባለስልጣናት ሥራና አሰራራቸውን ከማሻሻል ይልቅ ፖሊሶች፣ ወታደሮችና የደህንነት ሰራተኞች በመላክ ሕዝቡን ለሞት፣ ጉዳትና ለእስራት የሚዳርጉት ከሆነ ባለስልጣናቱ በሕዝቡ ዘንድ ያላቸውን ቅቡልነት፣ እንደ መንግስትም ያላቸውን ተቀባይነት ከግዜ ወደ ግዜ እያጡ ይሄዳሉ። በዚህም አንደኛ፡- መንግስት በሕዝቡ ዘንድ ያለውን የማስተዳደር
“
የአማራ ክልል መስተዳደርና የብአዴን አመራሮች ከሕዝቡ ለሚነሳው ጥያቄ የድጋፍ አዝማሚያ ማሳየታቸው ይታወሳል። በተቃራኒው የቀድሞ የኦህዴድ የበላይ አመራር በክልሉ ሲካሄድ የነበረውን የሕዝብ አመፅና ተቃውሞ በኃይል ለማዳፈን ያላሳለሰ ጥረት አድርጓል። ይህ ግን በአቶ ለማ መገርሳ የሚመራውን አዲሱን የኦህዴድ አመራር ወደ ስልጣን እንዲመጣ አድርጎታል። በሌላ አነጋገር፣ የአቶ ለማ መገርሳ አመራር በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ በኦሮሞ ሕዝብ ጫና እና ግፊት ወደ ስልጣን እንደመጣ መገንዘብ ይቻላል። በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሚመራው የአማራ ክልል መስተዳደር በስልጣን ላይ መቆየት የቻለው በወቅቱ የክልሉ ሕዝብ ላነሳቸው የነፃነት፥ እኩልነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄዎች የመደገፍ ዝንባሌ ስለነበረው ነው።
ሆኖም ግን፣ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ራሱን ለለውጥ ከማዘጋጀትና የተሃድሶ አቅጣጫ ከማስቀመጥ ይልቅ ለህዝቡ ጥያቄ የድጋፍ አዝማሚያ ያሳዩትን የብአዴን እና የኦህዴድ አመራሮችን ተጠያቂ ማድረግ መርጧል። በ2008 ዓ.ም መጨረሻ ላይ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ባደረገው ስብሰባ ህዝቡን በማስመረር ላይ ያለው ችግር ዋነኛ መንስዔ የመልካም አስተዳደር እጦት እንደሆነ በመጥቀስ በቀጣይነት “ከራሱ ጀምሮ” የሚታዩ የጥገኝነት አስተሳሰቦች እና የጥገኝነት ተግባራትን ለመታገል መወሰኑን ገልፆ ነበር። በወቅቱ ኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የሚከተለውን
“… ስልጣን ያለአግባብ ለመጠቀም ለሚሹ ግለሰቦች በመሳሪያነት ማገልገል ሲጀምር የተጀመረው ልማት ይደነቃቀፋል፡፡ መልካም አስተዳደርም ይጠፋል። …በአሁኑ ጊዜ ህዝብን በማስመረር ላይ ያለው ችግር ዋነኛ መንስዔ ይህ ነው፡፡ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በዚህ ረገድ ከራሱ ጀምሮ የሚታዩ የጥገኝነት አስተሳሰቦችና መገለጫ የሆኑትን ጠባብነትና ትምክህተኝነትት እንዲሁም የጥገኝነት ተግባራትን በጥብቅ በመታገል ይህ አዝማሚያ እንዲገታ ለማድረግ የሚያስችሉ ዝርዝር ዕቅዶችም አዘጋጅቷል፡፡”
በመግለጫ መሰረት የጥገኝነት አስተሳሰብ፣ በዋናነት
በ2009 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ በታወጀው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ አማካኝነት ሀገሪቷ ሙሉ በሙሉ በወታደራዊ ቁጥጥር ስር የቆየች ቢሆንም የሁለቱን ክልሎች አመራር እንደ ቀድሞ ለፌደራል መንግስቱ ተገዢ እንዲሆኑ ማድረግ አልተቻለም። ከዚያ ይልቅ፣ ብአዴን እና ኦህዴድ አመራሮች የሕዝቡን ጥያቄ ተቀብለው ማስተጋባት በጀመሩበት ወቅት ለሕገ-መንግስቱና ለፌደራሊዝም ስርዓቱ ጥብቅና የቆሙት በዋናነት የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች እና የሶማሌ ክልል መስተዳደር ናቸው።
ህወሓት/ኢህአዴግ በሀገሪቱ የፖለቲካ ላይ ያለውን
የሶማሌ ልዩ ፖሊስ በምስራቅና ደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ በሚገኙ አከባቢዎች ላይ ተከታታይ ጥቃት በመፈፀም በመቶዎች የሚቆጠሩ የክልሉ ነዋሪዎችን ከሞት፣ ከ200ሺህ በላይ ደግሞ ማፈናቀሉ ይታወሳል። ይህ ሲሆን የፌደራሉ መንግስት፥ የሀገር መከላከያ፥ የደህንነትና ፖሊስ ኃይሎች በሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ የሚፈፀመውን ኢሰብዓዊ ድርጊት ለማስቆም በተጨባጭ ይሄ ነው የሚባል ጥረት አላደረግም። ለዚህ ደግሞ ተጠያቂ የሀገሪቱ የፀጥታ ኃይል መዋቅር በበላይነት የተቆጣጠረውና አዲሱን የኦህዴድ አመራር ለፌደራል መንግስቱ ተገዢ እንዲሆን ከፍተኝ ጥረት እያደረገ ያለው ህወሓት/ኢህአዴግ ነው።
የብአዴን አመራር በራሱ ከፌደራሉ መንግስት ቁጥጥር ለመውጣት የበኩሉን ጥረት እያደረገ ሲሆን የደኢህዴን አመራር ደግሞ በፌደራል መንግስቱ መዋቅርና እንቅስቃሴ ላይ ያለው የመወሰን አቅም እጅግ በጣም ውስን ነው። በዚህ መሰረት፣ የፌደራሉ መንግሰት ህወሓት ብቻውን የሚንከላወስበት ኦና ቤት ሆኗል። በአጠቃላይ የመከላከያና ደህንነት ኃይሉን በበላይነት የተቆጣጠረው የህወሓት/ኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር ግራ ተጋብቶ ሀገሪቷን ወደ እርስ በእርስ
ከሕዝቡ ሲነሱ ለነበሩት የዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ባለፉት ሁለት አመታት የኢህአዴግ መንግስት መውሰድ የነበረበት የለውጥ እርምጃዎች ምንድን ናቸው? በመጀመሪያ ደረጃ ራሱ
በመቀጠል በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ረገድ ስር ነቀል የለውጥ እርምጃዎች መውሰድ ይጠበቅበታል። በዚህ ረገድ ከኢህአዴግ የሚጠበቀው፤ አንደኛ፡- የዜጎችን ዴሞክራሲያዊ መብትና ነፃነት ማክበር ሁለተኛው ደግሞ የመልካም አስተዳደር እጦትን በዘላቂነት መቅረፍ ነው፡፡ በዚህ መሰረት የኢህአዴግ መንግስት ከሕዝቡ እየተነሱ ያሉትን የዴሞክራሲ ጥያቄዎች በአግባቡ ለመመለስ አስተዳደራዊ ተሃድሶ (Administrative reform) እና ፖለቲካዊ ተሃድሶ (Political reform) ማድረግ ይጠበቅበታል።
ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች እየተነሱ ያሉት የእኩልነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄዎች ከመልካም አስተዳደር እጦት ጋር በቀጥታ የተያያዙ ናቸው፡፡ የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመፍታት ግልፅነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት የአስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡ በዚህ መልኩ የአስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓቱን ጥራት ለማሻሻል በቅድሚያ ብቃት ያለው አመራር ሊኖር ይገባል፡፡ ከሙያዊ ብቃት ይልቅ በፖለቲካ ታማኝነት ላይ የተመሰረተ አመራር ግልፅነትና ተጠያቂነት የሰፈነበትና ጥራት ያለው አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ለመዘርጋት ዋና ማነቆ ነው፡፡ በዚህ ረገድ ሥር-ነቀል የሆነ ለውጥ ማድረግ ካልተቻለ ሕዝቡን ክፉኛ እያማረረ ያለውን የመልካም አስተዳደር እጦት ችግርን በዘላቂነት መቅረፍ አይቻልም፡፡
የፖለቲካ ተሃድሶ መሰረታዊ ዓላማው የብዙሃኑ የሕብረተሰብ ክፍል እኩልነት፣ ነፃነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የተረጋገጠበት ፖለቲካዊ ሥርዓት – ዴሞክራሲ – መገንባት ነው፡፡ ይህ በሕገ-መንግስቱ ዋስትና የተሰጣቸውን የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ያለ ምንም መሸራረፍ ማክበርና ማስከበር ይጠይቃል፡፡ ይህ ደግሞ በተራው በተለያየ ግዜ የወጡና የዜጎችን መብትና ነፃነት የሚገድቡ ፖሊሲዎችን፣ አዋጆችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን፣ እንዲሁም ከሕገ-መንግስታዊ መርሆች ውጪ የሆኑ ሥራና አሰራሮችን ሙሉ ለሙሉ መቀየር ያስፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት፣ የኢህአዴግ መንግስት ሊያከናውናቸው ከሚገቡ
- የታሰሩ ፖለቲከኞችን፣ ጋዜጠኞችን፣ የመብት ተሟጋቾችን እና ሌሎች የፖለቲካ እስረኞችን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መፍታት፣
- የዜጎች ዴሞክራሲያዊ መብቶችን የሚገድበውን የፀረ-ሽብር አዋጁን መሻርና ከሕገ-መንግስቱ ጋር በተጣጣመ መልኩ እንደገና ማርቀቅ፣
- የመንግስትና የግል ሚዲያ ተቋማትን ሥራና አሰራር ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ ማድረግ፣ ለዘርፉ እድገት ማነቆ የሆነውን የመረጃ ነፃነትና ሚዲያ አዋጅ ከሕገ-መንግስቱ ጋር በተጣጣመ እንደገና ማርቀቅ፣
- የሙያና ሲቪል ማህበራት በሀገሪቱ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ምቹ ሁኔታ መፍጠር፣ ለተቋማቱ አንቅስቃሴ ማነቆ የሆነውን የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ማቋቋሚያ አዋጅ እንደገና ማርቀቅ፣
- የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችን እና ሌሎች የፖለቲካ ኃይሎችን “ፀረ-ስላም…ፀረ-ሕዝብ…ፀረ-ልማት” ብሎ በመፈረጅ የጠላትነት መንፈስ እንዲያቆጠቁጥ ከማድረግ ይልቅ መልካም ግንኙነት ማዳበርና ለብሔራዊ መግባባት መስራት ይጠበቅበታል፡፡
ባለፉት ሁለት አመታት ውስጥ የኢህአዴግ መንግስት ከላይ ከተጠቀሱት ዋና ዋና ተግባራት አንዱን እንኳን ተግባራዊ አድርጓል? አላደረገም! ከዚያ ይልቅ፣ በሶማሌ ክልላዊ መስተዳደር አመራርና ልዩ ፖሊስ አማካኝነት ከላይ የተጠቀሱት የለውጥ ጥያቄዎች ዳግም እንዳይነሱ ለማድረግ፣ በዚህም የለውጥና መሻሻል ንቅናቄውን በእጅ አዙር ለማዳፈን ጥረት እያደረገ ነው።
በሁለቱ ክልሎች መካከል ግጭት በመፍጠር ወይም እንደ መንግስት የሚበቅበትን ድርሻና ኃላፊነት ከመወጣት ይልቅ ዳር-ቆሞ በመመልከት ላይ ይገኛል። በመሆኑም እንደ መንግስት ድርሻና ኃላፊነቱን በተግባር መወጣት ተስኖታል። ስለዚህ በግልፅ የፌደራሉ መንግስት መዋቅሩን ተከትሎ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ተስኖታል። በአጠቃላይ የፌደራሉ መንግስት በተግባር ወድቋል፥ አልቆለታል፥ አብቅቶለታል፥…. ኦሮማይ!!