>

ባርነትንም ባቅሙ መልክ አለው (መስቀሉ አየለ)

በትግሬ አገር አንድ ተረት አለ አሉ። ስለ አካባቢው ህብረተሰብ ስነልቦና የሚናገር ይመስለኛል። ሰዎቹ አህያቸው ታመመባቸውና አዋቂ ፍለጋ ወደ ጎንደር መጡ። አህያውን ይዘው መሆኑ ነው። ነገር ግን ገና አዋቂ ሳያየው ሌሊቱን ሞቶባቸው ቢያድር የሞተውን አህያ ተሸክመው እንደና ትግራይ ገብተዋል። “ለመብላት ለመብላት የአገራችን ጅብ ይብላው” ሲሉ ነው። ዘረኛ ህብረተሰብ ከዚህ በላይ ማሰብ ቢቸግረው አይገርምም።
ሰሞኑን “ገዱ ተሰደበብን” ያሉ አማራ ነን የሚሉ ሰዎች ለገዱ ያላቸውን መቆርቆር ሲያራግቡ እያየ ነው። “ምንም ይሁን ምን ደሙ ደማችን ነውና ገዱ ሲሰደብ ማየት አንሻም” ማለታቸው ነው። “በግል የተጠቀምነው ነገር ባይኖርም ህወሃት የሚያደርገውን ነገር የመደገፍ የዘር ግዴታ አለብን” እንደሚሉት ትግሬዎች መሆኑ ነው።

ወያኔ እናት ኢትዮጵያን ሲያያርድ፣ ህዝባችንንም ሲደፍር (ሬፕ ሲያደርግ ) የኖረው ብአዴንና ኦህዴድን በመሰሉ ስቴሮይድ ተጠቅሞ መሆኑን እያወቅን ለነዚህ የራሳቸው ክብር ለሌላቸውን አሽከሮች የምናድርገው መቆርቆር እንዴት ቤት እንደሚመታ ግልጽ አይደለም።
ለዚህ አይነቱ አጋጣሚ በጣም ጥሩ ምስላኤ የሚሆነው ታሊባን ስለ ባራክ ኦቦማ ወደ ሁዋይት ሃውስ መግባት አስመልክቶ የተናገረው በጣም ወደ ጽንፍ የተገፋ አገላለጥ ነበር።
እንዲህ አለ። “ባርነት ሁለት አይነት ነው። አንዱ የመስክ ባሪያ ነው። ውሎው በውጭ ስለሆነ ጌታውን ቶሎ ቶሎ አያይም። ሰርቶ ሲደክመው ያርፋል። ቢቆዝም ያንጎራግራል። ቢበላ ብቻውን ቢጸዳዳ ብቻውን ነው። ስራው ድካም ቢበዛብትም አንጻራዊ ነጻነት አለው።

የቤት ውስጥ ባሪያ ግን ጌታው በወጣ በገባ ቁጥር የሚያጎነብስ፣ ማታ ማታ የእመቤቱን እግር የሚያጥብ፤ ጠዋት ጠዋት የጌታውን ያደረ ሽንት የሚደፋና እነሱ ባነጠሱ ቁጥር መሃረብ ይዞ የመሮጥ ግዴታ ሁሉ ያለበት ይልቁም በበረት ውስጥ ካሉት የጋማ ኩብቶች የተሻለ ለአይን የማይቆረቁር ነው..” ነበር ያለው። ለኔ ገዱም ሆነ ደመቀ መደባቸው ከዚህ አይነት የቤት ውስጥ ባሪያ የተሻለ አይደለምና ባርነትን እንደ ኒሻን አጎንብሰው በመቀበል የህዝባቸውን ሲቃ ለሚያራዝሙ እሪያዎች ገና ለገና አማራ ናቸው ስለተባለ ብቻ ግዜ የተረፈን ይመስል ዛሬ የመታገያ አጀንዳ መሆናቸው ተገቢ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን ትግሉ የደረሰበትን ደረጃ በቅጡ ያለመረዳት ጭምር ይመስለኛል። እናት ኢትዮጵያ የሚባክን ነቑጥ ሰአት የላትም።

ዋናው ነገር “አብርሃምን በምግባር መምሰል እንጅ አብራሃም አባት አለን ማለት የሚያዋጣ አይምሰላችሁ” ሲል ጌታ በወንጌል እንዳጸናው ሁሉ አገር የማዳኑም ትግል ከዘር ይልቅ መርህን መሰረት ያደረገ ይሁን የምንለው ለዚህ ነው።
Filed in: Amharic