>
5:13 pm - Friday April 19, 5241

የከሸፉ ጎንደርን የማፍረስ ሴራዎች (ቬሮኒካ መላኩ)

የጎንደርን ትክክለኛውን ” የታሪክ ወርክሾፕ›› አጠር አድርገን እንመልከት ። ትንታኔአችንን ” ታሪክ ራሱን ይደግማል “ በሚለው የፈላስፎች ሐልዮት ላይ መሰረት አድርገን በታሪክ መነፅር ወደ ኋላ እንምዘግዘግ። ያለፈውን የ300 አመታት ታሪክ ወደ ኋላ ተመልሼ የማነሳው ትግሬዎች ጎንደርን ለማጥፋት የመሰረት ግንባታው ደርዝ መያዝ የጀመረው የዛሬ 300 አመታት በ18ኛው ክዘ መሆኑን ለማስመር ነው። የረዘመውን የከሸፉ አገር የማፍረስ ሸፍጦች እጅግ በጣም አሳጥሬ ልከትበው።

ጎንደር በ400 አመታት አስደናቂ ታሪኳ ሶስት ጊዜ ህልውናዋን የሚፈታተን መንገራገጭ ደርሶባታል። ይሄ የአሁኑ አራተኛው መሆኑ ነው። የሚገርመው ነገር ሶስቱም የጎንደር መንገራገጭ ሸፍጥ የተጎነጎነው ከትግራይ በመጡ ሰዎች ነው። የአሁኑም አራተኛውም የተሸረበው በእነሱው ነው። ትግራዮች ጎንደርን ለማጥፋት መሃላ የገቡ ቢመስሉም አንድም ቀን ተሳክቶላቸው አያውቅም።
1~ የመጀመሪያው ሴራ
የመጀመሪያው ሴራ የተሸረበው በአፄ ኢያሱ አድያም ሰገድ ላይ ነው።
ይሄ ሴራ ታላቁን ንጉስ ህይወት ሲያስከፍል ጎንደር ግን ከተሸረበባት ሴራ አገግማ ታላቅነቷን ጠብቃ መቀጠል ችላለች።
እያሱ አድያም ሰገድ ወይም ‹‹ታላቁ ኢያሱ›› የተባለው ኢትዮጵያዊ ንጉሥ ከ1683-1706 የገዛና እጅግ ገናና ከሚባሉት ነገስታት አንዱ ነበር። የፈረንሳዩ ሉዊ 16ኛ በአውሮፓ “ፀሃዩ ንጉስ ” እየተባለ ሲጠራ የሉዊ አቻና ወዳጅ የነበረው እያሱ አደደያም ሰገድ ደሞ “ታላቁ ንጉስ ” በመባል ይጠራ ነበር።
በ “ታላቁ እያሱ ” ዘመን የኢትዮጵያ ግዛት እስከ ሱዳኗ ስናር ድረስ የተዘረጋ ነበር ።

በአፄ እያሱ አድያም ሰገድ ዘመን ጎንደር አለም አቀፍ ዝና ያተረፈች የፖለቲካና ንግድ መአከል ነበረች። በጎንደር አካባቢ የነበረው እድገት በዘመኑ በአውሮፓ ከነበረው ስልጣኔ የሚወዳደር እንደነበር ተረጋግጧል።

በ1699 አም ከፈረንሳይ መንግስት ተልኮ ጎንደር የገባው ዶ/ር ቻርልስ ጃክዌዝ ፖንሴት እንደፃፈው << ገና ጎንደር ስትገባ ከተማው ትልቅ መሆኑን ትመለከታለህ ። አንተን የውጭ ሰው አውሮፓዊ ነህ ብሎ ዘውር ብሎ የሚመለከትህ ሰው የለም ። መጀመሪያ ግር ቢለኝም ምክንያቱ የገባኝ ወድያውኑ ነው። ጎንደር የግሪኮች ፣ ፖርቱጋሎች ፣ አርመኖችና አረቦች መናሀሪያ የሆነች ትልቅ ከተማ በመሆኗ ለአገሬው ሰው አውሮፓዊ ብርቁ አልነበረም። ጎዳናው አስፋልት ያልለበሰ ሰፊ አውራ ጎዳና ነው፣ የቤቶቹ አሰራር እንደ አውሮፓ ከተሞች ያምራል ።>> በማለት ዘግቧል።
ወደ መጀመሪያው ሴራ ስንመለስ ” ታላቁ እያሱ ” በከፍተኛ ብቃት አገሪቱን በአንድነትና በፍቅር አስተሳስሮ በመምራት በነበረበትና በመጨረሻዎቹ የስልጣን ዘመኑ ከትግሬ በምትወለደው ሚስቱ ወ/ሮ መለኮታዊት ፣ በሚስቱ ወንድም የትግሬው ራስ ፋሪስ ሴራ መጎንጎን ጀመሩ።
የዚህ ሴራ አላማ አፄ እያሱ አድያም ሰገድን ከስልጣኑ ፈንቅሎ ከትግሬዋ ሚስቱ ለሚወለደው ተክለሀይማኖትን ማንገስ ነበር። ይሄ ሴራ የመጀመሪያ ግቡን መትቶ አፄ እያሱ አድያም ሰገድን በአሰቃቂ ሁኔታ ካስገደሉት በኋላ ተክለሀይማኖትን አነገሱ።
ህዝቡም ከትግሬ እናቱና አጎቱ በማሴር አባቱን ገድሎ የነገሰውን ተክለሀይማኖትን ” ርጉም ተክለ ሀይማኖት ” በማለት ይጠራው ጀመር።
“ርጉም ተክለ ሀይማኖት ” ብዙ አመት ሳይገዛ በነገሰ በሶስተኛው አመት ተገድሎ የአፄ እያሱ አድያም ሰገድ ህጋዊ ወራሽ በንጉስነት ተሾመ ። ጎንደርም ከዚህ ሸፍጥ መዳን ቻለች።
2~ ሁለተኛው ሴራ ~ 
በ1762 ዓ.ም የትግራዩ ተወላጅ ራስ ስሑል ሚካአል ወደ ጎንደር ብቅ አለ ። ብዙም ሳይቆይ ተንኮልና ሴራ መጎንጎን ጀመረ። ይሄ ትግሬ ጎንደር ቤተመንግስት ከገባ ጀምሮ ቤተመንግስቱ ሰላም አጣ ። ትንሽ ቆይቶ ንጉስ ኢዮአስን ጎንደር ቤተ-መንግስት ውስጥ በሻሽ አንቆ ገደለ፡፡ አፄ ኢዮአስን ከገደለ በኋላ ልኡላን በግዞት ከሚቀመጡበት ወህኒ አምባ ዮሀንስ የተባለ የ80 አመት ሽማግሌ አነገሰ ። እርሳቸውንም ትንሽ ቆይቶ በመርዝ አስገደለ። ህዝቡም ይሄን በላኤ ሰብ ” ቀታሌ ንጉስ ” እያለ መጥራት ጀመረ። ጎንደር የቁልቁለት ጉዞ ጀመረች።ከዚያ በኋላ የየክፍላተ-ሐገሩ መኳንንቶች አንገዛም በማለት ተበታተኑ፡፡ ስለዚህ ከራስ ስሁል እስከ ታናሹ ራስ አሊ ድረስ (ከ1762 -1845) ዘመነ-መሳፍንት ተባለ፡፡
በመጨረሻ በዘመነ መሳፍንት የተከፋፈለችውን እና ለመሞት ነፍስ ግቢ እና ነፍስ ውጭ ስትል የነበረችውን አገር አፄ ቴዎድሮስ ከጎንደር ተነስቶ ኢትዮጵያን ዳግም አንድ አደረጋት ።
3 ~ ሶስተኛው ሴራ ~ 
በትግሬው ሚካኤል ስሁል ተዳክማ ለመሞት በማጣጣር ያለችውን አገር ቴዎድሮስ ከጎንደር ተነስቶ ነፍስ ቢዘራባትም ሶስተኛው ሴራ አሁንም ከተከዜ ማዶ ከትግራይ ተጀመረ። የዚህን ሴራ ከሌሎቹ የሚለየው የውጭ ሀይል እርዳታ የነበረበት መሆኑ ነው። በዝብዝ ካሳ ወይም የንግስና ስሙ አፄ ዮሀንስ የሚባል ሰው ጠንካራ መሆን የጀመረችውን አገር ለማሰናከል ከእንግሊዝ ጋር ሴራ ማሴር ጀመረ። ሴራውም ግቡን መትቶ በሮበርት ናፒየር የሚመራ ጦር አገሪቱን እንድወርር ስንቅ በማቀበልና ጓዝ በመሸከም ኢትዮጵያን በእንግሊዝ እንድትወረር ተባበረ ። የህዝቡ ሁኔታ ያላማራቸው እንግሊዞች ኮሎኒ ሊያደርጉት ያሰቡትን አገር ጥለው ወጡ። ዮሀንስ ግን አገሩን ለውጭ ወራሪ ማመቻቸቱ የሴራው አንድ አካል ነው።
4~ አራተኛው ሴራ የቅማንት ካርድ ይዞ መጥቷል። ጎንደር ባለፉት 300 አመታት የጥፋት ሴራ ቢደገስላትም ሸፍጡን አፈራርሳ መትረፍ ችላለች ።
የኢትዮጵያ የባለፉት 400 አመታት ታሪክ የሚነገረን ትግሬ እያፈረሰ፤ ጎንደሬ እየካበ በመውደቅና በመነሳት አዙሪት ውስጥ የሚንከባለለው አሳዘኙን የኢትዮጵያ ታሪክ ነው።

የአለምን ታሪክ መለስ ብለን ካሰላሰልነው ስርዓት እንደ ሰው ሲወለድ፤ ሲያረጅና ሲሞት ይነግረናል፡፡ ነባራዊና ህሊናዊ ነገሮች ሲሟሉ የአሮጌ ስርዓት ሞትና የአዲስ ስርዓት ልደት ይበሰራል።የሟቹን ስርዓት ተዝካር በልቶ፤ አዲሱ ስርዓት ይቆማል።
ዛሬ ወያኔ አመል ሆኖበት በአገሪቱ አራቱም መአዘን የለኮሰው እሳት ራሱን ሊበላው እየተቃረበ ነው። የህዝብ የለውጥ ንቅናቄ እንደ ውቂያኖስ ማዕበል እየሰገረና እየፎገላ መጥቶ፤ የስርዓቱን አስኳል የሆነውን ወያኔ በእሣት ምላሱ ለመላስ እየተንደረደረ ነው።
ይሄ ሴራ ተፈጥሮው የሆነው አናሳ ቡድን ሌሎችን አጠፋለው ሲል ራሱ ለመልዐከ ሞት እጁን ሰጥቶ ከምድረ ገጽ ለመሰናበት እና ወደ ታሪክ ቅርጫት ሊገባ አንድ ሳምንት ቀርቶታል። እኛም በመቃብር ሳጥኑ ላይ ትልቁን ሚስማር ገድግደንበት ወደ ጥልቅ ጉድጓድ ለመወርወር ዝግጅታችንን ጨርሰናል።

Image may contain: outdoor
Filed in: Amharic