>
5:13 pm - Wednesday April 20, 7718

‹‹በአባቶቻቸው የማይኮሩና ለልጆቻቸው የማይጨነቁ በቅሎዎች ብቻ ናቸው፡፡››

(ወዲ ሻምበል ዘ-ብሔረ ኢትዬጵያ)
በዚያድባሬ ወረራ የተነሳ ተነስ ታጠቅ ዝመት ተዋጋ እናሸንፋለን በማለት ነበር የቀድሞው የኢትዮጵያ መሪ ኮለኔል መንግስቱ ኃይለማርያም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ያደረጉትን ጥሪ አፋጣኝ መልስ በመስጠት ቀፎው እንደተነካበት ንብ መላው የአገራችን ህዝብ ወራሪዎችን በሚገባቸው ቋንቋ ለማናገር ከዳር እስከዳር የተንቀሳቀሰው።
ታዲያ በምድር እና በሰማይ ከነበሩት ጀግኖች መካከል ወደር የማይገኝለት የአገሪቱን የላቀ የጦር ሜዳ ጀብዱ ተሸላሚዎች ብርጋዴር ጀነራል ለገሰ ተፈራና ወታደር ሚልሻ አሊ በርኬ ግንባር ቀደም ተጠቃሾች ናቸው። ጀግንነት የፈፀሙት ለክልል ወይም ለጎጥ እንዲሁም ለተገኙበት ብሔር አልነበረም ኢትዬጵያዊነት በሚሉት ፍቅር ተለክፈው የቆየውን የአባቶቻቸውን ታሪክና ድንበር ላለማስደፈር በነብሳቸው ተማምለው ከዚች አገር በፊት እኛ እንለፍ ብለው ወራሪውን ዶግ አመድ አደረጉት።
ዛሬ ዛሬ አባቶቻቸው ለዚህች ሃገር ያደረጉትን ነገር ሁሉ በዜሮ አባዝተውታል፤ ከአድዋ እስከ ካራማራ፣ እስከ ቀይባህር ድረስ ያፈሰሱት ደም ጭራሽ ለቅኝ ግዛት እንደዳረጋቸው በድፍረት ይናገራሉ፣ እንደባንዳም ይቆጥሯቸዋል፡፡ ልጆቻቸውን ደግሞ በማይቆም የጦርነት አዘቅት ውስጥ ለመክተት ያለእረፍት ይደክማሉ፡፡ እነዚህን ሰዎች ልብ ስል ሮበርት ኢንገርሶል የተባለው አሜሪካዊ ፖለቲከኛ ያለውን አስታውሳለሁ፣ ሮበርት ምን አለ ….. ‹‹በአባቶቻቸው የማይኮሩና ለልጆቻቸው የማይጨነቁ በቅሎዎች ብቻ ናቸው፡፡››
ዛሬ ኢትዮጵያ ህወሃት በተባለ ደደቢት ላይ የበቀለ የመርገም ዛፍ አገር ስትታመስ ኢትዬጵያዊ ሁሉ በምስራቅ ድንበር ላይ ህይወቱን እንዳልገበረ ይህ ያንተ መሬት አይደለም ያኛው የእኔ መሬት ነው በሚል እርስ በእራሱ እንዲጫረስ ህወሃት በቀደደለት ቦይ ሲፈስ ሲታይ በጣም ያማል። ዛሬም ቆም ብለን ካሰብንበት ህወሃትን እድሜውን ለማሳጠር በአንድነት ሁነን ካልታገልነው በተናጠል ማንም ነፃ አይወጣም ትርፉ የወያኔን እድሜ እያራዘሙ ከመኖር በስተቀር።ክብር ለኢትዬጵያ የቀድሞው ሰራዊት በአራቱ መአዘን ለተሰዉትና አካላቸው ለጎደለ እንዲሁም በህይወት ላሉት በተጨማሪም ለመላ ቤተሰቦቹ
Filed in: Amharic